አየር ሐይልን ከድቶ በይፋ ግንቦት 7ን የተቀላቀለው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ታናሽ ወንድም ሠይፈ መዘነ በማዕከላዊ ቶርች እየተደረገ መሆኑ ታወቀ
"ተዋጊ አውሮፕላኖች የኮንትሮባንድ ማመላለሻ ሆነዋል" በማለት የኢትዮጵያ አየር ሃይልን እና የገዢውን ፓርቲ አካሄድ በመቃወም ግንቦት 7ን መቀላቀላቸው የሚታወሠው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ቤተሠቦች አደጋ ላይ ይገኛሉ፡፡
ኮተቤ 02 አካባቢ በተለምዶ ቆርቆሮ ሠፈር እየተባለ በሚጠራው ስፍራ የሚኖሩት የሻለቃ አክሊሉ ቤተሠቦች ሻለቃ አክሊሉ በተለያዩ ምክንያቶች ግንቦት 7ን መቀላቀላቸውን ተከትሎ በቤተሠቡ ላይ የሚካሄደው ምርመራ እና ክትትል በገዢው ፓርቲ የደህንነት ሀይሎች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በተለይም በታናሽ ወንድሙ ሠይፈ መዘነ በማዕከላዊ ቶርች እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጧል፡፡
ይህንን ዜና በኢሜይል የላከልኝ ወጣት እንደገለፀው ከሆነ ወጣት ሠይፈ መዘነ ማዕከላዊ እንደሚገኝ ያወቁት ቤተሠቦቹ ወደስፍራው በማቅናት ለመጠየቅ ቢሞክሩም በፖሊሶች መከልከላቸውንና ቤተሠቦቹም እስረኛን መጠየቅ መብታቸው መሆኑን ሲገልፁ ፖሊሶች ሠይፈ አዘነ እስረኛ ሣይሆን አሸባሪ ነው በማለት መልሠዋቸዋል፡፡
ሻለቃ አክሊሉ አዘነ ሴፕቴምበር 2013 ኢሳት ላይ ቀርቦ አየር ሐይል እንደገና ካልተዋቀረ አገርን መከላከል የሚችልበት ደረጃ እንደማይገኝ የገለፁ ሲሆን በተጨማሪም ተዋጊ አውሮፕላኖች የኮንትሮባንድ ማመላለሻ ሆነው እንደሚአገለግሉ፣ አብራሪ የሚባሉት በሚሊሻ ደረጃ መገኘታቸው፣ የዘር መድልዎ እንደሚደረግ፣ የህወሃት ድጋፍ ያላቸው ብቻ የሚስተናገዱበት መሆኑ፣ ከችግሮቹ በግንባር የሚገለጹ ናቸው ሲሉ መግለፃቸው ይታወሳል።
ሻለቃ አክሊሉ ላለፉት 15 ዓመታት ያህል በታማኝነት የኢትዮጵያ ህዝብን ያገለገሉ ሲሆን በአየር ሃይል ውስጥ የሚሰራው የቡድን፣ የዘርና አጠቃላኢ አለው አሰራር ብልሹነት አሳሳቢ በመሆኑ አገር ጥለው በመውጣት ከሶስት ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ግንቦት7 ንቅናቄን መቀላቀላቸውን በወቅቱ ገልፀው ነበር።

No comments:
Post a Comment