አቶ በቀለ ገርባ የ እስር ጊዜያቸውን ጨርሰው መፈታታቸው ተሰማ:: የደረሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አቶ በቀለ ዛሬ ተፈተው እቤታቸው ከገቡ በኋላም እንደገና ደህንነቶች “ያልተጣራ ነገር” አለ ብለው እንደገና ወስደው ለሰዓታት ካሰሯቸው በኋላ መልሰው ሞጆ ላይ ለቀዋቸዋል::
አቶ በቀለ ገርባ 26 ዓመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ልሳን መምህር የነበረሱ ሲሆን የሰውነት አቋማቸው ግን ገና 26 ዓመታትን የሚሰሩ ያስመስላቸዋል።
የኢሳት ራድዮ ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ “የአቶ በቀለ አፈታት ድራማ” በሚል በዘገበው ዘገባው ላይ የሚከተለውን ጽፏል::
*ዛሬ መጋቢት 21 2007 ዓም አቶ በቀለ የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው የሚፈቱበት ቀን ነው።
*ጠዋት ላይ ባለቤታቸው ወይዘሮ ሀናን ጨምሮ የአቶ በቀለ መፈታትን ለማየት ወደ ዝዋይ እስር ቤት አቀኑ
*አቶ በቀለ ተፈቱ:: ቤተሰባቸውን በእቅፋቸው አድርገው በደስታ እንባ ታጅበው መነፋፈቃቸውን ገለጹ። ከዚያ ጉዞ ወደ ቤት…
*በድንገት የህወሓት ፖሊሶች ወደ አቶ በቀለ መጡና “መጣራት ያለበት ጉዳይ ስላለ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ይወሰዳሉ” አሉ:: ቤተሰብም አቶ በቀለም ቀልባቸው ተገፈፈ:: ደስታቸው ብን ብሎ ጠፋ!
*በደንጋጤ የተዋጡት ወይዘሮ ሀና ይህንን ጉዳይ ለኦፌኮ አመራሮች አሳወቁ። የኦፌኮ አመራሮች በፍጥነት አቶ በቀለ ይሄዳሉ ወደተባሉበት ቃሊቲ እስር ቤት ተጓዙ።
*ሆኖም ቢጠበቅ-ቢጠበቅ አቶ በቀለ ብቅ ሳይሉ ቀሩ
*አቶ በቀለን ይዘው የነበሩት ጠባቂዎች ታሳሪውን ይዘው ሞጆ አካባቢ ለቀቋቸው።
ውዥንብሩ ለምን እንደተፈጠረ ባይታወቅም ዋናው ደስታው ነውናን ቤተሰባቸው አቶ በቀለ ገርባን ይዞ ወደ አዳማ ናዝሬት ይዞ ሄደ። አቶ በቀለና ሴት ልጃቸ ቦንቱን ኢሳት በስልክ አግኝቶ አነጋግሯቸዋል::
በካንጋሮው የሕወሓት ፍርድ ቤት “በሽብርተኝነት” ክስ ጥፋተኛ ተብለው 3 ዓመት ከ7 ወር የተፈረደባቸው አቶ በቀለ በመጀመሪያ ስምንት ዓመት ቢፈረድባቸውም ተከራክረው ወደ 5 ዓመት ማስደረጋቸው ይታወቃል:: በየኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የ3 ዓመት ከ7 ወር የእስር ጊዜያቸውን እንደጨረሱ በኣመክሮ መለቀቅ የነበረባቸው ቢሆንም መከልከላቸው ይታወሳል:: እስር ቤትም ህክምናም ሳያገኙ ብዙ ተሰቃይተዋል:: አቶ በቀለ ገርባ የ 3 ዓመት ከ 7 ወር የእስር ጊዜያቸውን ኣጠናቀው መለቀቅ የነበረባቸው ባለፈው ጥር 11 ቀን ነበር::
No comments:
Post a Comment