Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, March 4, 2015

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) ከዩቲዩብ ታገደ , Ethiopian TV ,EBC blocked from YOUTUBE

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) ከዩቲዩብ ታገደ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ( EBC ) ዩትዩብ ኦፊሴላዊ ቻናልን (EBC tv) መዝጋቱን ዩትዩብ በዛሬው እለት አሳወቀ። የአለማችን ትልቁ የቪዲዮ መጋሪያ የማህበራዊ ድረገፅ ዩትዩብ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በርካታ 3ኛ ወገን አካላት ኢቢሲ የቅጂ መብታቸውን በመጣስ ቪዲዮዎችን ዩትዩብ ላይ ጭኗል የሚሉ ተደጋጋሚ ክሶች በማቅረባቸው መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል። ኢቢሲ በዩትዪብ በኩል እንደዚህ “ብሔራዊ ውርደትን” የተከናነበ የመጀመሪያው የመንግሥት ተቋም ሳይሆን አይቀርም። ኢቴቪ(ETV) ስሙን ወደ ኢቢሲ(EBC) ከመቀየሩም በፊት ከፊፋና ካፍ እውቅና ውጪ በሕገ ወጥ አለም አቀፍና አህጉራዊ ስፖርታዊ ክንውኖችን በቴሌቪዥን በማሳየት ሌላ ሕገ ወጥ ድርጊት ፈፅሞ እንደነበረ ይታወሳል ።
Source- ethioforum.org

No comments:

Post a Comment

wanted officials