የማለዳ ወግ ... አፈሳውና ፣ አዲሱ የኮንትራት ስምምነት ረቂቅ መዳረሻ !
* ፍተሻ እንጅ የምህረት አዋጅ አለመኖሩ ይነገራል
* ኢትዮጵያና ሳውዲ በኮንትራት ውል ገና አልተፈራረሙም
ባለፉት ሳምንታት ብቻ በዋና ከተማዋ ሪያድ ፣ በጅዳ ፣ በመካ፣ በደማምና በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህገ ወጥ ነዋሪዎች መያዛቸው ተጠቁሟል። በቀጣይ ሳምንታትም እጅግ ከፍ ያለ ፍተሻ እንደሚደረግ ከሚሰጠው መግለጫ ባለፈ ምልክቶች እየታዩ ነው። ባሳለፍናቸው ሳምንታት በፍተሻው መኖሪያ ፍቃድ ከሌላቸው ጋር ተጎራብተው በህብረት የሚኖሩ ሳይቀር የአሰሳውና አፈሳው ሰለባ እንደ ነበሩ በርካታ ነዋሪዎች በስልክ ገልጸውልኛል።
በተለያዩ አካባቢዎች ስለተደረገው አሰሳ እና ፍተሻ መረጃ ያቀበሉኝ ወገኖች የመኖሪያ ፈቃድ ከሌላቸው ነዋሪዎች የተገኙ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ሳይቀር በስፋት መያዛቸውን ጠቁመዋል ። በተለይም ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ ይዘው የተገኙ ወንዶች ከተያዙት ሲናገሩ " ህጋዊ መኖሪያ ያለንን መኖሪያ ፈቃድ ከሌላቸው ሴቶች ጋር ፎቶ እያነሱ አሰሪዎቻችን ሊያስ ፈቱን ሲመጡ ህገ ወጥ ስራ ሲሰሩ ያዝናቸው!" በማለት አሳሪዎች ምክንያት እንደሚሰጡ መረጃውን ያደረሱኝ ወገኖች ገልጸውልኛል ። በሪያድ አካባቢ የተያዙት በበኩላቸው ከተያዙ በኋላ ከእስር ለመውጣት እስከ 6000 ሪያል እንደሚከፍሉና በሙስና ከእስር ስለሚለቀቁ ፖሊሶች ይህን ለምደው በሰላማ ዊ ህጋዊ ነዋሪዎች ላይ ጫና እያደረጉ መሆኑን በርካቶች ይናገራሉ ። እዚህ ጅዳ አካባቢም ከወትሮው ጠንከር ያለ ህገ ወጥ ነዋሪዎችን የማጽዳት ዘመቻ የተጀመረ መሆኑ የተጠቆ መ ሲሆነ በአንዳንድ አውራ ጎዳናዎች በተቀናጀባ በተደራጀ መልኩ የመንገድ ላይ ፍተሻ ሲደረግ የመታዘቡ እድል አጋጥ ሞኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሀገሪቱ ታዋቂ ጋዜጦችን ምንጭ የጠቀሰው በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስል መ/ቤት ፍተሻው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመጠቆም ዜጎች በእንቅስቃሴያ ቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የዜጎች ላይ ድጋፍ ለማድረግ ክትትል እንደሚያደርግ ያልተለመደ ምክር መለገሱ ይታወሳል።
የሳውዲ ታዋቆ ጋዜጦች ህገ-ወጦችን ለማጽዳት ባለፉት ሳምንታት በዋና ከተማዋ ሪያድ ኢትዮጵያውያን የሚገኙባትን የመንፉሃን መንደ ር ጨምሮ በተለያዩ መንደሮች መጠነ ሰፊ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መያዛቸውን አስታውቋል ። ጋዜጣዎች በማከልም በዘመቻው የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ህገ ወጥ ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ እንደ ነበርና የተያዙት ህገ ወጦች አስፈላጊው ን ቅጣት አግኝተው ወደ ሀገራቸው እንደሚሸኙ የጋዜጠው ዘገባ ጠቁሟል።
በሳውዲ የመን ድምበር ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያው ያን ወደ ሳውዲ በመግባት ላይ መሆናውን የአይን እማኞች ሲጠቁሙ በድንበር አሰሳው ቁጥራቸው ቀላል የማይባል መያዛቸው ተጠቁሟል።
በዚሁ የመን ሳውዲ ድንበር 20,424 ህገ ወጦችና 2,813 አሸጋጋሪዎችና ለመሸጋገሪያ ይጠቀሙባች የነበሩ 1,634 መኪናዎች መያዛቸውን ከድንበር ከተማዋ ጅዛን የሚሰራጩ መረጃዎች ያመለክታሉ ።

No comments:
Post a Comment