Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, March 14, 2015

ከአማራ ድሞክራሳዊ ሃይል ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ ንቅናቂያችን የሚገነጥሉትንም ሆነ መገንጠልን አጥብቆ ይቃወማል::

ከአማራ ድሞክራሳዊ ሃይል ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ
ንቅናቂያችን የሚገነጥሉትንም ሆነ መገንጠልን አጥብቆ
ይቃወማል::
ከሰሞኑ በአልተለመደ ሁኔታ የፋሽስት ወያኔ ቡድን በአማራዉ ላይ
የሚያደርሰዉን ሰቆቃ በመጥቀስ ስለ አማራዉ መገንጠል
በተወሰኑ ግለሰቦች በአጀንዳነት ተይዞ ወደ ማህበራዊ ሚድያ
ቀርቧል::
በመሆኑም ይህን ጉዳይ የሰሙ ወገኖች ለንቅናቂያችን ስለ
መንገጠል በተለያየ መንገድ ጥያቄቸዉን አድርሰዉናል::አሁን
አማራዉ በየትኛዉም የኢትዮጵያ ቦታ ግፍ እና ስቃይ እየደረሰበት
በሕይወት የመኖር ሕልዉናዉ ፈጥሞ አደጋ ዉስጥ እንደሚገኝ
ለኢትዮጵያዊን ቀርቶ ለአለም ሕብረተሰብ ግልፅ ነዉ::
ከዚህ መከራ ለመገላገል መገንጠል እንደሆነ መፍትሄዉ
በማህበራዊ ሚድያ አማካኝነት የቀረበዉን ሃሳብ በንቅናቂያን
ፍፁም ተቀባይነት እንደሌለዉ አጥብቀን ማስገንዘብ እንወዳለን::
አማራዉ የትኛዉንም ፀረ አማራ ቡድን ለመታገል በአማራነቱ
መደራጀት እንዳለበት ቁርጠኛ አቋም በመዉሰድ ንቅናቂያችን
ተደራጅቶል::
ንቅናቂያችንም ከተመሰረተ ጀምሮ የሕዝባችንን ሕልዉና
ለማረጋገጥ መራራ መስዋትነት ከፍሎል:: በመክፈል ላይም
ይገኛል::
የሕዝባችን ትግል እንደሚያሸንፍ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነን::
በአሁኑ ወቅት ለአማራዉ በቀዳሚነት እና በቁርጠኝነት በየበረሃዉ
የሚዋደቀዉ ንቅናቄአችን መገንጠልን አጥብቆ
ይቃወማል::ያወግዛል!
ወደ አንድ ጥግ በመጓዝ መገንጠል የሚል ሃሳብ ይዞ ማቀንቀን
ለምናደርገዉ የነፃነት ትግል ቅንጣት ታክል ፋይዳ እንደለለዉ
ማስገንዘብ እንወዳለን::
አማራዉ ከጥንት ጀምሮ ደም እና አጥንቱን በመከስከስ ከሌሎች
ወንድሞቹ ጋር በመሆን የሕይወት መስዋትነት በመክፈል
ኢትዮጵያ
እንደ ሐገር እንድትቆም እና እንድትቀጥል ያልከፈለዉ አንዳችም
መስዋትነት የለም::
ንቅናቄያችንም ዛሬም ነገም ይሑን መስዋትነትን በቁርጠኝነት
በመክፈል ሕዝባችንን ከመጥፋት በመታደግ ኢትዮጵያ እንደ ሐገር
በነፃነት እንድትቀጥል ያደርጋል::
የትኛውንም አይነት መከራ ና ስቃይ ቢደራረብም ለድል
ንቅናቂያችን ለነፃነት ሌትተቀን በቆራጥነት በመታገል ላይ
ይገኛል::
በየትኛዉም መስፈርት ተቀባይነት የሌለዉን በወያኔ ቡድን
ተዘጋጅቶ የአማራዉ ክልል ተብሎ የተሰየመዉን ቦታ ለስም ያህል
በማሻሻል ግፍ እናን በመጥቀስ በገንጠል ተፈጣሚነት ተቀባይነት
እንደለለዉ በግልፅ እየታወቀ ተቆርቆሪ መስሎ ይህን ሃሳብ
ማራመድ ወያኔ ለሚያደርገዉ የዘር ማጥፋት ወንጀል ዱላ
ማቀበል
በሆኑን ማንም ኢትዮጵያዊ ሊገነዘበዉ ይገባል::
ንቅናቂያችን በኢትዮጵያ አንድነት የፀና አቋም እንዳለዉ የሚሻማ
ጉዳይ ሆኖ አያዉቅም:: ይሁን እንጅ ንቅናቄችን በአማራነቱ
መደራጀቱን ብቻ እንደ ምክንያት በመዉሰድ የመገንጠል ሃሳብ
ሊያራምድ ይችላል ብሎ መናገር በራሱ የንቅናቄያችንን አላማ
በተገቢዉ መንገድ ከአለመረዳት የመነጨ ይሆናል ብሎ በቀናነት
ለመረዳት ይከብዳል::
አሁን በታሰብ እና መተግበር ያለበት የሕዝባችንን ህልዉና
ጨርሰዉ ለማጥፋት ከሚዳክሩት ከወያኔ ነፃ ማዉጣት ነዉ::
ይሕን ደግሞ ንቅናቄአችን በአስደናቂ መልኩ እየተገበረዉ
ይገኛል::
በመሆኑም በየትኛዉም የአለማችን ክፍል የምትገኙ
ኢትዮጵያዊያን በአማራዉ ላይ በተለየ ሁኔታ የዘር ማጥፋት እና
ጨርሶ ህልዉናዉን ለማስወገድ የሚደረገዉን እኩይ የወያኔ
ተግባር በመቃወም በማዉገዝ ንቅናቄችንን በመቀላቀል በመደገፍ
ሕዝባችንን እንድታደገዉ ጥሪያችንን እናቀርባለን ::
የአማራ ሕዝብ ትግል ያሸንፋል!
3/7/2007

No comments:

Post a Comment

wanted officials