Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, March 24, 2015

በሰሜን ጎንደር የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዘዙ

በሰሜን ጎንደር አካባቢ የታየውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዘዙ

ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር አካባቢ የታየውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የአገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ካለፈው ሃሙስ ቀን ጀምሮ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዛዋል።
Ethiopian soldiers ride on an army truck on the road to Afgooye, south of Mogadishu
የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል አባላት ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ ከግቢ እንዳይወጡ ሲታዘዙ የተወሰኑት ደግሞ ከደብረዘይት እና ድሬዳዋ አየር ሃይል  ወደ መቀሌ አምርተዋል። ብዛት ያለው የእግረኛ ሰራዊትም ወደ ኤርትራና ሱዳን ድንበሮች አቅንቷል።
ወታደራዊ ልምምዶችና አዳዳስ ምልመላዎችም እየተካሄዱ መሆኑንም ምንጮች ገልጸዋል።
ማንነታቸው በውል ያልታወቀ የተቃዋሚ ሃይሎች ጎንደር ከተማ ውስጥ የሚሊሺያ አዛዥ የሆነውን ኮማንደር ተፈራን ገድለው  ካመለጡ በሁዋላ፣ እነሱን ለመያዝ መጋቢት 12 አርማጭ ልዩ ቦታው እንኮይ ተራራ ላይ በተደረገ ጦርነት ፣ ከተቃዋሚዎች በኩል ሻምበል ይርዳውና
አዲሱ የተባሉ  ሲገደሉ፣ ከመንግስት ታጣቂዎች በኩል ደግሞ  የልዩ ሃይል አባል የሆነው  እባበይ እንዲሁም አንድ ስሙ በውል ያልታወቀና ሁለት የሚሊሺያ አባላት ተገድለዋል። ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ጀምሮ እስከ ምሽት በቀጠለው የተኩስ ልውውጥ፣ አንድ ተማሪ በመንግስት
ሃይሎች ተገድሏል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ምሽት ላይ አካባቢውን ጥለው መውጣታቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስትን አስተያየት ለማካተት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።

No comments:

Post a Comment

wanted officials