Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, March 22, 2015

Ethiopian fighter jets hit Ertrean Bish Mine የኢትዮጵያ ጄት አርትራን ደበደበ ተባለ



ኢህአዴግ ጦረነት አማረኝ የምትለን ነፍሰ ጡር ሆና ወይስ ለኛ ነፍስ ቁብ አጥታ!
ዛሬ እየሰማን ያለነው ዜና እንደሚያስረዳን እና እንደሚያረዳን... ኢህአዴዬ አይኗን ጨፍና ወደ ጦር ሜዳ ልትወስደን አንድ ብላ ጀምራለች። ትላንት ከኢትዮጵያ የተነሱ የጦር አውሮፕላኖች በኤርትራ ጥቃት ፈጽመዋል አሉ። እወነት ይሄ ነገር ለኢህአዴግ ይጠቅማታል... ? ለምርጫ ማስቀየሻ ተብለው የሚተኮሱ አየር ሃይሎⶭ በዛው እንደማይቀየሱ ኢህአዴግ የትኛው አዋቂ ነግሯት ነው ጦርነት የለኮሰችው! እንጃላት...


ኢህአዴግ መስተፋቅር ያሰራችበት ቢኒያም ከበደ (ቤን) እንደነገረን ከሆነ ጦርነቱ የተጀመረበት ምክንያት ያቺ አቶ ኢሳያስ 8100A ብለው ሞልተው ደረሰቻቸው የተባለችው ኢሊኮፍተር ናት አሉ! ያቺ ኢሊኮፍተር ስንት ሰው ታወጣለች...!? ከዚህ በፊት በአንድ ባድመ የተነሳ ስድሳ ሺዎች ተሰውተው ጠብ ያለልን ነገር ምን ነበር... ምንም!!!

ፌስ ቡክ ያላችሁ ወታደሮች እና የሀገሬ ወጣቶች የምነግራችሁ ነገር ቢኖር ኢህአዴግ ጦረነት አማረኝ ያለቸው ነፍሰ ጡሮ ሆና ሳይሆን ለኛ ነፍስ ቁብ በማጣቷ ነው! እንግዲህ ራሷ ከጀመረችው... ራሷ ትወጣው እንጂ፤ ጎንደር አለ በሎ ቤኒሻንጉል አለበሎ ወለጋ አለ በሎ አፋር አለ በሎ ትግራይ አለ በሎ.... ብትል ልንሰማት አይገባም!

እንግዲህ ከ አቶ ሃይሌ ጀምሮ፣ አቶ ሳሞራው አቶ ቴውድሮስ አድሃኖም፣ አቶ በረከት ስሞን፣ አቶ አባ ዱላ ገመዳ.... አቶ ሬዲ እና ሽመልስ ሳይቀሩ... ያሟሙቁ...

እኛ ኢህአዴግ ጦርነት ባማራት ቁጥር የምንማገድበት ምክንያት ያለ አይመስለኝም!

No comments:

Post a Comment

wanted officials