Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, March 23, 2015

የሕወሓት መንግስት በኤርትራ ላይ የአየር ጥቃት ፈጸምኩ የሚለው ቅዠት ነው ተባለ

የሕወሓት መንግስት በኤርትራ ላይ የአየር ጥቃት ፈጸምኩ የሚለው ቅዠት ነው ተባለ * “እንኳን የአየር ድብደባ ይቅርና ሞቅ ያለ ጭብጨባም አልተሰማም”

(ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት መንግስት በኤርትራ በማይ እዳጋ የሚገኘው የሚሻዕ ወርቅ ማዕድን ካምፓኒ ላይ የአየር ጥቃት አደረስኩ ብሎ ከገለጸ በኋላ የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ምንም አይነት ጥቃት እንደደረሰበት የገለጸው ነገር አልነበረም:: አስመራ የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ በማይ እደጋ እንኳን የአየር ድብደባ ይቅርና ሞቅ ያለ ጭብጨባም አልተሰማም::
Vandalism
በኤርትራ ይህን የወርቅ ማዕድን የሚያወጣው የካናዳው የማዕድን አውጪ ድርጅት (NEVSUN RESOURCES LTD) ማምሻውን በድረገጹ (www.nevsun.com) ባወጣው መግለጫ የአየር ጥቃት እንደደረሰበት አልገለጸም:: ድርጅቱ ማርች 13 ቀን 2015 ልክ በማንኛውም መስሪያ ቤት እንደሚደርስ አደጋ መጠነኛ መሰባበር የደረሰበት ቢሆንም ጥገና አድርጎ ወደ ስራ እንደሚመለስ ገልጿል:: ይህ ጉዳት የደረሰበት የሕወሓት መንግስት እንደሚለው በአየር ጥቃት እንደሆነ ካምፓኒው ያስቀመጠው ነገር የለም::
የሕወሃት መንግስት ለምን ይህ ዜናን ማሰማት ፈለገ? የሚለውን ዘ-ሐበሻ ወደ አስመራ ምንጮቿ ጋር ደውላ የነበረ ሲሆን ምንጮቹም “የሕወሓት መንግስት ይህን ዜና ማሰራጨት የፈለገው ከፍራቻ የተነሳ ነው:: በዚህ በሚሻዕ የወርቅ ማዕድን ማውጫ በማንኛውም ድርጅት ውስጥ እንደሚፈጠር መጠነኛ የማሽኖች መሰባበር አደጋ መፈጠሩን የወያኔ ደህነንቶች መረጃ አላቸው:: የዚህ ድርጅት አካባቢ ደግሞ የኢትዮጵያ ነፃነት ታጋዮች የሚገኙበት ወታደራዊ ካምፖች አሉ:: አደጋው ከደረሰ ከአንድ ሳምንት በኋላ የሕወሓት መንግስት በኤርትራ ላይ የአየር ጥቃት እንደፈጸመ ማውራቱ ከገባበት ውጥረት የሕዝቡን አመለካከት ለመቀየር ነው” ብለዋል::
በተለይም በጎንደር አካባቢ በሕወሓት ወታደሮች እና በጎንደር ሕዝብ መካከል በተፈጠረው ውጥረት በዛሬው ዕለት 4 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎና ሰሞኑንም ሕዝቡ ጠመንጃ እየያዘ ጫካ እየገባ በመሆኑ ይህን ለማስቀየስ የሕወሓት መንግስት የቀየሰው የፕሮፓጋንዳ ስልት ነው ሲሉ እነዚሁ ወታደራዊ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::
source: Zehabesha

No comments:

Post a Comment

wanted officials