Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, March 31, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ለ10ኛ ጊዜ ተመለሰ

የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ለ10ኛ ጊዜ ተመለሰ
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክትን አላስተላልፍም ብሎ መመለሱን ዛሬ መጋቢት 21/2007 ዓ.ም ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡ ፋና የሰማያዊ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ‹‹አላስተላልፍም›› ብሎ የመለሰው፤-
• ህወሓት/ኢህአዴግ የሚባል ገዥ ፓርቲ በኢፌድሪ የመንግስት አወቃቀር ውስጥ የሌለ በመሆኑ፣
• በጎሳ ላይ የተመሰረተ የፌደራል ስርዓት የሚለው በትክክል ስላልተገለጸ፣
• ብሔር ብሔረሰቦች መሃል ተፈጠሩ ተብለው በዝርዝር የቀረቡት ጉዳዮች አንዱን ብሄር ከሌላው ብሔር ጋር እንዲጋጭ የሚያነሳሱና ግጭትን የሚያራግቡ ናቸው በሚል ነው፡፡
ሚዲያዎች የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክትን ‹‹አናስተላልፍም›› ብለው ሲመልሱ የፋናው ለ10ኛ ጊዜ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials