Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, March 27, 2015

ድምጻችን ይሰማ የጠራው የሳንቲም መሰብሰብ ተቃውሞ ተጀመረ

ድምጻችን ይሰማ የጠራው የሳንቲም መሰብሰብ ተቃውሞ ተጀመረ
መጋቢት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ወደ ማእቀብ እና ትብብር የመንፈግ ሂደት መሸጋገሩን ድምጻችን ይሰማ ካስታወቀ በሁዋላ፣ አርብ መጋቢት 20 የሳንቲም መሰብሰቡ ሂደት ተጀምሯል።
ምን ያክል ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጥሪውን ተቀብለው ተግባራዊ እያደረጉት መሆኑን ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም ሙስሊሙ ከዚህ በፊት ይተላለፉ የነበሩ የድምጻችን ይሰማን መመሪያዎች ሲተገብር በመቆየቱ፣ አዲሱን መመሪያም ተግባራዊ ያደርጋል ተብሎ
እንደሚታሰብ ዘጋቢያችን ገልጿል። የሳንቲም መሰብሰቡ ተቃውሞ በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳድረው የጎላ ተጽአኖ ባይኖርም፣ መንግስት ሳንቲሞችን ለማስቀረጽ ወጪ እንደሚያስወጣው፣ እንዲሁም በገንዘብ ልውውጡ ስርአት ላይ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል
የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ከሁሉም በላይ የአሁኑ ውሳኔ በቀጣይነት ለሚኖሩ ጠንከር ያሉ ተቃውሞች መነሻ እንደሚሆንና ህብረተሰቡ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ፊት ለፊት ሰይጋፈጥ በመንግስት ላይ ተጸእኖ ለማሳደር የሚያስችለውን ልምድ እንዲቀስም እንደሚያግዘው ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
ሳንቲም ቆጥቦ የመሰብሰብ ተቃውሞ የሚካሄደው በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች እና ከተሞች ነው።
ተቃውሞው በድምጻችን ይሰማ እስከሚገለጽ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቀጥል ሲሆን፣ ለወደፊቱ አንድ ብርና ከዛም በላይ ያሉ የብር ኖቶችን ከመሰብሰብ ጀምሮ ሌሎች በአተገባበራቸውም ሆነ በእንድምታቸውጠንክረው እያደጉ የሚሄዱ የትብብር መንፈግ እና የቦይኮት
ስልቶችን ቀስ በቀስ በመለማመድ ሰላማዊ ትግሉን እንደሚቀጥል ድምጻችን ይሰማ መግለጹ ይታወሳል።
Like · Comment · 

No comments:

Post a Comment

wanted officials