Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, March 19, 2015

ኤልፓና መከላከያ በባቡር የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የተነሳ እየተወዛገቡ ነው

ኤልፓና መከላከያ በባቡር የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የተነሳ እየተወዛገቡ ነው

መጋቢት (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚሰራው የቀላል የባቡር መንገድ የኤሌክትሪክ ሃይል መስመር ዝርጋታ ርክክብን በተመለከተ በኢትዮጵያ መብራት ሃይል ኮርፖሬሽንና እና በመከላከያ ኢንጂነሪንግ የስራ አስፈፃሚ አመራሮች መካከል ከፍተኛ ውዝግብ መነሳቱን የውስጥ ምንጮች አመለከቱ፡፡Image result for ethiopian train accident
በመጀመሪያ መንግስት ለባቡሩ የሚያስፈልገውን  የኤሌክትሪክ አቅርቦት ግንባታ ለማስጀመር ከአንድ የግብጽ ኩባንያ ጋር ለመዋዋል በእንቅስቃሴ የነበረ ቢሆንም፣  ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ደብረ ጺዮን ገ/ሚካኤል እንቅስቃሴው እንዲቋረጥ  ቀጥተኛ ትዕዛዝ በመስጠት፣ ስራው ያለምንም ጨረታ በጄል ክንፈ ደኘው ለሚመራው ለመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን እንዲሰጥ አድርገዋል፡፡
መከላከያ ኢንጂነሪንግ ሥራውን አጠናቆ ለኤልፓና ለምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለማስረከ በእንቅስቃሴ ላይ የነበረ ቢሆንም፣ ኤልፓ  የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታው ከሚጠበቀው ጥራት ደረጃ ወይም ከፍላጎት መገለጫ በታች በመሆኑ አልቀበልም ብሎአል፡፡
በምድር ውስጥ ከሚቀበረው የኤሌክትሪክ መስመር ገመድ ውፍረት፣  ገመዱ የምድር ሙቀት መሸከም ከመቻልና ካለመቻል እንዲሁም ገመዱ የሚቀበርበት የጥልቀት መጠን ጋር በተያያዘ መከላከያ ኢንጅነሪንግ ሰርቶ ያቀረበው የጥራት ችግር እንዳለበት  የኮርፖሬሽኑ  ስራ አስፈፃሚና የባለሙያዎች ቡድን ማረጋገጫ ሰጥቷል።
የመብራት ሃይል ድርጊት ያበሳጫቸው ዶ/ር ደብረጺዮን  ወደ ስራ አስኪያጁዋ ኢ/ር አዜብ አስናቀ  ስልክ በመደወል “ባለሙያዎችሽ የጥራት ችግር እንዳለበት የሚያወሩት ምን አውቀው ነው? ምን አገባቸው?” በማለት አስፈራርተው ርክክብ እንዲደረግ ለማድረግ ቢሞክሩም ፣ የኤልፓ ከፍተኛ ባለሙያዎችና ስራ አስኪያጆች “በሰው ህይወት ላይ አንቀልድም ከተባረርንም እንባረር እንጂ ርክክብ አንፈጽምም” በማለታቸው ውዝግቡ እልባት ሳይገኝ በእንጥልጥል ላይ እንደሚገኝ የውስጥ ምንጮች ተናግረዋል።
የመከላከያ ኢንጂሪንግ ኮርፖሬሽን አስተዳደር የተለያዩ ፋብሪካዎች ከመከላከያ በተውጣጡ በአንድ አካባቢ ሰዎች የተያዘ ነው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials