Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, March 11, 2015

ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ድብደባ ተፈጸመባቸው

ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ድብደባ ተፈጸመባቸው

መጋቢት ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ ዛሬ ከቀትር በሁዋላ ማንነቱን በማያውቁት ሰው ድብደባ ተፈጸመባቸው።
ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ወደ ፍርድ ቤት እየሄዱ ሳሉ ሜክሲኮ አካባቢ ብሔራዊ አረቄ ፋብሪካ መታጠፊያ ላይ አንድ  እብድ የሚመስል ሰው  ተንደርድሮ ዐይናቸውን በቡጢ  ክፉኛ መቷቸዋል።
ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ጠበቃ ሆነው ለረዥም ጊዜ በመከራከራቸው በስርዓቱ  ሰዎች ዛቻና ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው መቆየቱ ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials