Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, March 25, 2015

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የካሳ ክፍያ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚዘረፍ ኦዲት መስሪያ ቤት አስታወቀ



በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የካሳ ክፍያ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚዘረፍ ኦዲት መስሪያ ቤት አስታወቀ

መጋቢት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የባለሰልጣኑ የኦዲት ሪፖርት እንደሚያሳየው በአማራ ክልል የባህርዳር ከተማ፣በምዕራብ ጎጃም ዞን የባህርዳር ዙሪያና የይልማና ዴንሳ ወረዳዎች የጣና- በለስ-ባህርዳር 400 ኪሎቮልት እና የባህርዳር- ደብረማርቆስ 400 ኪ.ቮ. የኃይልማስተላለፊያ ፕሮጀክቶች፣በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን የምስቃን ወረዳ፣በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ የወላይታ ሶዶ- አዲስ አበባ 400 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክት በካሳ ግምት ስም ከፍተኛ ገንዘብ ተበልቶባቸዋል።
የጣና በለስ – ባህርዳርየ400 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ መስመሩን ለመዘርጋት ሲባል በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ካሳ ተከፍሎ ሰዎች ከተነሱ በኋላ መስመሩ  በባህርዳርአየር ማረፊያ ክልል ውስጥ የሚያልፍ በመሆኑ ወደ 12 የሚጠጉ ምሰሶዎች
ከተተከሉ በኋላ መስመሩ በአየር ማረፊው አካባቢ ማለፍ እንደሌለበት ተቃውሞ በመቅረቡ ድጋሚ የመስመር ለውጥ ተደርጎ ሌሎች ሰዎች እንዲነሱና ሌላ ተጨማሪ መጠኑን ማወቅ ያልተቻለ የካሳ ክፍያ እንዲፈፀም መደረጉ ተገልጿል።
በኦዲቱ ወቅት በናሙና በታዩት ባህርዳር- ደብረማርቆስ- አዲስአበባ 400 ኪሎቮልት ኃይል ማስተላፊያ ፕሮጀክት እና የወላይታ ሶዶ- አዲስ አበባ 400 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጄክቶች ለሚነሱ ሰዎች አስፈላጊው የካሳ ክፍያ ሳይፈጸም እንደተፈጸመ ተደርጎ ሪፖርት መቀርቡም ተመልክቷል።
በአሉቶ-ላንጋ ጂ ኦ ተርማል ፕሮጀክት፣ አላማጣ- መሆኒ- መቀሌ ኃይል ማስተላለፍ ፕሮጀክት 230  ኪሎ ቮልት 2 ሚሊዮን 630ሺ 619 ብር ከ 83 ሳንቲም እንዲሁም በቆቃ-ሁርሶ-  ድሬዳዋ ፕሮጀክት 230 ኪሎ ቮልት 1 ሚሊዮን 423 ሺ 16 ብር ከ56 ሳንቲም በህገ ወጥ መንገድ ወጭ ተደርጎ በሃላፊዎች ተበልቷል

No comments:

Post a Comment

wanted officials