Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, March 31, 2015

በኦሮሞ ስም ወያኔ የሚያቃጥለው ባንዲራ የኦሮሞዎች ነው። ምኒልክ አልነበራቸውም

በኦሮሞ ስም ወያኔ የሚያቃጥለው ባንዲራ የኦሮሞዎች ነው። ምኒልክ አልነበራቸውም

http://zabraham.blog.com/2015/03/31/tplf-in-oromo-name-burns-africans-flag/

ማስታወሻ 1:- ባንዲራ በማቃጠል ቪዲዮ የጀመረው ወያኔ ነው

ሰሞኑን እየተለቀቁ ባሉት ዘረኝነት ቆስቋሽ ቪዲዮች ሁለት ጊዜ የ ኢትዮጵያ ባንዲራ ሲቃጠል ተመልክተናል። የማቃጠል ቪዲዮውን ለመጀመሪያ ፌስቡክ ላይ የጫነው ስሙን ከሰኢድ ኢድሪስ ኣባ ገመቺስ ብሎ የለወጠ የወያኔ ካድሬ መሆኑ ተደርሶበታል። በተለይ ጸሃይ የምትባለዋ በላከችው ሀውሃት መራሽ ቁስቆሳም ሆነ ባንዲራ አቃጣዩ ንግ ግር ዉስጥ መሃሉ ላይ ኮከብ ያለው ባንዲራ ምክንያት የብሄርብሄረሰቦች እኩልነት ተከብሯል ሲሉ እንደ ኢቲቪ ይወሸክታሉ። የወያኔ ተልዕኮ መሆኑን ለመረዳት የዚሁ ቅጥረኛ ፌስቡክ አካውንት ላይ የ ኦህዴድ ደጋፊነቱን፤የመከለካያ ቀን ሲከበር የተነሳውን ማየቱ በቂ ቢሆንም አሁን ያለው ባንዲራ መሃሉ በቅርቡ በአውሮፓ በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ኮከቡ የሰይጣን መንፈስ ነው ተብሎ በመቃጠሉ ምክንያት ራሱም የተበሳጨ እንደነበረ ፌስቡኩ ላይ ያወረደውን ስድብ ቪዲዮው ላይ ለቆታል ውሾች ሲል። አያይዘውም የህወሃት ኣርማ በዋሽንገትን በመቃጠሉ ኦሮሞውን ተቆጥቷል ይላሉ። ልክ እናስገባቸዋለን እየተባለ የሚዛትባቸው ኦሮሞዎች በወያኔዎች በየቀኑ የሚገደሉት ኦሮሞዎች እንዴትም ተብሎ ወያኔን እንደማይደግፉ እሙን ነው። የሰይጣኒዝም ምልክት የሆነው አርማ ተለይቶ በአውሮፓ በተቃጠለ ማግስት እና ድምጻችን ይሰማ ትብብር የመንፈግ አዲስ ስልት ነድፎ ሙስሊሙ ወያኔን ለማርበድበድ በተነሳሳበት ሰሞን ህወሃት ይህንን ለመነጣጠል እንዲያመቸው በቪዲዮው ላይ የድሮው የኦሮሞን ብሶት በማስታከክ ክብ ውስጥ ያለው ኮከብ ብሄር ብሄረሰቦችን ይወክላል የሚለውን መርዝ እያሰራጨ ነው። ይሁንና እነሱም ሆነ ሌሎቹ እየላኩት ያለው አብዮት ለሌሎችም መጠቀሚያ ሆኗል።
በ1984 በነበረው የሽግግር መንግስት ጉባኤ ላይ የተነገረችውን አሁንም በቀጥታ ይሄንን ባንዲራ እያሳዩ ወረውናል ገድለውናል ይለወጥልን እያለ የሚደግምልን ህ ወ ህት እንጂ ማን ሊሆን ይችላል። ለዚያውም አሁንም ድረስ የሚያውለበልቡት እነሱ ብሄረሰቦችን ይወክላል የሚሉት ኮከብ ያለውን ባንዲራ ሆኖ እያለ እንደ አዲስ መጠየቅ ለምን አስፈለገ። የድምጻችን ይሰማ ሆነ በዉጪ ያሉት ሌሎች እንቅስቃሴዎች መንግስትን ለመለወጥ አፋፍ ላይ ስለደረሰ የድሮ ስርዓት ሊመጣባችሁ ነው ወያኔን ደግፉ እንጂ ለማለት እንደሆነ ግልጽ ነው። ለማንኛውም አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም የኦነግም ባንዲራ መለያ እንደሆነ ያስተውሉ።
ማስታወሻ 2:- ባንዲራችን ላይ ያለው ክብ ውስጥ የገባ ኮከብ የሰይጣን ተከታዮች አርማ ነው። የብሄር እኩልነት ምልክት አይደለም
ኢ ህ አ ዴግ ወያኔም በየዕለቱ እንደሚወሸክተው ተከታይ ካድሬዎችም በመደጋገም ብዛት እውነት ለማድረግ እንደሚጥሩት ፤በየቪዲዮው እንደሚያስተጋቡት የኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ የተለጠፈው ክብ ውስጥ የገባ ኮከብ ሆነ ጨረር እኩልነትን አያመላክትም።ኮከብ የመበላለጥ የማዕረግ ምልክት ስለመሆኑ በወታደር ቤት ያለፈ ያውቀዋል። ደረቱ ወይ ትከሻው ላይ ሁለት ወይም ከዛ በላይ ኮከብ የተለጠፈለት ፓሊስ ምንም ማእረግ ከሌለው ይበልጣል። በመጽሃፍ ቅዱስም የኮከብ ክብር ከኮከብ ክብር ይበልጣል። እውነተኛ ፌደራሊዝምን የሚጠቀሙ አንዳንድ ሃገራት ሰንደቅ አላማቸው ላይ ኮከብ ቢያደርጉም ኮከቡን በክብ ውስጥ ያስገባች ሃገር ኢትዮጵያ ናት።
በክብ ውስጥ የገባ የተጠላለፉ ሶስት ማዕዘናት የተሰራ ኮከብ ደግሞ የሰይጣን ተከታዮች አርማ እንደሆነ በአለም አቀፍ ይታወቃል።
እናም ክርስትናን ሆነ እስልምናን ቀድመው የሚያውቁ እና ለእምነቱ ሟች ዜጋ ለሚኖርባት ሃገር አሁንም ቢሆን የሰይጣን ተከታዮች ኢሉሚናቲ አርማ ሰንደቅ ኣላማችን ላይ መወገድ አለበት። የዋቄ ፈታም ሆነ በተራራ የሚያመልኩ ባንዲራ አለም አቀፉ የሰይጣን አርማ እንዲለጠፍበት አይፈቅዱም።

ማስታወሻ 3:- ኣጼ ምኒልክ ወደ ደቡብ፥ኦሮሚያ ሲዘምቱ ባንዲራ አልተጀመረም
ባለ ቪዲዮው የወያኔ ቅጥረኛ ከ 1894 እስከ 1895 አጼ ምኒልክ ወደ ደቡብ እንዲያዉም ሃዲያ ኦሮሚያ ብሎ ጠቅሶ ሲዘምቱ ባንዲራ ይዘው ነበር ይህ ባንዲራ ደም መጣጭ ነው ይለናል። በወቅቱ ግን አጼ ምኒልክ ባንዲራ በኢትዮጵያ ኣልጀመሩም። በይፋ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰንደቅ ኣላማ የተጀመረው በ ጥቅምት 1997 ሲሆን ይህም የሆነው ሁላችንም በሃገር ፍቅር ስሜት ተሳትፈን አደዋ ላይ ጣልያንን ድል ባደረግን ካንድ አመት በኋላ ነው። ሁሉም ከዳር እስከ ዳር በሃገር ፍቅር ስሜት ጣልያንን አደዋ ላይ ድል ባደረጉ ካንድ አመት በኋላ ነው። ደቡብ ወይ ኦሮሞ ላይ ዘመቻ አደረጉ በተባለበት 1895 ወቅት ድረስ ለዚህ ባንዲራ ተገዛ የሚል ዘመቻ አጼ ምኒልክ ኣላካሄዱም። ቢሆንም ግን በትገብራለህ ኣልገብርም ፍልሚያ በርካቶች መሞታቸው አይካድም።
የአሁኗ ኢትዮጵያ ቅርጽን በኣጼ አምደጽዮን ዘመነ መንግስት ከ ጀመሮ ወደ ደቡብ ሃዲያ ኦሮሚያ ሲስፋፉበት የነበር እንጂ ወያኔዎች እንደሚሉት የመቶ አመት ታሪክ አጼ ምንሊክ የተጀመረ አይደለም። እስከ 1374 ኣመተ ምህረትም ድረስ የኦሮሞዎችን እንቅስቃሴ ከዝዋይ እንዳያልፉ የተገደበ እንደነበር በርካታ ሰነዶችን መዘርዘር የሚቻል ሲሆን ጽንፈኛ ናቸው የሚባልላቸው የ ኦሮሞ ምሁር ቡልቻ ደመቅሳ ሳይቀር እንደመሰከሩት የደቡብ ኢትዮጵያ ከሰሜን ጋር መተባበር እና ኦሮሞን ማስገበር የተጀምረው ከምኒልክ በፊት ከአጼ አምደ ጽዮን 1314–1344 ንግስና ጀምሮ ነው።
እምዬ ምኒልክ ጡት ቆረጡ የሚለው ሃሰት የፈጠራ ወሬ መሆኑን ዶር ነጋሶ ጊዳዳ ሳይቀር የመሰከሩት እና ጡት መቁረጥ ብልት መስለብ እስካሁንም የአማራ ሳይሆን የጉጂ ኦሮሞ ልማድ እንደሆነ ማስተዋል በቂ ነው። ይልቁንም የአረመኔነት ተግባር የምኒልክ ጦር ላይ የፈጸሙት ኦሮሞዎች እንደነበሩ የቀረበዉን ማስረጃ ይመልከቱ። ከኣስራ ኣምስት ጊዜ በላይ አማራ ላይ የተፈጸመ ድርጊቶችን የሚቀጥለውን ሊንክ በመጫን ያንብቡ። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/11329
ይሁንና ከመቶ ሃያ አመት በፊት ለተፈጸመ ታሪክ የአሁኑ ትውልድ ተጠያቂ የሚሆንበት ብሎም ጥበበኛው ሸማኔ ዶርዜ የጠለፋት ባላክር የአንገት ስካርፍ የሚቃጠለው ምን ባደረገ ነው? እያሳዩን ሰገድንለት የሚሉት የንጉሱ ሰንደቅ አላማም ከሆነ ከደርግ መባቻ ጀምሮ ከተጣለ ከአርባ አመት በላይ ሆኖታል። በዘመነ ደርግም ቢሆን ለአስራ ሰባት አመት በህገመንግስቱ ያጸደቀው ባንዲራ መሃሉ ላይ የ አክሱም ሃዉልት በዘንባባ ተከቦ የነበረበት እንጂ ኢትዮጵያውያን ዉስጥ ያኔም መቼም የማይጠፋው ምንም የሌለበት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ምልክታችን ነው።
ደርግ በሽግግር ወቅት(1975–1987) በኢህአዴግም የሽግግር ወቅት(1991–1996) ሲጠቀሙበት የነበረው ሰንደቅ ኣላማ መሃሉ ላይ ምንም ምልክት ያልነበረበት እንደነበረ ልብ ይሏል።ደርግ በመጨረሻው ያስቀመጠው መሃሉ ላይ የስልጣኔ ምልክት የሆነውን አክሱምን ሲሆን ኢህ ኣዴግ ወያኔ ግን የሰይጣን ተከታዮች ምልክት የሆነውን ክብ ኮከቡን ውጦት የሚያሳይ አርማ ለጥፎበት ለሱ ለሰይጣን ተገዙ ይለናል።

የ ኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ባንዲራንም ያየን እንደሆነ ያሉት ቀለማት እነዚሁ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት ናቸው። ኦነግ ይሄንን የቀስተ ዳመና የሚመስለውን ቀለማት ሲመርጥ ወያኔዎች እንደሚሉት ለክርስቲያኖች አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ከሰማይ ከቀስተ ዳመና ወይ ከፈጣሪ የተሰጠን የኖህ ቃልኪዳን ነው ብሎ አምኖ እንዳልሆነ ይታወቃል።
በኦሮሞ ስም ወያኔ የሚያቃጥለው ባንዲራ የኦሮሞዎች ነው። ምኒልክ አልነበራቸውም ከኦሮሞዎች ጋር ብቻም ሳይሆን ከሌሎች ከጠቅላላው የ አፍሪካ ህዝብ ጋር መጣላት መነካካት ነው።
በ አፍሪካ ከ13 በላይ ሀገራት ይህንን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት ኣቀማመጡን በማቀያየር የሃገራቸው መለያ አድርገው የወሰዱት ከኢትዮጵያ ነው። ምክንያቱም ሶስቱ ቀለማት ቅኝ ግዛትን የማሸነፍ ምልክት የነጻነት አርማ ስለሆኑ በኛ ምልክት አፍሪካውያን ብቻ ሳይሆኑ ራስተፈሪያንም የካሪቢያን ሀገሮችም ይመካሉ።
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማትን ማቃጠል ማለት ሌሎች የ አፍሪካ ሀገራትንም መንካት ብቻ ሳይሆን ትርጉሙ ነጻነት ሳይሆን ቅኝ ገዦች ይሻሉናል ማለታቸው ነው። እንዳሉት ኢትዮጵያዊነትን ብቻ ሳይሆኑ አፍሪካዊነታቸውን ክደዋል። እኛ ጥቁር አይደለንም ምክንያቱም ኢትዮጵያ ማለት ጥቁር ማለት ነው ሲሉም ሰምተናቸዋል።
ማስታወሻ 4:- እስቲ ኢትዮጵያዊ የሚለውን ፓስፖርታቸውን ያቃጥሉት ?
በዚህ ኦሮሞ ካንዲት ጉራጌ ጋር ሲከራከሩ በሚያሳይ ሶስተኛ ቪዲዮ ላይ እና እናንተ ፈረንጅ ናችሁ ተብላ የተጠየቀችው ወያኔ ሰራሽ ኦሮሞ ስታፍር አረብ ለመሆን ሲዳዳት አይተናል።ጠያቂዋም ልክ አልጀዚራ ላይ ጃዋር መሀማድ እንደተጠየቀው አንቺ መጀመሪያ ኢትዮጵያ ነሽ ወይስ መጀመሪያ ኦሮሞ ነሽ የሚል ኮፒ የማንነት ጥያቄ ደግማለች። ሰዎች እኔ በቅድሚያ አፈር ነኝ የማለትም መብታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በአረብ ሃገር በስደት የሚኖሩ ወገኖቻቸው ኢትዮጵያዊ አይደለንም እያሉ በማስተባበር ፓስፖርት ኣልባ ሊያደርጓቸው እና ሊያሳስሯቸው የተሸረበውን ሴራ አለማወቃቸው ያሳዝናል። ለሺህ ዘመናት የኖረ ኢትዮጵያዊነት ከሚቃጠል በወያኔ በሃያ አራት አመት ጊዜ ዉስጥ የተፈጠረ ዘረኝነት ቢቃጠል ይሻላል።
ማስታወሻ 5:- ኦሮሞን እየጨፈጨፈ ያለው የህወ ሃት ባንዲራ ለተቃጠለ ኦሮሞን ጠበቃ ማድረጋቸው ታውቋል
ዝም ብለን በሰማናቸው ቁጥር እየጨመሩት ባሉት ትኩስ ቪዲዮ ላይ በአሜሪካ ተቀምጠው በርገር እየገመጡ ያሉ ኢትዮ አማሮች የህወሃትን ባንዲራ ማቃጠላቸው ኦሮሞዎችን አስቆጥቷል ይሉናል። ለመሆኑ በየቀኑ የሚታሰሩት የኦሮሞ ልጆች አይደሉ እንዴ የሀገሪቱን እስር ቤቶች የሞሉት? በቅርቡ እንኳ የኣዲስ አበባን ማስተር ፕላን ማስፋት ሰበብ ገበሬዎችን ማፈናቀሉን በተቃወሙ ተማሪዎች የተገደሉት የታሰቃዩት ሳያንስ አሁንም ልክ እናስገባቸዋለን እያለ ኦሮሞ ላይ የሚዝተው አባይ ጸሃዬ ህወሃት አይደለም እንዴ?
ሁሉም አድርባይ ይመስል እንዴት ኦሮሞዎች ወያኔን አይቃወሙም ይባላል? ከማንም ቀድሞ ብረት ያነሳው ማነው። የሰሞኑ የዘረኝነት ቪዲዮዎች ድንገት እያገረሹ ያሉት ኣማራን እና ኦሮሞን በማጣላት ህወሃት ቁጭ ብሎ ሊስቅ የጠነሰሳት ዘዴ መሆኑን ያልባነነ ሰው የለም። እውነት መስሏቸው የአይሲስን አክራሪነት አረብ ሃገር ሆነው ለማምጣት የሚፍጨረጨሩትም ሊታቀቡ ይገባል።
አለም በግሎባላይዜሽን አንድ እየሆነች ስለመጣች መገነጣጠል አይቻልም። እንደለመድነው በ ኢትዮጵያዊ ጭዋነት የጋራ ጠላት የሚሆኑብንን የ ሃይማኖት አክራሪነት፥ ዘረኝነት፥ ድህነት፥ በጋራ ብንከላከል ይበጀናል። አ ይ ሲ ስነት ሙስሊም ሃገራትን እርስ በ እርስ እንዴት እያፋጀ እንደሆነ እያየን መሰል እልቂት በ ጎጥ መናፈቅ የለብንም።

No comments:

Post a Comment

wanted officials