የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የአልጀሪያው -ኤል ኡልማ ቡድኖችን ጨዋታ ለማየት በባህርዳር ስታዲየም በእንግድነት የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ከጨዋታው በፊት ንግግር እንዲያደርጉ በተጋበዙበት ሰአት ጨዋታውን ለመመልከት በስቴዲየሙ የተገኘው ሕዝብ በታላቅ ቁጣ የተቃውሞ ድምጽ በማሰማቱ ንግግራቸውን እንዲያቋርጡ መገደዳቸውን የክልሉ ወኪላችን ገልጻለች፡፡
አብዛኛው ህዝብ ከተቃውሞ ድምጹ ጋር የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት በእጁ በማሳየት አቶ ደመቀ ንግግራቸውን እንዲያቋርጡ አስገድዷቸዋል፡፡
No comments:
Post a Comment