Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, March 5, 2015

ፈገግ ሚያሰኘው ዜና

ፈገግ ሚያሰኘው ዜና
የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 

የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች እና መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተደረገው የምስጋና ሲመፖዝየም በከተማዋ ከሚገኙ ክፍለ ከተማዎች የተመረጡ የገዢው ፓርቲ አባላትና አቀንቃኞች እንዲሁም ከየመምርያው የተወከሉ አባላት በተገኙበት መከላከያ ሰራዊቱ ለሃገሪቱ ዘብ የቆመ፣ በልማቱ ተሳታፊና ሁለንተናዊነቱን በማንሳት መወድሰ- መከላከያ ሰራዊት ሲደረግ ውሎአል።
በዚህ የሰራዊቱን አመራሮች የማድነቅ ስነስርዓት ላይ ንግግራቸው በጭብጨባ እንዲታጀብ እጠየቁ ተሰብሳቢውን ሲያነቃቁ የነበሩ አንድ ሴት በንግግራቸው መካከል ነገር አሳመርኩ ብለው ያልተጠበቀ ነገር ተናገሩ።
እኝህ እናት ከፊት ለፊት የተደረደሩትን ባለስልጣናት በመመልከት “ዛሬ ያለው ውጊያ ከድህነት ጋር ነው፣ሀገራችን ከበለጸጉ ሀገሮች ጋር እኩል ሆና ሀገራችንን እንደምናያት ርግጠኛ ነኝ፡፡” አሉ፣ ቀጡለና በዚህ ስርዓት የሴቶች መብት ተከብሯል ፣የመናገር መብት ተከብሯል፡፡
የነበረውን ስርዓት እናውቀዋለን ካሉ በሁዋላ የቀድሞውን ስርአት ወደ መግለጽ ገቡ፡፡
በቀድሞው ስርዓት ስኳር በግድ ውሰዱ ተብለን እንቀጣ ነበር ፣ አሁን ግን ብለው ሲናገሩ ባለስልጣናቱ ራሳቸው ሳቃቸውን መቆጣጠር ተሳናቸው። ነገር አሳመርኩ ያሉት ተናጋሪም በድንጋጤ ነገሩን ለማድበስበስ ሲሞክሩ ተሰብሳቢውን የበለጠ አሳቁት ፡፡


No comments:

Post a Comment

wanted officials