መንግስት- የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት አባላት ናቸው ባላቸው ሁለት የመቀሌ ነዋሪዎች ላይ የሽብርተኝነት ክስ መሰረተ
መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ውስጥ አባላትን ሲመለምሉና መንግሥትንና ተቋማቱን ሲሰልሉ ተደርሶባቸዋል፣ እና የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ዴምሕት) ቡድን ምልምሎች ናቸው>> ባላቸው ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ ዐቃቤ ህግ ክስ መሠረተ፡፡
<<የወንጀሉ ድርጊት በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የአይዲዎሎጂ ዓላማን ለማራመድ፣ ሕዝብን ለማስፈራራትና በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ሲንቀሳቀሱ ነበር>> ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው፣ ነዋሪነታቸው በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሆኑት አቶ አማረ ተወልደና አቶ ታሪኩ በላይ ላይ ናቸው፡፡
የፌዴራል አቃቤ ህግ በክሱ ፦<<ተከሳሾቹ የሽብር ቡድን ነው ከተባለው ድርጅት ጋር በስልክ በመገናኘት፣ አባል በመሆንና መመርያ በመቀበል ኢትዮጵያ ውስጥ አባላትን በመመልመል፣ የኢትዮጵያ ተቋማትን በመሰለልና መረጃ አሳልፈው በመስጠት በሽብር ወንጀል ውስጥ የተሳተፉ ናቸው>> ይላል።
አቃቤ ህግ አቶ አማረ ተወልደ በተባሉት አንደኛ ተከሳሽ ላይ ያቀረበው ዝርዝር ክስም ፦” ኢትዮጵያ ውስጥ እያሉ ያውቋቸው ከነበሩትና አሁን ኤርትራ ከሚገኙት የትሕዴን ወይም ዴምሕት አመራር አቶ ጐይቶም በርሔ ጋር በተንቀሳቃሽ ስልክ እየተደዋወሉ የግለሰቦችን ተንቀሳቃሽ ስልክ ይሰጡ ነበር” ብሏል።
አቶ አማረን በሽብርተኝነት ያስከሰሳቸውና አቀበሉት የተባለው መረጃም፦” የኢትዮጵያ መንግሥት -ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ እንዳይጠሩ ይፈልጋል፣ ሕዝቡ በስብሰባ እንዳይሳተፍ አፈና ያደርጋል የሚሉ” መሆናቸው በአቃቤ ህግ ክስ ተመልክቷል።።
እንዲሁም በጭላ፣ በኢሮብና በማይጨው በሚገኙ የዓረና ትግራይ ለሉዓላዊነት ፓርቲ አባላት ላይ ችግር እያደረሰባቸው መሆኑን፣ ዓረና ፓርቲ ውቅሮ ከተማ ውስጥ የተሳካ ሕዝባዊ ስብሰባ ማድረጉን፣ አቶ ብርሃነና አቶ አብርሃ በተባሉ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ስብሰባው መመራቱን መረጃ ሲያስተላልፉ ነበር ያለው አቃቤ ህግ፤ <<መንግሥት ያላደረገውን እንዳደረገና በሕዝብ ላይ በደል የደረሰ በማስመሰል ሐሰተኛ መረጃ አስተላልፈዋል ብሏል።
በትግራይ ሕዝብ ላይ የተለየ በደል እየደረሰ መሆኑን፣ በወልቃይት የስኳር ፋብሪካ ለመገንባት በሚል የአካባቢው ነዋሪዎች ያለምንም ካሳ እየተፈናቀሉ እንደሆኑ የሐሰት መረጃዎችን በማቀበል አገርን አደጋ ላይ የሚጥል እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል ያለው አቃቤ ህግ፤ <<ሁለቱም ተከሳሾች ትሕዴን የሚባል ስያሜ ያለው የሽብር ቡድን ውስጥ አባል በመሆንና ከቡድኑ አመራሮች ጋር በስልክ መረጃ በማስተላለፍ፣ በፈጸሙት በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ ተከሰዋል>>ብሏል።
በኢትዮጰያ የጸረ- ሽብር ህጉም ሆነ አዋጁ የፖለቲካ ተቀናቃኝን ማጥቂያ መሳሪያ እንደሆነ በ ዓለማቀፍ ደረጃ የታወቀ ቢሆንም፤ ደምሒት ለይስሙላም ቢሆን በፓርላማው በሽብርተኝነት ባልተፈረጀበት ሁናቴ አቃቤ ህግ ተከሳሹቹን “የሽብርተኛ ድርጅት አባል በመሆን” ብሎ መክሰሱ ታዳሚዎችን አስገርሟል።
ሌላው ታዳሚዎችን ያስገረመው በሽብር ተከሳዖቹን ያስከሰሳቸውና አስተላልፈውታል የተባለው መረጃ ይዘት በግልጽ የሚታወቅና ተቃዋሚዎችና ህብረተሰቡ በየጊዜው የሚናገሩት መሆኑ ነው ያለው ወኪላችን፤ “መንግስት ተቃዋሚዎች ህዝባዊ ስብሰባ እንዲያደርጉ አይፈቅድም” ብሎ ማውራት ሀገርን አደጋ ላይ በመጣልና በሽብር ወንጀል ማስከሰሱ፤ የሽብርተኝነት ህጉ ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን መቅጫ ለመሆነ ተጨማሪ ማረጋገጫ ነው ብሏል።

No comments:
Post a Comment