Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, March 11, 2015

ሰበር ዜና የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ኦማር በዋሽንግተን ዲሲ ዛሬ ተቃውሞ ደረሰበት

የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት በዋሽንግተን ዲሲ ለደረሰባቸው የኢትዮጰያውያን ተቃውሞ የብልግና ምላሽ ሰጡ።
መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር በዋሽንግተን ዲሲ ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጠማቸው።
ፕሬዚዳንቱ በተገኙበት ሆቴል የተገኙ ኢትዮጰያውያን ፦” ሰውዬው እጃቸው በደም የተጨማለቀ፣ የሱማሌ ክልል ወጣቶችን በመግደል በዘር ማጥፋት ክስ የተመሰረተባቸውና እና ለዚህም በዓለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ሊጠየቁ የሚገባ ወንጀለኛ መሆናቸውን በማውሳት ከፍ ያለ ተቃውሞ አሰምተዋል።
በደረሰባቸው ድንገተኛ ተቃውሞ የተበሳጩ የመሰሉት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሀመድ በተደጋጋሚ ጸያፍ ቃል ሲናገሩ ተደምጠዋል። ስለ ሁኔታው መረጃ ደርሰሠቸው በስፍራው የደረሱ የሴኩሪቲ ሰራተኞችም ተቃውሞውን አብረደውታል።
Somali regional chief, Abdi Mohamed (Photo Reporter)

የዲሲ ግብረሀይል አንበሶች ክንፍ ዛሬም የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንትን እንዲህ አሽማቀቁት።
ታዲያ ስዱ የወያኔ ባለስልጣን የሚናገረውን አሳፋሪ ቃል አድምጡት።
ሀገራችን በእነዚህ ቦዘኔዎች ነው የምትመዘበረው።
አጂብ!



No comments:

Post a Comment

wanted officials