Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, March 31, 2015

በጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ የሚሰሙት የደረጃ ምስክሮች ዛሬም ቀጥለዋል::



በጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ የሚሰሙት የደረጃ ምስክሮች ዛሬም ቀጥለዋል::
 የሁለተኛ ቀን የአቃቢ ሕግ የሃሰት ምስክሮች በዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ እየተሰማ ሲሆን ጎን ለጎን በሃሰት ተወንጅለው በእስር የቆዩ ሶስት ሙስሊም ወገኖቻችን እንዲፈቱ ሲወሰን የነ ኤሊያስ መዝገብ ለግንቦት 17 ተቀጥሯል::ሼኽ አብዱራህማን ኡስማ ያለበቂ ምክንያት ከረጅም ጊዜ የእስር ቆይታ በኋል በነፃ እንዲሰናበቱ ፍርድ በቱ አዟል።ሞባይል ስልኮችን ወደ ችሎት ይዞ መግባት ተከልክሏል::


"እኛ ብቻችንን አይደለም የታሰርነው። ቤተሰቦቻችን እና ጓደኞቻችን አብረውን ታስረዋል። ክቡር ፍርድ ቤቱ ይህንን ከግምት ዉስጥ እንዲያስገባልን እንጠይቃለን" ናትናኤል ፈለቀ - በዛሬዉም እለት ጠዋት የቀረቡ ምስክሮች እንዲሁ ሲደናበሩ የተስተዋሉ ሲሆን ማን ላይ ልትመሰክር መጣህ የተባለው በፍቃዱ ሃይሉ ከማለት ይልቅ ፍቃዱ ታምሩ ሲል ተደምቷል::ይህን ያህል; እየዘባረቁ ምስክርነት መስጠቱ አላስፈላጊ መሆኑንና በሚታወቅ ጉዳይ ላይ ጊዜን በሃሰት ምስክር መግደል የገረማቸው የተከሳሾች ጠበቆች አስረድተው የደረጃ ምስክርነቱ እንዲቆም ጠይቀዋል::

አገርን በሽብር ሊፈጁ ሲሉ፣እጅ ከፍንጅ ያዝኩዋቸው"ሲል የነበረው ከሳሽ ያቀረባቸው 14 የሃሰት ምስክሮች በሁለት ቀናት፣2ሰአት በጠቅላላው በማይሞላ ችሎት አሰምቶ ጨርሶዋል::...... እሰካሁን በቀረቡት ምስክሮች መሰረት ቂሊንጦ መላክ ያለባቸው ከሳሾቹ ናቸው::ደሞ አያፍሩም ተጨማሪ ጊዜ ይጠይቃሉ!ሲሉ ችሎቱን የታደሙ ተናግረዋል ከሰዓት በኃላ የተሰየመው ችሎት ያልቀረቡ ምስክሮችን እና ሌሎች ተጨማሪ የሰው ምስክሮችን ለመስማት ለመጋቢት 30/2007 ቀጠሮ በመስጠት ተጠናቋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials