Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, March 9, 2015

የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺና አብርሃ ደስታ ችሎት ደፍረዋል በሚል ማክሰኞ ሊቀጡ ነው



የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲ አመራሮች የነበሩት የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺና አብርሃ ደስታ በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ጉዳያቸው እየታየ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ‹‹ችሎት ደፍራችኋል›› በሚል ቅጣት ሊጣልባቸው ነው፡፡ ወርቅ አገኛው 
በሳለፍነው አርብ የካቲት 27 ቀን 2007 ዓ.ም በነበረው ችሎት ሐሙስ የካቲት 26 ቀን 2007 ዓ.ም በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ የሺዋስ፣ ዳንኤልና አብርሃ ‹‹በፍርድ ቤቱ ላይ አላግጣችኋል፣ የችሎቱን ሥራ ረብሻችኋል፣ ...ወዘተ›› በሚል በችሎት መድፈር ወንጀል ክስ በማሰማት የችሎቱ ሰብሳቢ ዳኛ አርብ ዕለት ጥፋተኛ ብለዋቸዋል፡፡ 
የሺዋስም በፍርድ ቤት ላይ እምነት እንደሌለው በመግለጽ አስተያየቱን ሊነገር ቢጥርም ፍርድ ቤቱ ከቅጣት አስተያየት ውጪ እንዳይናገር በተደጋጋሚ ከልክሎታል፡፡ ዳንኤል ሺበሺ እና አብርሃ ደስታም በተመሳሳይ መልኩ የቅጣት አስተያየት እንዲሰጡ ተጠይቀው ስለተፈጠረው ነገር እና ችሎቱ ችግራቸውን እንዳልሰማቸው በመጥቀስ የቅሬታ አስተያየታቸውን በየተራ ለመናገር ጥረት ቢያደርጉም ፍርድ ቤቱ ከቅጣት አስተያየት ውጪ ምንም እንዳይናገሩ ንግግራቸውን በተደጋጋሚ ሲያቋርጥ ተመልክቻለሁ፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፣ አብርሃ በተናደደ ስሜት ውስጥ ሆኖ፣ ለችሎት አስተያየቱን ለመስጠት ጥረት ሲያደርግ በችሎቱ የነበሩ መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶች መሳሪያቸውን ጠበቅ አድርገው በመያዝ ወደእስረኞቹ ሲጠጉ እና አብርሃን የሺዋስ ወዳለበት ቦታ እንዲቀይር ሲያስገድዱት ታዝቤያለሁ፡፡
ፍርድ ቤቱም በዚሁ ዕለት የተጠቀሱት ተከሳሾች ‹‹ችሎት እያወኩ ነው›› በሚል በድጋሚ በመናገር ከነገወዲያ የካቲት 30 ቀን 2007 ዓ.ም ቅጣት ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ሀብታሙ አያሌውም ‹‹መደበኛው ችሎት መቼ ይቀጥላል?›› በማለት ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን የሰባተኛ ተከሳሽ ክስ ተስተካክሎ ማክሰኞ እንደሚቀርብና ከቅጣት ውሳኔው በኋላ እንደሚቀጥል የዕለቱ ሰብሳቢ ዳኛ ተናግረዋል፡፡ እነየሺስ፣ ዳንኤል፣ አብርሃና ሀብታሙ ደስ በማይል ስሜት እንደተናደዱ እጃቸው በአንድ ካቴና ለሁለት እየታሰሩ ከችሎት ወጥተዋል፡፡
በዚህ ዕለትና ችሎት ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ እና ጦማሪ አቤል ዋበላ ነበሩ፡፡ ከርቀት ለምን እንደመጡ ስጠይቃቸው ‹‹ለምስክርነት›› አሉኝ፡፡ እስከግማሽ ቀን ድረስ ሌለ ምስክርነት እየተሰማ ስለነበረ የእነተስፋለምን ምስክርነት ማድመጥ አልቻልንም፡፡ ለከሰዓት በኃላ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials