Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, June 30, 2016

Allow Ethiopian opposition politician to obtain treatment abroad for torture-sustained injuries

Allow Ethiopian opposition politician to obtain treatment abroad for torture-sustained injuries

The Ethiopian authorities must allow an opposition politician who is now unconscious due to injuries sustained in torture and other ill-treatment to obtain life-saving medical treatment abroad, said Amnesty International in a letter to Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn.
Habtamu Ayalew, the former spokesman for the opposition Andenet (Unity) party was arrested on July 8, 2014 and charged with terrorism for allegedly collaborating with the opposition Ginbot 7, which the Ethiopian government has designated a terrorist group. He was detained at the notorious Maekelawi and Qilinto Prisons, where he was subjected to torture and other ill treatment through denial of access to toilet facilities, a situation that led to him to develop excruciatingly painful hemorrhoids.
“Habtamu has been prevented from leaving the country because the prosecutor has appealed the High Court’s decision that released him from prison. The appeal is currently pending before the Supreme Court,” said Haben Fecadu, Amnesty International’s Campaigner for the Horn of Africa.
“He must be urgently let out of the country on humanitarian grounds, if for nothing else, if his life is to be saved.”
Although easily treatable in the early stages, Ayalew’s hemorrhoids were left to deteriorate to Stage-3 which requires surgery, after his jailers repeatedly denied him access to medical treatment.
“The authorities should promptly and impartially investigate the detention conditions that caused Habtamu’s health to deteriorate so much. They must also prosecute anyone reasonably suspected of personal responsibility for this and related offences, including torture or other acts of ill-treatment, in fair trials,” said Fecadu.
Although the High Court acquitted Habtamu and other defendants of the terrorism Charges on September 20, 2015, he was not released until five months later, by which time his condition had deteriorated further.


አንዳንድ የኤርትራ መሪዎች እንዲጠየቁ ጅቡቲና ሶማሊያ አሳሰቡ






ጅቡቲና ሶማሊያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በኤርትራ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ ተጠያቂነት እንዲኖር የውሣኔ ሀሳብ አቀረቡ።


ዋሽንግተን —

ጅቡቲና ሶማሊያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በኤርትራ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ ተጠያቂነት እንዲኖር የውሣኔ ሀሳብ አቀረቡ።
ሁለቱ የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች የዓለሙ ድርጅት በኤርትራ ላይ ያሠማራው የመብቶች አያያዝ አጣሪ ቡድን ያቀረበውን ሪፖርት አወድሷል፡፡
አንዳንድ የኤርትራ መሪዎች በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ወይንም በሌሎች የፍትህ ችሎቶች ክሥ እንዲመሠረትባቸው ያቀረበው ምክር በውሳኔ እንዲደገፍ የሃገሮቹ ሃሣብ መክሯል፡፡

የቁም እስረኛው የኣቶ ሃብታሙ ኣያሌው ጤና የመጨረሻው ኣሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

የቁም እስረኛው አቶ ሃብታሙ ኣያሌው ጤና የመጨረሻው ኣሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ከሃገር ውጪ እንዳይታከም በ አቶ ጸጋዬ በርሄ የወያኔ ደህንነት ኣማካሪ ባለስልጣን በኩል የጠጣለው እገዳ አልተነሳለትም፤ በኣሁን ወቅት በኮማ ውስጥ ይገኛል።
ወጣት ሀብታሙ አያሌው ህይወቱ አደጋ ላይ ነው ወጣት ፓለቲከኛ ሀብታሙ አያሌው በአሁኑ ሰአት በጠና ታሞ ሀኪም ቤት መግባቱን በአቅራቢያ ባሉ ሰዋች ሰምቻለሁ በዚህ ሰአት ሀኪም ቤት ይገኛል ሁላችንም ፀሎት ልናረግ ይገባል ህክምናውን በሀገር ውስጥ ማድረግ ባይቻል መንግስትን ከሀገር ውጪ ለመታከም ቢጠይቅም መንግስት ግን የቁም እስረኛ በማረግ ይሄን ወጣት ለከፍተኛ ህመም ዳርጎታል በዚህ ሰአት የሀብታሙ አያሌው ህይወት አደጋ ላይ ነው በጠና ታሞል ጀግኖችን መጠበቅ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሀላፌነት ነው

Wednesday, June 29, 2016

አቶ ሀብታሙ አያሌው በአስቸኳይ የውጭ ሀገር ህክምና እንዲያገኙ ሰማያዊ ፓርቲ ለጠቅላይ ሚንሲትሩ አሳሰበ



አቶ ሀብታሙ አያሌው በአስቸኳይ የውጭ ሀገር ህክምና እንዲያገኙ ሰማያዊ ፓርቲ ለጠቅላይ ሚንሲትሩ አሳሰበ!!! በግለሰቡ ሕይወት ላይ ለሚደረስው አደጋ መንግሥት ኃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን ጭምር ፓርቲው አክሎ ገልጾአል ።
-----------
መንግስት የዜጎችን ደህንነትና ጤንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት ቢሆንም በሀገራችን በሕግ ከለላ ስር ያሉ ዜጎች ተገቢውን ሕክምና ባለማግኘታቸው ሕይወታቸው አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ በእስር ቤት እያሉ ተገቢውን ሕክምና ማግኘት ባለመቻላቸው ለሞት የተዳረጉ እንዳሉ የሚታወቅ ነው፡፡
አቶ ሀብታሙ አያሌው በተለምዶ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በመባል በሚታወቀው ተቋም በምርመራ ወቅት በደረሰባቸው ህመም ሕክምናውን በሀገር ውስጥ ባሉ የጤና ተቋማት መታከም እንደማይችሉና ወደውጭ ሀገር ሄዶ ህክምና ማግኘት እንዳለባቸው የተገለፀ ቢሆንም ከሀገር እንዳይወጡ በፍ/ቤት ታግደዋል፡፡
በመሆኑም አቶ ሀብታሙ አያሌው በፍ/ቤት የተጣለባቸው ዕግድ ተነስቶ ወደ ውጭ ሀገር ሂደው እንዲታከሙ አስፈላጊው ሁሉ እንዲደረግ እየጠየቅን ይህ ባይሆንና ህክምና ባለማግኘቱ በግለሰቡ ሕይወት ላይ ለሚደረስው አደጋ መንግሥት ኃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን እናሳስባለን።
ግልባጭ፣
፨ ለኢፊዲሪ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት
፨ለሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ለፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ

Tuesday, June 28, 2016

በላፍቶ ልዩ ስሙ ቀርሳ ኮቱማ በሚባለዉ አካባቢ በፖሊስና በነዋሪዎች መካከል በተነሳዉ ግጭት 17 ፖሊሶች መሞታቸዉን ነዋሪዎቹ ገለጹ።



በላፍቶ ልዩ ስሙ ቀርሳ ኮቱማ በሚባለዉ አካባቢ በፖሊስና በነዋሪዎች መካከል በተነሳዉ ግጭት 17 ፖሊሶች መሞታቸዉን ነዋሪዎቹ ገለጹ።
በአዲስ አበባ አካባቢ በላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ቀርሳ ኮቱማ በሚባለዉ አካባቢ በፖሊስና በነዋሪዎች መካከል በተነሳዉ ግጭት 17 ፖሊሶች መሞታቸዉን ነዋሪዎቹ ለቢቢኤን ገለጹ። በፖሊሶችና የቀበሌ አመራሮች በ አካባቢዉ ያሉትን ቤቶች ለማፍረስ የመብራት ቆጣሪዎችን ለመንቀል ሲሞክሩ በተነሳዉ ግጭት ነዋሪዎቹ የፖሊሶቹን መሳሪያ በመቀማት፣በዱላና በድንጋይ በተከፈተ ጥቃት ነዉ ፖሊሶቹ የሞቱት።
ግጭቱን ተከትሎ የጦር መሳሪያን የታጠቁ የፌዴራል ፖሊሶች ወደ አካባቢዉ በመግባት ነዋሪዉን እየደበደቡ በጭነት መኪና እያፈሱ ወዳልታወቀ ቦታ እየወሰዱ መሆኑን ቢቢኤን ለማወቅ ችሏል። ህጻናትና እናቶች ያለቤት አባወራ ሜዳ ላይ እንደተጣሉና ለአደጋ እንደተጋለጹ ነዋሪዎቹ ያስረዳሉ።ጿሚዎች ማፍጠሪያ ምግብና ቦታ እንደሌላቸዉ ገልጸዋል። እራሳቸዉን ከፌዴራል ፖሊስ ጥቃት ለማዳን የሚሸሹ የቤት አባወራዎች በየጫካዉ ዉስጥ መቀመጣቸዉን፣ ምንገዶች ሁሉ መዘጋታቸዉን ነዋሪዎቹ ለቢቢኤን ገልጸዋል።ከነዋሪዎቹ ለመረዳት እንደተቻለዉ ቢያንስ አንድ የቀበሌ አመራር ሞቷል።









Monday, June 27, 2016

በሻሸመኔ ወንጀለኞች ታስረዋል ቢባልም ወንጀሉ ግን እንደቀጠለ ነው። By Minilik Salsawi

በሻሸመኔ ወንጀለኞች ታስረዋል ቢባልም ወንጀሉ ግን እንደቀጠለ ነው። By Minilik Salsawi


ባለፈው ሳምንት በሻሸመኔ ከተማ ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ወንጀለኞች ተብለው የተያዙ ሰዎች ካለምንም ምርመራ ከ23 ኣመት እስከ እድሜ ልክ ድረስ የተፈረደባቸው ቢሆንም ኣሁንም ወንጀሎች መቀጠላቸውን የከተማው ነዋሪዎች እየተናገሩ ይገኛሉ።እነዚህ ግለሰቦች ታስረው ከተያዙ እንኳን በፊት በተፈፀመው መልኩ ሌሎች ሁለት ግለሰቦች በከተማዋ ተወግተዋል።
ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብለው ስማቸው የተዘረዘሩትና ተይዘው የታሰሩት ግለሰቦች በከተማዋ በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው እራሳቸውን የሚያስተዳድሩ ድሆች ናቸው።
፩። ተስፋዬ በቀለ ወልደየስ ፡ በእድሜ ልክ እስራት
፪። እዮብ ዋዳ ዋለልዬ ፡ በእድሜ ልክ እስራት
፫ ጌታሁን ሙሉጌታ መንግሥቱ ፡ በእድሜ ልክ እስራት
፬ እሸቱ ታደስ ለማ ፡ በ23 ዓመት ጽኑ እስራት
፭። ጠንክር ጀሊላ ጎቶሮ ፡ በ23 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል።
እነዚህ ግለሰቦች ወንጀሉን ስለመፈፀማቸው ትክክለኛ የምርመራ ሂደት ሳይከናወን እስራት ተፈርዶባቸዋል። እውነትም እነዚህ ሰዎች ወንጀሉን ፈፅመውት ከሆነ ህዝቡ በግልፅ ሊያየው በሚችል መልኩ አግባብ ያለው ምርመራ ተደርጎባቸው፤ አስፈላጊው የሰውና የቴክኒክ ማስረጃ ቀርቦባቸው ለምን አልተፈረደባቸውም።
እንዚህ ግለሰቦች ታስረው ከተያዙ እንኳን በፊት በተፈፀመው መልኩ ሌሎች ሁለት ግለሰቦች በከተማዋ ተወግተዋል። ወያኔዎች በድራማዊ ቅንብራቸው ሊያታልሉን እንደሞከሩት የወንጀሉ ፈፃሚዎች ታስረው ፍርድ ከተሰጠባቸው ዳግም የሻሸመኔን ህዝብ እያደነ የሚገኘው አካል ማን ይሆን፧ በርግጥ ታስረው ከተፈረደባቸው መካከል በወንጀሉ ውስጥ ሚና ያላቸው ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን እነዚህ ግለሰቦች ታስረው ፍርድ ተሰቷቸዋል እየተባለ ወንጀሉ መቀጠሉ አሁንም ቢሆን የወንጀሉ ትክከለኛ ፈፃሚና አስፈፃሚ አካላት አዳዲስ ግለሰቦችን በማሰማራት በነፃነት ህዝቡን እያጠቁ መሆኑን ነው።

Saturday, June 25, 2016

ሶማሊያዊው የአትሌት ገንዘቤ ዲባባ አሰልጣኝ ታሰረ

 የአትሌት ገንዘቤ ዲባባ አሰልጣኝ ጃማ ኤደን ስፖርተኞች ከሚወስዱት አበረታች ዕጽ ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ ስፔን ውስጥ መታሰሩ ተሰማ::
ገንዘቤ ከወራት ወዲህ በኢዩጂን፡ በኦስሎና ስቶክሆልም የሩጫ ውድድሮች የነበሯት ሲሆን ባልታወቀ ሁኔታ በነዚህ ውድድሮች ሳትሳተፍ መቅረቷ አይዘነጋም::
የዓመቱ ምርጥ አትሌትነትን እና ሌሎች ሽልማቶችን የጠቀለለችው ገንዘቤ የወቅቱ የ1 ሺህ 500 ሜትር የዓለም ሻምፒዮና ስትሆን ሶማሊያዊ ዜግነት ያለው አሰልጣኟ በስፔን በካታሎኒያ አትሌቶችን ሰብሰበው በሚያሰለጥኑበት አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ መያዙን የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ዘግቧል;:
ከሶማሊያዊው አሰልጣኝ ጋር እነማን አትሌቶች እንደተነካኩ የተዘገበ ነገር የለም::

Israel Is a Racist Country: Take It From Me, an Ethiopian Israeli


Israel Is a Racist Country: Take It From Me, an Ethiopian Israeli







“Israel is one of the most racist countries in the world,” said Tahunia Rubel, an Ethiopian-born Israeli model and actress. The remarks by Rubel, who became famous on the Israeli version of “Big Brother,” were published in the mass-circulation daily Yedioth Ahronoth last weekend.

Rubel said things like “We have a screwed-up government … and the police are total idiots.” She added: “People in Israel find it strange to see an Ethiopian woman who behaves like an Israeli.” According to a report this week by the Berl Katznelson Foundation, the interview stirred particularly violent posts on social networks.

That leads me to conclude that I’ve spent 21 years in Israel, the total number of my years on earth, in a country totally different from the one where Israelis so angry at Rubel live. For a moment it was nice to wake up in a parallel universe where Israel and Israeli society aren’t racist, and where people get angry at people who claim they’re racist.

Of course it’s possible to refuse to acknowledge that the experience of a black woman in a white space isn’t identical to that of a white man in a white space, and to believe that he will never be able to understand my subjective feelings. But why talk about subjective feelings? The pain and anger are a product of institutional practices.

Israel commits racist crimes. A prominent example is the police violence during the demonstrations by young Ethiopian men and women a year ago. (Police violence, incidentally, isn’t limited to young Ethiopians; many young Arabs encounter it as well.) Another example is the investigation that revealed the pressure on Ethiopian women to receive shots of the birth control hormone Depo-Provera before immigrating.

In Israel, women of Ethiopian origin suffer oppression on two fronts: gender-related and race-related. The furious reactions to Rubel’s statement that Israel is a racist country only prove the justice of her claims. They refer to the fact that she’s a woman, an Ethiopian (“Go back to Ethiopia”) and a black person (“a disgusting African”).

As far as they’re concerned, a black woman in the white mainstream should always be pretty, quiet, polite and filled with gratitude for the right to be a part of the mainstream. If you don’t play along you’ll pay a high price.

The reactions are a perfect illustration of the difficulty facing minorities in Israel. They’re accepted into the mainstream only if they refrain from criticism.

So you belong to a minority and you want to express criticism? They’ll immediately remind you that you shouldn’t take for granted that you’re here and will suggest that you return to your country of origin. That’s if you’re Ethiopian, of course, because leftist Israel-haters are sent to Berlin regardless of their ethnicity.

Some people say that in other countries the situation is much worse, so we shouldn’t criticize Israel but only praise it because we’re better than the non-Jews. Well, I don’t think that’s love for one’s country. After all, anyone who loves the country must criticize it, put a mirror in front of it and take steps to change it. Formal equal rights aren’t enough. Equality must be seen on the ground. In life itself. Even on the Internet.
by Revital Iyov | HAARETZ

Thursday, June 23, 2016

የአውሮፓ ሕብረት የኤርትራን ጨምሮ የ19 ሃገራት አየር መንገዶች በአውሮፓ እንዳይበሩ አገደ



ሲሲቲቭ የተሰኘው የቴሌቭዥን ጣቢያ ዛሬ እንደዘገበው የአውሮፓ ሕብረት በ12 የአፍሪካ ሃገራት አየር መንገዶች ላይ በሕብረቱ የአየር ክልሎች እንዳይበሩ እገዳ አስተላለፈ::

ሕብረቱ ኤርትራን ጨምሮ በ12 ሃገራት ላይ እገዳውን ሲጥል ሃገራቱም

1ኛ . ቤኒን
2ኛ. ኮንጎ ሪፐብሊክ
3ኛ. ዴሞክራሲያ ሪፐብሊክ ኮንጎ
4ኛ. ጅቡቲ
5ኛ. ኢኳቶሪያል ጊኒ
6ኛ. ጋቦን
7ኛ. ላይቤሪያ
8ኛ. ሊቢያ
9ኛ. ሞዛምቢክ
10ኛ. ሴራሊዮን
11ኛ. ሱዳን ናቸው::

የአውሮፓ ሕብረት የ214 አየር መንገዶችን የደህንነት ደረጃ የመረመረ ሲሆን ከአፍሪካ 12 እንዲሁም ከሌሎች ዓለም ሃገራት 7 በጥቅሉ የ19 ሃገራትን አየር መንገዶች አግዷል::

ለረዥም ጊዜያት እገዳ ተጥሎበት የቆየው የዛምቢያና የማዳጋስካር አየር መንገዶች በአውሮፓ እንዲበሩ የተፈቀደ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት ሃገራት አየር መንገዶች ለመንገደኞች ደህንነት አስጊዎች ናቸው በሚል በክልሉ እንዳይበሩ መታገዱን ዘ-ሐበሻን ከሲሲቲቭ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል

ሻሸመኔ ሕዝቡ የመረረ ተቃውሞውን አደባባይ ወጥቶ እያሰማ ነው – “የምሽት ግድያው ይቁም!”

በሻሸመኔ ከተማ በየዕለቱ ወጣቶች ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ የመገኘታቸው ዜና ያንገሸገሸው የሻሸመኔ ነዋሪ ዛሬ ብሶቱ ገንፍሎ ወጥቶ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን ሲያሰማ ዋለ::
“በየምሽቱ እየተገደሉ የሚገኙት ወገኖቻችን ደም መፍሰሱ ይቁም” ሲሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የሻሸመኔ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን በአደባባይ ቢያሰሙም የፌደራል ፖሊስ እና አጋዚ ሕዝቡ ላይ ጥይት በመተኮስ ለመበተን ሞክረዋል::
በሻሸመኔ ማን እንደገደላቸው አይታወቅ እንጂ ከኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ ጋር የሚገናኙ ወጣቶች ተገድለው እየተገኙ ነው:: ባለፈው ሳምንት ህዝቡ ለቀብር በወጣበት ወቅት በአደባባይ ተቃውሞውን ቢያሰማም ሰሚ አጥቶ እንደውም ግድያው እየተባባሰ መሄዱ ዛሬ ህዝቡ በአደባባይ ወጥቶ ብሶቱን እንዲያሰማ ምክንያት ሆኖታል::
በዛሬው ተቃውሞ ተማሪዎች እና ነዋሪው ሕዝብ በአንድ ላይ ወጥቷል::shashemene

የቀድሞ ሰማያዊ ፓርቲ አባል አርበኛ ሜሮን አለማየሁ አርበኞች ግንቦት7ን ተቀላቀለች

 አይሲስ በሊቢያ ኢትዮጵያውያንን መግደሉን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ ላይ ያሳየውን ቸልተኝነት በመቃወም በተጠራው ሰልፍ ላይ በመውጣት ‹ወያኔ ሌባ፣ መንግስት የለም፣ አትነሳም ወይ፣ የታረደው ወገን ያነተ አይደለም ወይ›› በሚል ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራለች በሚል ተከሳ 6 ወር ተፈርዶባት የነበረችው የሰማያዊ ፓርቲ አባሏ ሜሮን አለማየሁ አርበኞች ግንባርን በኤርትራ መቀላቀሏን አስታወቀች::
በአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ ላይ ቀርባ ከአስመራ የሰማያዊ ፓርቲ አባልና የአዲስ አበባ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል ሀገር ቤትበነበረችበት ወቅት በሕወሓት መንግስት የደረሰባትን መከራ ያስረዳችው ሜሮን ኢትዮጵያን ነፃ ለማውጣት ያለው አማራጭ ቆርጦ ጫካ መግባትና ጠመንጃ መያዝ ነው ብላለች::
ሜሮን ከአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ ጋር ያደረገችውን ቃለምልልስ ያድምጡ

ኢትዮጵያ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በተመለከተ ለእንግሊዝ መንግስት ስትሰጥ የነበረው መረጃ የተሳሳተ እንደነበር ተገለ

ኢሳት (ሰኔ 15 ፥ 2008)
የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ ለብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተሳሳተ መረጃ ሲሰጡ እንደነበር ዛሬ ረቡዕ የወጣ መረጃ አመለከተ።
ሪፕሪቭ የተባለው ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አንዳርጋቸው ጽጌን ለመርዳት ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ የብሪታኒያ ባለስልጣናትን ላይ እንቅፋት ሆኖ እንደቆየና፣ በሰውየው መለቀቅ ጉዳይ ላይ ተስፋ እንዲቆርጡ ጥረት ሲያደርግ እንደነበር አጋልጧል።
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የት እንደታሰሩ ለመናገር ፈቃደኛ እንዳልነበሩና የቆንስላ ጉብኝቶችን ጨምሮ ለመታሰራቸው መሰረታዊ የህግ አግባብነት ያላቸውን ጥያቄዎችን ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ሪፕሪቭ በመግለጫው አትቷል። የብሪታኒያው የውጭ ጉዳይ ሚስተር ፊሊፕ ሃመንድ አቻቸው የሆኑት የኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም መሰረታዊ ጥያቄዎቻቸውን እንኳን በተደጋጋሚ ለመመለስ ባለመፈለጋቸውን ሲማረሩ እንደነበር መገለጹ ተመልክቷል።
በተመሳሳይ ሁኔታም የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ያለቀለት በመሆኑ ጠበቃ እንደማያስልፈልጋቸው ለብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መግለጻቸው ተመልክቷል።
የሪፕሪቭ ሪፖርት እንደተመለከተው፣ አቶ አንዳርጋቸው በታሰሩበት በሁለት የሰቆቃ አመታት፣ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል የገቧቸውን ነገሮች ሁሉ በተደጋጋሚ ሲያጥፉ እንደነበር ገልጿል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የህግ መብት እንደሚጠበቅላቸው በቅርቡ ቃል የተገባላቸው ፊሊፕ ሃምንድ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ሰቆቃ ከማባባስ/ከማስረዘም ባለፈው ምንም መፍትሄ አያመጡም ሲሉ የሪፕሪቭ ዳይሬክተር የሆኑት ማያ ፎዓ መናገራቸው ተገልጿል።

Wednesday, June 22, 2016

የዘረኝነት ወረርሽኝ፣ ተስፋ አስቆራጭና አስፈሪ የጨለማ ጉዞ መድሃኒቱ ያልተገኘለት ትልቁ በሽታ እና የበታችነት አባዜ




የዘረኝነት ወረርሽኝ፣ ተስፋ አስቆራጭና አስፈሪ የጨለማ ጉዞ መድሃኒቱ ያልተገኘለት ትልቁ በሽታ እና የበታችነት አባዜ
አብዛኛው የምናየው በሰብዓዊነት እና በቀና መንፈስ እየተንደረደረ የወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ቫይረስ ተሸካሚ ሆኗል፤በሰከነ መልኩ ረጋ ብለን በተዘዋዋሪ ማሰብ የጀመርን ቀን ይገባናል ከዚህ ጎን ለጎን መርሳት የሌለብን ነገር ቢኖር ለዚህ ቫይረስ ማስፋፊያ እና ማበረታቻ ወያኔ የፈጠራቸው የዘረኝነት መርፌ ወጊዎች መኖራቸውን ነው፤ በዩንቨርስቲዎች በቅርቡም በስፖርት ሜዳዎች የተከሰቱት የዘረኝነት ችግሮች እና ግጭቶች ከዚህ የወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ሂደት ጋር በጣም የተሳሰሩ መሆናቸውን ልናውቅ ይገባል።ሳንፈልገው እያንደረደረ ወስዶ ከጎሳው ፖለቲካ ስለዶለን በዘረኝነት ስንፎር የምንውል መሆናችንን ባለመረዳታችን የበታችነት ስሜት አየተጠናወተን በጥላቻ አየተመምን ነው።

የዘረኝነት ወረርሽን ከአመት አመት እየተባባሰ፣ አገሪቱ እየተንሸራተተች ናት። የበርካታ ምሁራንና ዜጎች አዝማሚያ ስትመለከቱ… ሁሌም ባይሆን አንዳንዴ፣ የዚህች አገር ነገር፣ተስፋ ያስቆርጣል። ኢህአዴግ፣ ተቃዋሚዎቹን ያወግዛል – “የሁለት ተማሪዎችን ፀብ፣ የብሔረሰብ ፀብ አስመስለው ያራግባሉ” በማለት። ተጠያቂዎቹ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከሆኑ፣ ስልጣን ላይ ከሃያ አመት በላይ የቆየ ፓርቲ፣ ይህን በሽታ ማቃለል ለምን አቃተው? በርካታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ኢህአዴግን ይኮንናሉ – “የብሄረሰብ ፖለቲካን አስፋፍቷል፤ የቀበሌ መታወቂያ ላይ ይመዘግባል” በማለት።ምንሊክ ሳልሳዊ ግን፣ ኢህአዴግ ስልጣን ባልያዘበት በአሜሪካ፣በዳያስፖራ ፖለቲካና በፌስቡክስ ዓለም ለምን ዘረኝነት ገነነ? በዚህ መሃል ግን፣ የዘረኝነት ወረርሽን ከአመት አመት እየተባባሰ፣ አገሪቱ እየተንሸራተተች ናት። የዘረኝነት ወረርሽኝ ለኢትዮጵያ አስፈሪ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ። እርስበርስ፣ “አንተ ነህ ዘረኛ”፣ “አንቺ ነሽ ዘረኛ” እያሉ ይወነጃጀላሉ። ብዙዎቹ የሚያቀርቧቸው አማራጮች ግን፣ በቅፅል ብቻ የሚለያዩ የዘረኝነት መልኮችን ነው።
ምንም እንኳ፣ ኢትዮጵያ በብዙ አይነት የጥፋት ፈተናዎች ውስጥ፣ ህልውናዋን ሙሉ ለሙሉ ሳታጣ ያለፈች አገር ብትሆንም፣ የበርካታ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች ዝንባሌን ስትታዘቡ፣ የበርካታ ምሁራንና ዜጎች አዝማሚያ ስትመለከቱ… ሁሌም ባይሆን አንዳንዴ፣ የዚህች አገር ነገር፣ተስፋ ያስቆርጣል። ከአመት አመት፣ የዘረኝነት ወረርሽኙ እየባሰበት፣ አገሪቱ ወደለየለት የጥፋት አዘቅት እንዳትሰምጥ አትሰጉም? በእርግጥ፣ አልፎ አልፎ፣ የዘረኝነት በሽታው፣ ለአፍታ ጋብ ሲልለት… እሳቱም ትንሽ ሲበርድለት እያየን፣ የእፎይታና የተስፋ ስሜት እናገኛለን። ግን፣ እፎይታው ብዙም አይቆይም። እንደገና በሽታው ያገረሸበታል። ማገርሸት ብቻ አይደለም። ከእያንዳንዱ እፎይታ በኋላ፣ ወረርሽኙ ባገረሸ ቁጥር፣ ከቀድሞው እጅጉን ብሶበት እናገኘዋለን። ተስፋ አስቆራጩና አስፈሪው ነገር ደግሞ ምን መሰላችሁ? የዘረኝነት ወረርሽኙን ለማስቆም የሚያስችል፣ አስተማማኝ መላ ምን እንደሆነ በግልፅ ጎልቶ አለመታየቱ ነው። ዙሪያው ሁሉ በጨለማ የተዋጠ ጉዞ ይመስላል።
በዩንቨርስቲዎች በቅርቡም በስፖርት ሜዳዎች እያየን ያለነው ጉዳይ አጅግ የሚገርም እና የለውጥ ሃይል ነን የሚሉ ኣማሳኞች ሳይቀሩ አየተራወጡ ያሉበት የዘረኝነት መነባነብ በኣገሪቱ ስር አንዳይሰድ ትውልዱ እንዳይበከል የሚያስፈራ ጉዳይ መሆኑ ውሎ ኣድርዋል፥፥ምንሊክ ሳልሳዊየሚደርሱኝ መረጃዎች አንደሚጠቁሙት ዘረኝነትን ለማስፋፋት የተለያዩ ኣካላት ገንዘብ መድበው በሃገር ቤት ያለውን ወጣት ለፍጅት እና ለኣጀንዳቸው ማስፈጸሚያ አያጩት ነው።ይህ ደግሞ የሕወሓት አጅ የለበትም ማለት ዘበት ነው። ሕወሓት ወንጀለኘ አና ኣሸባሪ ዘረኛ እና ኣስመሳይ ማፊያ እና ዘራፊ ሕገወጥ ድርጅት ነው።
በዲያስፖራው ዘንድ በስፋት አየተራገበ ያለው ይህ ወያኔ ወለድ በሽታ ዋናው ክስተቱ የገዢው ፓርቲ ሕወሓት የፈጠረበት የበታችነት ስሜት ሲሆን በሕወሓቶች ዘንድ ከበታችነት ለመላቀቅ በሚደረግ መራወጥ የሚፈጠር ጥላቻ ዘረኝነት የሰረጸባቸው ያዩት የሰሙት ሁሉ የሚያስደነብራቸው የበታች መደቦች ኣንድ ጉዳይ በተነሳ ሰኣት ሁሉ ዘር ላይ የሚንጠለጠሉ እና የስልጣን ጥማትን ለማርካት ሲባል የሃገር አና ሕዝብን ሃብት ለመበዝበዝ የነገ ትውልድ ኣደጋ የማይታያቸው ሕዝብን በዘር በመከፋፈል ለመግዛት የሚያደርጉት ደባ ነው። ቆቤ ኦሮሞ ፤ ቤተ ኣማራ ፤ ትግራዋይ ምናምን እየተባለ በወያኔ የደህንነት ተቍማት ስራ የሚደራጁ ክንፎች በነማን እንደሚመሩ በነማን በጀት እንደሚጦዙ የኣጀንዳዎቹ መነሻዎች እነማን እንደሆኑ ምስክር ኣያስፈልግም።
ይህ ወያኔ ወለድ የሆነ የዘረኝነት በሽታ በኢትዮጵያ ውስጥ ይህን ያህል ባይስፋፋም በዲያስፖራው ዘንድ ግን ስር የሰደደ በሽታ ከሆነ ሰነባብዋል።ጥቂት ዲያስፖራዎች በሃገር ቤት ያሉትን ወጣቶች በገንዘብ በመግዛት ዘረኝነትን ለማስፋፍት ሲጣጣሩ ይስተዋላል።ኣለም በኣንድ የእድገት መሰረት ላይ ለመመስረት በቴክኖሎጂ እና ትልልቅ ግኝቶች ላይ ባተኮረበት በዚህ ዘመን ጥቂቶች የሚፈጥሩት የድህረገጽ የዘረኝነት ወከባ አጅግ ኣሳዛኝ እና ኣስደንጋኝ ነው።ሕወሓት አነዚህን በቆሸሸ ታሪክ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሰዎችን በመጠቀም ኢትዮጵያውያንን በዘር ከፋፍሎ ኣጀንዳውን ለማስፈጸም አየሮጠ ነው።በዲያስፖራው ጉያ ስር ተወኅቀው የወያኔን የዘረኝነት ኣጀንዳ ለመፈጸው አያወቁም ሳያውቁ ደፋ ቀና የሚሉ ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ሊያስቡ ይገባቸዋል።የማያዘልቅ ጸሎት ለቅጽፈት መሆኑን ተረድተው ከዘረኝነት በሽታ ሊላቀቁ ይገባቸዋል። በጥቅም ላይ የተመሰረተ ወጣቱ ያላመነበት የዘረኝነት መስፋፋት ውጤቱ በአኩይ ተግባር ላይ ለተሰማሩ ዘረኞች ኣደጋ ነው።‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Sunday, June 19, 2016

የጳጳሳት ሹመትና ተቸዎች ያላወቁት እውነት

የጳጳሳት ሹመትና ተቸዎች ያላወቁት እውነት

የጳጳሳት ሹመትና ተቸዎች ያላወቁት እውነት የኢትዮጵያ ህዝብ በስደትም ይሁን በሃገር ቤት ቁጥሩ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው በዚያው ልክ እረኛ አባት ማስፈለጉ አያጠያይቅም እንዳለመታደል ሁኖ የሁለት ሲኖዶስ ባለቤት ከሆን ሰንበትበት ብለናል ልዩነቱን ባንደውም በየፊናቸው እየሰሩት ያለው ግን ቀላል አይደለም ምንአልባትም ባንድነታቸው ሊሰሩት አይችሉ ይሆናል ምክንያቱም ለመላ አሜሪካ ይመደብ የነበረው ጳጳስ አንድ ብቻ ነበር አሁን ውድድር ስለሆነ በሁሉቱም በኩል ቁጥሩ ጨምሯል ግን አሁንም በቂ አይደለም ምክንያቴን ወደፊት እገልጻለሁ ልዩነቱ ያመጣው መዘዝ ለትውልድ ከተረፈ ግን አደጋው የከፋ ቢሆንም ለጊዜው ግን ሁሉም በየፊናቸው ለቤተክርስቲያን እንድገት በአቅማቸው ጊዜው የሚጠየቀውን አድርገዋል እያደረጉ ነው በርግጥ ከእነሱ ብዙ ስለምንጠብቅ ከተሰራው፡ ሊሰራ የሚገባው ጎልቶ በማየታችን ድክመታቸውን አጉልተን ስንናገር እንሰማለን ይህም ለስራው ካለን ቀናኢነት እንጅ አባቶች ጠልተን አይደለም ይሁንና በስራው ቀርበን ሳንጠይቃቸው ሳናግዛቸው ወቅቱ ውስብስብ መሆኑን ሳንገነዘብ ያቅማቸውን ውስንነት ሳንረዳ መፍረዱ የኛን የአረዳድ ድክመት ከማሳየት አልፎ በነሱ ላይ ለውጥ ሊያመጣ ግን አይችልም በስደት የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች ለመሾም የሄደበት መንገድ አግባብነት አለው ምክንያቱም ሲኖዶስ እስካለ ድረስ ጳጳስ መሾም ጥያቄም ውስጥ ሊገባ አይገባውም የሲኖዶስ ሥራው ምንሆነና ነው። መጀመሪያ እራሱን ሲኖዶሱን በሰው ሃይል ማጠናከር ተገቢ ነው ባይሾሙ ነበር እንጅ የሚገርመው መሾማቸው ምን ይገርማል ብዙ ሰዎች የማያስገርመው ያስገርማቸዋል ቅዱስ ሲኖዶስ ጳጳስ ለምን ሾመ ብሎ መጠየቅ እናት ለም ልጅ ትወልዳለች ብሎ እንደ መጠየቅ ያህል ያስቆጥራል ወይም የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣንና ልዕልና አለመረዳት ነው በሀገርቤቱም ይሁን በስደቱ ለቤተክርስቲያኒቱ የሚያስቡና የሚሰሩ አባቶችን ህዝቡ በስማ በለው ሳያውቃቸው መተቸቱ ልማዳዊ ባህል እየሆነ መጥቷል የማያውቀውን የሚተች ህዝብ እየበረከተ መምጣቱ እጅግ ያሳዝናል አባቶቻችን እስከነ ድክመታቸውም ቢሆን ወርቃማ ናቸው የነሱን ሩብ ዘመን ሳንኖር የሰሩትን ስራ እንኳን አይተን ሳንጨርስ ለመተቸትና ለመናገር እንቸኩላለን እኛ ምን ሰራን ብለን ግን እራሳችን ጠይቀን አናውቅም አሁን የተሾሙ ጳጳሳት ጉድለታቸው ምንድ ነው ከተሿሚዎቹ አንዱ ምን አልባትም አባ ወልደ ትንሳኤ አሳማ ብሉ በለው አስተምረው ከሆነ ይህን ቀድመው በመጻፍ ያስቀመጡት ብጹእ አቡነ ጎርጎሪዮስ ናቸው የሳቸውም ትምህርት ከውጭ ሀገር ተምረው ሲመለሱ አውሮፓውያን ሳይመርጡ ሲበሉ ማየታቸው የእኛን ሀገር ትውፊትና ባህል በተጣረሰ መልኩ ጽፈዋል ቢሆንም ብጹነታቸውን እንወዳቸዋለን ታዲያ አባ ወልደ ትንሳኤን /አቡነ በርናባስ/ ለምን እጠላቸውአለን ለመሆኑ መናፍቅ ብሎ ለመናገር እኮ ተናጋሪው መጀመሪያ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና ትውፊትና ባህል ለይቶ ማወቅ አለበት የቱ ነው መናፍቅ የሚያሰኘው የሚለውንም መረዳት አለበት አንዳዶቹ የግል አለመግባባታቸውን ሃይማኖታዊ ሽፋን በመስጠት ለማስጠላት ይሞክራሉ እንዴውም አባ ወልደ ትንሳኤ/አቡነ በርናባስ/ ትምህርቶቸ መሠረት ያደረጉት የአቡነ ጎርጎሪዮስን መጻህፍቶችን ነው በመሆኑም ስህተት የለበትም እንጅ ቢኖርበት ተጠያቂ የሚሆኑት አቡነ ጎርጎሪዮስ ናቸው አንባቢ ማስተዋል ያለበት ሃቁ ነው የግል ጥላቻ በቤተክርስቲያን ላይ ባይጸባረቅ ጥሩ ነው ከሆነም ደግሞ ሰው መወቀስ ያለበት በሰራው እንጅ ሌላ በሰራው መሆን የለነበትም አባ ወልደ ትንሳኤ ብዙ ጥሩ ኳሊቲ አላቸው በምንኩስናቸው አይታሙም የገንዘብ ጾር የለቸውም አንደበተ ርቱእ ናቸው ቤተክርስቲያንን በብዙ መልኩ ይጠቅማሉ ከበብዞች ያጣነውን ንጽህና ማገኘቱ በራሱ ቀላል አይደለም በርግጥ ደፋር አስተማሪነታቸው ቢወደድም ሃይማኖት መገለጫው ባህል ነውና ይህን ያለማክበር አዝማሚያ በአንድ ወቅት አሳይተው ነበር አሁን ግን ትተዋል ብዞቹ አባቶች በሃገር እርቀት በዘመን ብዛት በሀገር ውስጥ የሚደረገውን አያውቁም ቀደምሲል ነቃ ያሉት አገልጋዮች እንደ ሃይማኖት ለዋጭ ይቆጠሩ ነበር አለባበሳቸው አነጋገራቸው ሁሉ ይመዘን ነበር እናም መናፍቅ የሚትለው ቃል በሆነ ባልሆነው ስንጠቀምባት ስለ ቆየን አሁን ቤተከርስቲያኒቱ ሊያፈርሱ የተነሱትን ማጋለጥ እንኳን አልተቻለም እራሳቸው በወብሳይት እያስተዋወቁ አለን እያሉ ህዝቡ የራሱ የሆኑት ለይቶ ለማወቅ እድል አላገኘም ይልቁን የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ህዝቡን በማደናገር የሆኑትን ካልሆኑት መለየት እንዳንችል አድርገውናል ይህንን በማስመልከት ብዙ አላስተማሩ ይሆናል ክፍተቱ ግን የኢንፎርሽ እጥረት ነው ይህም የሆነው ብዞቹ አባቶች ከመጡ ከ 20 ዓመት በላይ የሆናቸውና ያንጊዜ ያለውንና አሁን ሆን ተብሎ ቤተክርስቲያን ለማዳከም የሚሰራውን አለማዎቃቸው ነው የችግሩ ምንጭ ይህ ካልሆነ በቀር አሁን የተሾሆሙ አባቶች የሚተቹበት ነውርም ሆነ ነቀፋ የለባቸውም ሿሚዎች ቤተክርስቲያኒቱ በሁለመናዋ ልቃ እንድትገኝ የደከሙ አባቶች ናቸው ያባቶችን ስህተት በማስረጃ አስደግፎ የጻፈ አላየሁም ጥላቻን ያንፀባረቀ ምቀኝነት መሠረት ያደርገ ብዙ ተብሏል እውነተኛ ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆር ካለ አባቶችን ቀርቦ የወቅቱን ተጨባጭ እውነታ ማስረዳቱና መረዳቱ ከከንቱ ጥላቻ ያድናል አንባቢ ሆይ እውነቱ ማወቅ ተገቢነው አቡነ መልከ ጼዴቅን ያህል ጸሎተኛ ጾሚ ለአግልግሎት ቀናኢ የለም ቀርበህ እወቃቸው በሩቅ አተች ለአንተም ጥሩ ነው እራስህን ታይበታለህ ምንአልባትም ወደፊት በወሬ መጥላት ታቆማለህ ይጠቅምሃል ወደፊት ሰፋ አድርገን እንመለስበታለን እስከ ዚያው ግን አባቱ የሚሰድብና የሚያቃልል ልጅ ከመሆነ እግዚአብሔር ይጠብቀን ይቀጥላል ከሊቀ መራህያን ማንኛውም ሰው እውነቱ ማወቅ ከፈለገ በንጹ አይምሮ በዚህ እሜል ሊያገኘኝ ይችላል jemis1968@gmail.com

Friday, June 17, 2016

የቅ/ላሊበላ ቤተ ሩፋኤል እና ቤተ ገብርኤል አብያተ መቃድስ: በ15 ሚ. ብር ወጪ ተጠገኑ

conservation and consolidation of Lalibela project111
በከፍተኛ ባለሞያዎችና በላቀ ቴክኖሎጂ ጥገና የተደረገላቸው ቤተ ሩፋኤልና ቤተ ገብርኤል
  • ዩኔስኮ፣ የዓለም ቅርስ ፈንድና የአሜሪካ መንግሥት በገንዘብና በሞያ ደግፈዋል
  • ቤተ ክርስቲያን፥ ከጸሎት እና ጥብቅ ክትትል ጋር በባለቤትነት ተሳትፋለች
  • ለይምርሐነ ክርስቶስ ጥገና የ150 ሺሕ ዶላር የጥናት ስምምነት ተፈርሟል
  • ደብሩ በአ/አበባ ሕንፃ ለማስገንባትና አስጎብኚ ቢሮ ለመክፈት ዐቅዷል
(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፰፻፶፮፤ ቅዳሜ ሰኔ ፬ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)
በዩኔስኮ የዓለም አስደናቂ ቅርሶች የተመዘገቡትና የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አካል የኾኑት የቤተ ሩፋኤል እና ቤተ ገብርኤል አብያተ መቃድስ፤ በረጅም ጊዜ አገልግሎት እና በተፈጥሮ በደረሰባቸው የመሠንጠቅና የማፍሰስ ጉዳት የተነሣ በከፍተኛ አደጋ ውስጥ የነበሩ ሲኾን፤ በ15 ሚሊዮን ብር ወጪ በከፍተኛ ቴክኖሎጂ የታገዘ ውጤታማ ጥገና እንደተደረገላቸው ተገለጸ፡፡
ከዩኔስኮ፣ ከዓለም ቅርስ ፈንድ(World Monument Fund) እና ከአሜሪካ መንግሥት(American Ambassador’s Fund) በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ የተካሔደውን የጥገና ፕሮጀክት በሓላፊነት ያሠራው በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የቅርስ ጥበቃ መምሪያዋና በደብሩ አስተዳደር በኩል፤ከፕሮጀክቱ ጥናት እስከ ፍጻሜው ድረስ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ በባለቤትነት መሳተፏ ታውቋል፡፡
አምስት ዓመት በወሰደው የፕሮጀክቱ ጥናት መሠረት፣ ኦልሚ ኦሊንዶ የተባለ አገር በቀል ደረጃ አንድ ኮንትራክተር የአብያተ መቃድሱን ጥገና ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሲያካሔድ የቆየ ሲኾን፤ የፌደራል ሳይንቲፊክ ኮሚቴ ያስተባበራቸው ኢትዮጵያውያን የሥነ ሕንፃ እና የሥነ ምድር ባለሞያዎች ከታዋቂ የእንግሊዝና የጣሊያን ጠበብት ጋር መሳተፋቸው ተጠቅሷል፡፡
የውቅር አብያተ ክርስቲያናቱን አካባቢ የኅብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈ ኮሚቴም፣ ለፕሮጀክቱ መሳካት የበኩሉን ድርሻ እንደተወጣና፤ የደብሩ አስተዳደርና ማኅበረ ካህናት ጸሎትም እገዛ እንዳደረገ፣ ባለፈው ሳምንት እሑድ የፕሮጀክቱን መጠናቀቅ አስመልክቶ በስፍራው በተካሔደየምረቃና የምስክር ወረቀት አሰጣጥ መርሐ ግብር ላይ ተገልጿል፡፡
ዓለም አቀፍ ቅርሱን ከማዳንና ለትውልድ ከማሸጋገር አንፃር በጥገናው ከፍተኛ ሥራ መሠራቱ በተገለጸበት በዚኹ መርሐ ግብር፤ በዩኔስኮ የአፍሪቃ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ኢ.አልፋኢ ራይት፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ፓትሪሺያ ሃስላች፣ የፌደራል ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ከፍተኛ ሓላፊዎች፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አባ ኃ/ማርያም መለሰ፣ የአማራ ክልል የሥራ ሓላፊዎችና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲኹም በርካታ ምእመናን ተገኝተዋል፡፡
Complition of the conservation and consolidation project
የጠቅ/ጽ/ቤት ም/ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አባ ኃይለ ማርያም መለሰ መልእክት ሲያስተላልፉ
በዓለም ቅርስነት የሰፈሩት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት፣ ከ800 ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩና ከአንድ ወጥ አለት ተፈልፍለው የተሠሩ 11 ውቅር አብያተ መቃድስ ያሉት ሲኾን፤ እነርሱም በሦስት ምድብ የተከፈሉ ናቸው፡፡ ቤተ መድኃኔዓለም፣ ቤተ ማርያም፣ ቤተ ሚካኤል፣ ቤተ መስቀል፣ ቤተ ጎልጎታ(ደብረ ሲና) እና ቤተ ደናግል ምድብ አንድ፤ ቤተ ዐማኑኤል፣ ቤተ መርቆሬዎስ፣ ቤተ ገብርኤል- ሩፋኤል እና ቤተ አባ ሊባኖስ ምድብ ኹለት፤ ከኹለቱ ምድቦች ፈንጠር ብሎ የሚገኘው ቤተ ጊዮርጊስ ደግሞ ምድብ ሦስት በመባል ይከፈላሉ፡፡
ከዐሥራ አንዱ ውቅር አብያተ መቃድስ፣ ቤተ መድኃኔዓለም በግዙፍነቱ፤ ቤተ ዐማኑኤል እና ቤተ ማርያም ባለደርብነታቸው(በፎቅነታቸው)፤ቤተ አባ ሊባኖስ ከዋናው አለት ጋር የተያያዘ በመኾኑ፤ ቤተ ጊዮርጊስ በመስቀል ቅርፅ በመሠራቱና ረቅቂ የኪነ ሕንፃ ጥበብ የተከወነበት በመኾኑ የየራሳቸው ልዩ ባሕርይና መስሕብ አላቸው፡፡ የስፍራውን የቱሪስት ፍሰት ያጠናክራል የተባለ አስጎብኚ ቢሮ በአዲስ አበባ ለመክፈትና ሕንፃም ለማስገንባት የደብሩ አስተዳደር መዘጋጀቱ ተጠቁሟል፡፡
የይምርሐነ ክርስቶስ ደብር ቤተ መቅደስ
የይምርሐነ ክርስቶስ ደብር ቤተ መቅደስ
በተያያዘ ዜና፣ የአብያተ መቃድሱን ጥገና በቴክኒክና በገንዘብ የደገፈው የዓለም ቅርስ ፈንድ፣ ከላሊበላ የ5 ሰዓት የእግር መንገድ ርቀት በተመሳሳይ ጉዳት ላይ ለሚገኘው የይምርሐነ ክርስቶስ ደብር ኪነ ሕንፃ የቅድመ ጥገና ጥናት፤ 150 ሺሕ ዶላር መለገሡንና ስምምነቱም፣ በፈንዱ የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ስቴፈን ባትልና በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መካከል ከኹለት ወራት በፊት በመንበረ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት መፈረሙ ተገልጿል፡፡

Thursday, June 16, 2016

ሰበር ዜና !! ዛሬም ቁስለኞች ወደ ትግራይ እየተጋዙ ነዉ!!



በትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን የተለኮሰዉን የጦር ጸብ አጫሪነት ኤርትራ በቀላሉ አልተመለከተችዉም!
በመሆኑም በኢትዮ ኤርትራ አዋሳኝ ድንበሮች ዙሪያ ከፍተኛ መጠን ያለዉና ዘመናዊ የሆነ ሰራዊት ማለትም የአየር ወለድና ባሕር ሐይል አጠቃላይ ፊቱን ወደ ትግራይ ነጻ አዉጪዉ ጦር በማዞር ለግዳጅ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን መረጃዎቻችን ተናግረዋል። 
ወያኔ ጦርነቱ ጋብ ብሏል የሚል ማስተባበያ ቢስጥም በኤርትራ በኩል ከፍተኛ የሆነ የበቀል እርምጃ በመዉሰዱ የወያኔ የቦርደር ሆስፒታሎች በቁስለኛ ወታደሮች ከመጨናነቃቸዉ በተጨማሪ ሌሎች ቁስለኞች ዛሬም ወደ ትግራይ ሆስፒታል መወሰዳቸዉን ምንጮች አሳዉቀዋል።
በባሕር ላይ ዉትድርና እረጅም አመታትን በእስራኤልና በግብጽ ሲሰለጥኑ የነበሩ የኤርትራ ሰራዊቶችን ወደተፈለጉበት የጥቃት ወረዳ እንዲፈነጠሩ በሚያስችል የወደብ ከተማዎች ላይ እያሰማራ የሚገኘዉ የኤርትራ አየር ሐይል ጦርነቱን እጅግ የሚፈልገዉ ይመስላል ያሉት መረጃዎች አክለዉ እንደገለጹት ዘመናዊ የሮማኒያ፣ ሩሲያ፣ እስራኤል ሰራሽ የሆኑ የጦር ጀቶች ትንኮሳ በተደረገባቸዉ ስፍራዎች ላይ እያንጃበቡ መሆኑን ገልጸዋል።
ዝግጅቱ በወያኔ በኩልም የቀጠለ ሲሆን የትግራዩ ነጻ አዉጪ ቡድን በአየር ሐይሉ ላይ ባለዉ ጥርጣሬ ምክንያት እንቅስቃሴዎች ብዙም እንደማይታዩ ምንጮች ሲገልጹ አያይዘዉ የወያኔ ሰራዊት ይህን ጦርነት ሆን ብሎ ለፍተሻ እንዳደረገዉ እና ኤርትራ ድብቅ የዉጊያ ስልቶችን፣ሐይሎችን እና ብቃትን በሙሉ ባለማዉጣት ወታደራዊ መረጃዎቿን እንድትጠብቅ አሳስበዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
http://www.madote.com/2010/02/picture...
( ጉድሽ ወያኔ )

የዐማራ ሕዝብ የመኖር ሕልውናው አደጋ ላይ ነው

የዐማራ ሕዝብ የመኖር ሕልውናው አደጋ ላይ ነው

ሙሉቀን ተስፋው
በአሜሪካን አገር የሚኖር አንድ ወዳጄ ሰሞኑን ቤት ልገዛ ነው አለኝ፡፡ ይህን ነገር ስሰማ በአእምሮዬ የመጣው ‹‹እንዴት በሰው አገር ቤት ለመሥራትና ቋሚ ንብረት ለማፍራት ጨከነ?›› የሚል ነው፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ይኖራሉ፡፡ ባላቸው የትህምርት ዝግጅትና ችሎታ ከማንኛውም የዓለማችን ዜጎች ጋር ተወዳድረው የፈለጉትን ሥራ ማከናወን ብሎም ገንዘብ አጠራቅመው ቋሚ ንብረት ማፍራት ይችላሉ፡፡
ነገር ግን በዚህ ዘመን ዐማሮች በአሜሪካ ወይም በሌላው የዓለማችን ክፍል ሀብትና ንብረት ለማፍራት የሚደፍሩትን ያክል በኢትዮጵያ ውስጥ መብት የላቸውም፡፡ ለነገ ብለው የሚያስቀምጡት ጥሪት ዛሬ ምሽት ሊወድም ይችላል፡፡ ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በየትኛውም ቦታና አካባቢ ዐማራ ሀብትና ንብረት ማፍራት አይችልም፤ ቢያፈራም በድንገት ሊወድምበት ይችላል፡፡
በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በጉምዝ፣ በአፋር፣ በሐረሪ፣ በሶማሌ፣ በትግሬ፣ በድረደዋ ብሎም በአዲስ አበባ ዐማሮች በይፋና በስልት ቀያቸውን ይለቃሉ፤ ይገደላሉ፡፡ ለመሆኑ ስንቶቻችሁ በአዲስ አበባ የሚፈናቀለው ዐማራ ቁጥር ከጉራ ፈረዳና ከቤንሻንጉል ጉምዝ ከተፈናቀለው ዐማራ ድምር ውጤት በላይ እንደሆነ ታውቃላችሁ?
አዲስ አበባን መልሦ ማልማት በሚል ፈሊጥ ስንቶቹ የዐማራ ርስቶች እየተነቀሉ ለወያኔ ካድሬዎች ተሰጥተዋል? ልደታ የተፈናቀለው ዐማራ ስንት ነው? አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት የተነሱት ዐማሮች የት ሔዱ? ካዛንችስ ምን እየሆነ ነው? አሜሪካን ግቢ? ሽሮ ሜዳ? … አዲስ አበባ ላይ ያለው መልሦ ማልማት ሥራ ዐማሮችን ከመሃል ከተማ እያስወጡ ባተሌ ለማድረግ እንደሆነ ስንቶቻችን ተረዳን?
እንግዲህ ዐማሮች በቆረቆሩት ከተማ፣ በተወለዱበት ቀዬ፣ በአቀኑት አገር መብት የላቸውም፡፡ ለሚገድሏቸውና ለሚያፈናቅሏቸው አበል እንዲከፍሉ ይገደዳሉ፡፡ ዕውነት ለመናገር ስለ ዐማራ መናገር ‹ወገንተኛ› የመሆን እና ያለመሆን ጥያቄ አይደለም፤ የሰብአዊነት ጉዳይ ነው፡፡
((ከታች የሚታየው ምስል በመስከረም 2007 ዓ.ም. በጉራ ፈረዳ በገጀራና በድንጋይ የተገደለ ዐማራ ነው))

አማራን ነጥለው በጠላትነት የፈረጁት ፋሺስት ጣሊያን፣ ናዚ ጀርመን፣ ምእራባዊያን ኢምፔሪያሊስቶች፣ የወያኔ ትግሬና ሻቢያ
~~~~~~~~~~~~~~~~~
እነ መለስ ተክሌን የመሳሰሉ በቀድሞው የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የነበሩ የትግሬና የኤርትራ ተወላጆች መሪነትና አነሳሽነት የተከፈተው ኢትዮጵያን በጎሳ የመከፋፈል ሴራና ጸረ አማራ ፕሮፓጋንዳ እንደ ዋለልኝ መኮንን ባሉ ጥራዝ ነጠቅ ቅጥረኞች ጽሁፍ አማካኝነት ገበያ ላይ ከመዋሉ እጅግ ቀደም ብሎ በጃን ሆይ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖር በነበረ ባሮን ሮማን ፕሮቻዝካ የተሰኘ ናዚ ኦስትሪያዊ የአውሮፓ ዲፕሎማቶች ተወካይ ተጠንስሶ፣ “Abyssinia the Powder Barrel” በተሰኘ በ 1926 ዓ ም ባሳተመው መጽሃፉ የሰፈረና በነዋለልኝና ጌቶቹ ቃል በቃል የተቀዳ መሆኑን ከሚቀጥለው ንጽጽር መረዳት እንችላለን:: ይህ የባሮን ፕሮቻዝካ ጸረ ኢትዮጵያዊነትና ጸረ አማራነት ጽሁፍ ከጣሊያን ወረራ አንድ አመት ቀደም ብሎ ለህትመት የበቃ ሲሆን የአሜሪካንን እንግሊዘኛ ጨምሮ በ 15 የአውሮፓ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በስፋት እንዲሰራጭ ተደርጓል::
ይህን መሰል ጸረ አማራ ፕሮፓጋንዳ በምእራባዊያን ዘንድ አማራ ለተሰኘ ነገድ ከፍተኛ ጥርጣሬ እንዲዳብር አስተዋጽኦ አድርጓል:: ጸጋዬ ገብረመድህን በአንድ ጦማሩ የአሜሪካ ሴኔት የአማራ ነገድ ጨቋኝና ጸረ ምእራባዊያን አመለካከት ያለው ነው ብሎ እንደሚያምን ኢትዮጵያዊያን በዋሽንግተን ዲሲ ባደረጉት ሰልፍ ላይ የሴኔቱ አባል የሆነ ግለሰብ የሰጠውን እጅግ ጸረ አማራ የሆነ መግለጫ ጠቅሶ አስነብቦናል:: ይህ ጸረ አማራ አመለካከት ይብዛም ይነስም አብዛኞቹ ምእራባዊያን ፖለቲከኞች የሚጋሩት እንደሆነ ከፖለቲካ ህይወት ልምዱ መታዘቡን ጸጋዬ ገብረመድህን በተጨማሪ ይገልጻል:: ጸጋዬ ለዚህ ምክንያት ሆኗል ያለውን ሲያስረዳ የወያኔ ትግሬዎችና እንደ ኦነግ ያሉ ጸረ አማራ ቡድኖች ለምእራባዊያን የመገቡት የተንሸዋረረና የጥላቻ የአማራ ነገድ ምስል ነው ይለናል:: ይህ ለኔ የዋህነት ነው:: ምእራባዊያን እንዲህ ጂኦ-ፖለቲካሊ እስትራቴጂክ ለሆነች ሃገር ፖለቲካ ባዕድ ሆነው አያውቁም:: ከአጼው ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ተከስተው ባለፉ አብዮቶችና አንኳር ፖለቲካዊ ክስተቶች፣ የርስበርስ ጦርነቶች፣ በኤርትራ የመገንጠል ጥያቄ፣ በስልሳዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴ፣በታህሳሱ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራና በመሳሰሉት የምእራባዊያን በተለይም የዘመናችን ኢምፔሪያሊስት ሃገረ አሜሪካ ቀጥተኛና የእጅ አዙር ተሳትፎ እንደነበረበት በግልጽ የሚያሳዩ ብዙ የታሪክ መረጃዎች አሉ (የፕሮፌሶር አለሜ እሸቴን ስራዎች እንድትመለከቱ እጋብዛለሁ)::
አሜሪካና አውሮፓዊያን ኢትዮጵያ እስከዛሬ ያለፈችባቸው የሃገሪቱን ገጽታና የምትመራበትን ርእዮተ አለም በአሉታዊ መልኩ ቀይረው ያለፉ ኩነቶችን ቅርጽ በማስያዝ የተጫወቱት ሚና ሃገር በቀሎቹ የኢትዮጲያዊነት ጠላቶች ሊኖራቸው ከሚችለው ሚና እጅግ የላቀ ነው:: የአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲ አይ ኤ በተወካዩ ማይልስ ኮፕላንድ በኩል በግዜው “ሰልፊ ንጻነት” በመባል ይታወቅ የነበረውን የሻቢያን አመራሮች በሲ አይ ኤ አባልነት በመመልመልና የሻቢያን ተገንጣይ አላማና ግብ አሜሪካ በቀጠናው የነበራትን ኢምፔሪያሊስት አጀንዳ በሚጠቅም መልኩ በመቅረጽ እንዲሁም ሻቢያን በትጥቅና በሎጂስቲክስ በማጠናከር በኢትዮጵያ ህዝብና ሉአላዊነት ላይ የፈጸመው ክህደት ለዚህ ትልቅ ማሳያ ነው:: የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ክሊንተን ባለቤት የሆኑት ሚስስ ሂላሪ በኤርትራ “ንጻነት” ዋዜማ አስመራ ተገኝተው ጨቅላዋ ሃገራቸው አዛውንቷን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ላበረከተችው አስተዋጽኦ በእቅፍ አበባና በሃገር ልብስ ስጦታ ተንቆጥቁጠዋል:: የአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲ አይ ኤ በ 2000 ዓ ም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ባወጣው አንድ ዶክዩመንት በኢትዮጵያ ያሉ ጎሳዎች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት በዘመነ ወያኔ መጎናጸፋቸውን ገልጾ ስለ መጪው የኢትዮጵያ እጣፈንታ ሲተነብይ በዚህ የሃገሪቱ ፖለቲካዊ አብዮት ጥቅሙ የተነካበት አማራ የተባለው ጨቋኝ ነገድ የቀድሞ የበላይነቱን ለማስመለስ በሚያደርገው ጥረት ምክንያትነት ሃገሪቷ እንደምትፈራርስ ያትታል:: ነገሩን በጥልቀት ስንመለከተው በራሱ የሚተማመን፣ የሃገሩንና የህዝቡን ጥቅም የሚያስቀድምና ለነሱ ፍላጎት ታዛዥ ያልሆነ እምቢተኛ ስርዓት በየትኛውም ሃገር እንዳይፈጠርና እንዳያብብ በማንኛውም መንገድ ማረጋገጥ ተቀዳሚው ተግባራቸው ያደረጉት ምእራባዊያን ኢምፔሪያሊስቶች የአማራን ነገድ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የቆመ የሃገሪቱ ጥቅም አስጠባቂ አድርገው የለዩት በመሆኑና የዚህ ነገድ በወሳኝ የሃገሪቱ የስልጣን እርከን ላይ መኖር በቀጠናው ላላቸው ኢምፔሪያሊስት አጀንዳ የማይመች መሆኑን በታሪክ ሂደት ስላመኑበት የአማራውን ነገድ ኢላማ ያደረጉ ተገንጣይ ሃይሎችን በጉያቸው ሸጉጠው ከመደገፍ በተጨማሪ በአማራው ላይ ለሚደርሱ ተደጋጋሚ ጉልህ ኢ-ሰብአዊ በደሎች ጆሮ ዳባ ልበስ ማለታቸውና ለወያኔ ትግሬ መንግስት እድሜ መርዘም ትልቁን ሚና መጫወታቸው የሚከተሉትን የጸረ አማራ ፖሊሲ ያስረግጥልናል :: እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂውማን ራይትስ ዋች ያሉ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሳይቀር የ 1993ቱ የወለጋው የአማራ ነገድ ጭፍጨፋና መፈናቀል ወቅት የአማራ ነገድን የቀድሞ “ጨቋኝነት” ገልጸው በጉዳዩ ጣልቃ ላለመግባት ያሳዩት ማመንታት የጸረ አማራ አመለካከቱ በምእራባዊያን ዘንድ ምን ያህል ስር እንደሰደደ ትልቅ አስረጅ ክስተት ነው::
የባሮን ፕሮቻዝካ መጽሃፍ ዛሬ የወያኔ ትግሬና ሌሎች ተገንጣይ ሃይሎች የየለት መዝሙር የሆነው የራስን እድል በራስ መወሰን የሚል የቃሉን ትርጉም የሚጣረዝ በታኝ አስተሳሰብ (“የእራስን” የሚለው ሃረግ ግለሰብን እንጂ የወል ስብስብን እንደማያመለክት ልብ ይለዋል) ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዮጵያ ያስተዋወቀ ነው:: ይህ የፋሺስት የከፋፍለህ ግዛው ጽንሰ ሃሳብ ከፋሺስት ወረራ ማክተም በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዮጵያ ምድር ነፍስ የዘራው በስልሳዎቹ የተማሪዎች አመጽ ዘመን ኤርትራዊ የሚል የባርነት ማንነት በያዙ ተማሪዎች አማካኝነት ነው:: የኤርትራዊያንን ጥያቄ ለማለዘብና ለማቀፍ በሚል የስልሳዎቹ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የኢትዮጵያ ዋነኛ ችግር ነው ብሎ ያስቀመጠው ኤርትራዊያን ተገንጣዮች ይዘው የተነሱትን የራስን እድል በራስ መወሰን የሚለው ፋሺስታዊ ጽንሰ ሃሳብ እንደ መፍትሄ የሚቀርብበት “የብሄር ብሄረሰብ ጥያቄ”ን ነበር:: እንደ ታላቁ ምሁር ፕሮፌሶር መሳይ ከበደ እምነት ኤርትራዊያን ብሄርተኞችን ለማባበል ሲባል ተቀብለን በመላው ኢትዮጵያ ላይ የተገበርነው “የኢትዮጵያ ችግር የብሄር ጭቆና ነው” መፍትሄውም የራስን እድል በራስ የመወሰንን መብት ለመጎናጸፍ የሚደረግ ትግል ነው የሚለው የኤርትራ ብሄርተኞች በፋሺስት አመለካከት የተቃኘ አቋም ኤርትራን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያንም አሳጥቶናል:: ኤርትራ የሚል የባርነት ማንነት ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ ጋር ፈጽሞ የተጣላ መሆኑን ያልተገነዘቡት ቀዳማዊ ሃይለስላሴና በዙሪያቸው የነበሩት እንደ አክሊሉ ሃብተወልድ ያሉ ፖለቲከኞች በአካል ድል የነሳነውን የቅኝ ገዢዎች መርዝ የቅኝ አገዛዝ ስሪታቸው በሆኑትና የኢትዮጵያዊነት የነጻነት መንፈስ ብል በሆኑት ኤርትራዊያን ተባዮች በኩል ጎትተው በማስገባት ሃገር አልባ ያደረገንን ታሪካዊ ቀይ ስህተት ባለማወቅና በየዋህነት ፈጽመዋል::
(የባሮን ፕሮቻስካ የጥላቻ መጽሃፍ ህትመትን ተከትሎ ባሮን ሮማን ፕሮቻዝካ በኢትዮጵያ መንግስት ከሃገር እንዲባረር መደረጉን ለአንባቢ ልንገልጽ እንወዳለን::)
የቀድሞው የኤርትራ አስገንጣይ ቡድን ጀብሃ ተላላኪ የነበረው ቅጥረኛው ዋለልኝ መኮንንና ኦስትሪያዊው የናዚ ፓርቲ አባልና የፋሽስት ሞሶሎኒ ደጋፊ የነበረው ባሮን ፕሮቻዝካ ኢትዮጵያዊነት ውሸትና የአማራው ፈጠራ ነው ሲሉ የሰበኩባቸው ጽሁፎች፥
ንጽጽሩን በዋለልኝ መኮንን የፋሺስት ፕሮፓጋንዳ ቅጂ ጽሁፍ እንጀምር:-
“የብሄር ትርጉም ከዚህ ውጪ ምንድን ነው? የራሱ የሆነ ቋንቋ፣ አለባበስ፣ ታሪክ እንዲሁም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አደረጃጀት ያለው ህዝብ ማለት አይደለምን? ይህ ከታወቀ ዘንዳ በኢትዮጵያ ውስጥ የኦሮሞ ብሄር፣ የትግሬ ብሄር፣ የአማራ ብሄር፣ የጉራጌ ብሄር፣ የሲዳማ ብሄር፣ የወላይታ ብሄር፣ የአደሬ ብሄር፣ እንዲሁም የቱንም ያህል ቢያስከፋችሁ የሶማሌ ብሄር መኖሩን ልገልጽ እወዳለሁ፡፡ ይህ ነው የኢትዮጵያ እውነተኛ ገጽታ፡፡ እርግጥ ነው ኢትዮጵያዊነት የተሰኘ በአማራው ገዥ መደብ አማካኝነት በሌሎች ብሄሮች ላይ ያለፍላጎታቸው በሃይል የተጫነ፣ በነዚህ ጭቁን አካላት ሳይቀር በየዋህነት የተገፋ የፈጠራና የውሸት ብሄራዊ ማንነት አለ:: ይህ ኢትዮጵያዊነት የተሰኘ የፈጠራ ብሄራዊ ማንነት ምንድን ነው? በቀላሉ የአማራው የበላይነት ማለት አይደለምን?”
( ዋለልኝ መኮንን ካሳ፤ “Struggle Magazine” ፤ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ፤ ህዳር 9፣ 1961 ዓ ም)
ለፋሺስት ጣሊያን የአምስት አመታት አገዛዝ እንደ መመሪያና “ማንዋል” ያገለገለው በጣሊያንኛ ትርጉሙ “አቢሲኒያ ፔሪኮሎ ኔሮ”(ABISSINIA PERICOLO NERO) ወይም “አቢሲኒያ ጥቁር አደጋ” የተሰኘው ኦሪጅናሉ የባሮን ፕሮቻዝካ ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ መጽሃፍ ውስጥ ሰፍሮ የሚገኘው ሃሳብ እንደሚቀጥለው ይነበባል፥
“አንድ የሆነ አቢሲኒያዊ ህዝብ የሚባል ነገር የለም:: ክርስቲያን ያልሆኑት አብዛኞቹ የአቢሲኒያ ጎሳዎች ከአማራ ጭቆና እንደመላቀቅ የሚመኙት አንገብጋቢ ነገር የለም:: እነዚህ ከአናሳው የአማራ ጨቋኝ ጎሳ በቋንቋ፣ በባህልና በሃይማኖት የሚለዩት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ህዝቦችና ጎሳዎች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ቢሰጣቸው ኖሮ የአማራን የጭቆና ቀንበር ድሮ ገና አሽቀንጥረው በጣሉት ነበር:: ከዚህ ይልቅ ከአውሮፓዊያን ተጽእኖና ተራማጅ የአውሮፓ ቅኝ አገዛዝ ለሃገሪቱ ሊያመጣ ከሚችለው ጥቅሞች በአማራው ጎሳ አማካኝነት በሃይል እንዲነጠሉ ተደርገዋል:: ”
(“Abyssinia the Powder Barrel” by Baron Roman prochazka published in 1934.)
ፕሮ ቻዝካ ኢትዮጵያን በጎሳ ላይ ተመስርቶ ለመበታተን አውሮፓውያንን የጎተጎተበትን ምክንያት ከላይ በተጠቀሰው መጽሃፉ ውስጥ ሲያስረዳ እንደሚከተለው ይላል፥
“የዚህ ሃገር(የኢትዮጵያ) መንግስት በአለም አቀፍ ውሎችና ስምምነቶች ስር የተገቡ ግዴታዎች እንዳይሟሉ በረቀቀ ሴራ እያሰናከለ እንደሆነና ህዝቡም አለም በገሃድ በሚያውቀው የፈረንጅ ጥላቻቸውና በተጋነነ ብሄራዊ ንቃታቸው እየተገፉ የአለም ጥቁር ህዝቦችን በሙሉ ያቀፈና ያሳተፈ የጦር ግምባር በአብሲኒያዊያን አመራር ስር በማደራጀት በነጭ ዘር ላይ ሁሉ አቀፍ ጥቃት ለመሰንዘር አዲስ ኢትዮጵያዊ እንቅስቃሴ እያጧጧፉ እንደሆነ ለማሳየት እፈልጋለሁ:: የአቢሲኒያዊያን ጸረ ነጭ ፖሊሲ የመጨረሻ ግብ ከጃፓን ጋር ግንባር በመፍጠር የአፍሪካ ጥቁር ህዝቦች በሙሉ አዳኝ ሆኖ መውጣት ነው:: በአቢሲኒያ ውስጥ የሚገኙ የስልጡን ሃገራት ቆንጽላዎች አቢሲኒያዊያን የምእራባዊያንን ባህልና ስልጣኔ ጥቃት ከፍተው ከናካቴው ከማውደማቸው በፊት መንግስታታቸውን የማያወላውል ጠንካራ አቋም እንዲወስዱ የማስጠንቀቅ ግዴታ አለባቸው::”
(“Abyssinia the Powder Barrel” by Baron Roman prochazka published in 1934.)
የፋሺስት ፕሮፓጋንዲስት የነበሩት ፕሮፌሰር ራፋኤል ዲ ላውሮ በበኩላቸው ኢትዮጵያን በጎሳ ላይ ተመስርቶ በመከፋፈሉ ተግባርና በአማራው (በተለይም በሸዋ አማራ)የነጭ ጠላትነት ዙሪያ እንዲህ ብለው ይጽፋሉ:-
“በጎሳ ላይ ተመስርተው ለተቋቋሙት አምስት ክልሎች የመንግስት መቀመጫ ምርጫና የድንበር ማካለሉ ስራ የተከናወነው ፖለቲካዊ ጥቅሞችንና ተፈላጊ ውጤቶችን ሊያስገኙ የሚችሉ ግልጽ የሆኑ ፖለቲካዊ መመዘኛዎችን ተከትሎ ነው:: ህግ አውጪው አካል አንድ አይነት ቋንቋ፣ጎሳና የታሪክ ማንነት ያላቸውን የኢትዮጵያ ህዝቦች በአንድ መንግስት ስር የማጠቃለል መርሃችንን በሚገባ ተከትሎ ተግባራዊ አድርጓል:: የእነዚህ የኮሎኒያል ግዛቶቻችን ድንበር አከላለል በግልጽ እንደሚያሳየው የፋሺስት ህግ አውጪዎች በኢትዮጵያ ያለውን ፖለቲካዊ ሁኔታ፣ የሃገሪቱን ያለፉት አንድ መቶ አመታት ታሪክ የሚወክሉ የተለያዩ ኩነቶችንና ህዝቦችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአትኩሮትና በጥንቃቄ ሰርተዋል:: የሸዋው መንግስት መገለጫ የሆነው በሌሎች የጫፍ ሃገር ህዝቦች ኪሳራ ሃገሪቱን የማማከል ዝንባሌ በሁሉም ዘንድ የታወቀ ነው:: ሸዋዎች ባጠቃላይ ለአውሮጳዊያን በተለይ ደግሞ ለጣሊያኖች ያላቸው ከፍተኛ ጥላቻ በደንብ የሚታወቅ ነው:: የቅኝ ግዛቶቻችንን ለማደራጀት ወይም ለማካለል የተጠቀምንበት መሰረታዊ ህግ (Legge Organica) በንጉሱ ዘመን የሁሉም ጸረ ጣሊያን እንቅስቃሴዎች ማእከል የነበረውን የሸዋን ግዛት ዛሬ ሸዋ የሚባል ግዛት በህልውና እንዳይኖር(ከካርታ ላይ እንዲነሳ)በተደረገበት ደረጃ ስሙን ጭምር በማጥፋት ይህን የሸዋ እባጭ(‘bubbone Scioano’) ማፍረጥ ችሏል::”
የወያኔ ትግሬ መንግስት ላለፉት 23 አመታት የአማራን ህዝብ ሰብአዊ ፍጡር ሳይሆን እንደ አንድ ሊጠፉ የሚገባው አደገኛ አውሬ አድርጎ ለመሳልና የተደራራቢ ቅጣት ሰለባ ለማድረግ የቻለበት መደላድል የተፈጠረው እንዲሁ ከምንም ተነስቶ አልነበረም:: የአማራው የገዛ ልጆች በቀንደኝነት የተሳተፉበት ለብዙ አስርተ አመታት ሲንከባለል የመጣና የተከማቸ የአማራን ማንነት የማጠልሸትና የማስነወር ተግባር ውጤት ነው:: የአማራውን ህዝብ ነጥሎ የማጥላላትና ማንነቱን የማጠልሸት ፕሮፓጋንዳ የተጀመረው እስከ ዛሬው እለት ድረስ “የኢትዮጵያዊነት ስሜት (የኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ስሜት) የሌለውና የተከፋፈለ” በማለት መጥራትን በመረጡት የኢትዮጵያ ህዝብ የተባበረ ክንድ በአድዋ ጦርነት የደረሰባቸውን ከፍተኛ ውርደት ተከትሎ ከተሳሳተ አረዳድ በመነሳት ኢትዮጵያዊነትን ከአማራው ማንነትጋር ለማያያዝ በሞከሩ የጣሊያን ቅኝ ገዢዎች አማካኝነት ነበር:: ይህን በታላቁ ንጉስ አጼ ሚኒሊክ በሳል አመራርነት በኢትዮጵያ ህዝብ የተባበረ ክንድ የደረሰባቸውን አሳፋሪ ሽንፈት ተከትሎ ነው እንግዲህ ፋሺስት ጣሊያኖች አማራውን የጥቃት ኢላማ ማድረግ የጀመሩት:: የጣሊያናዊያን ኮሎኒያሊስት የስነጽሁፍ ውጤቶች አማራውን ጭራቅ አድርገው በሚስሉ ፕሮፓጋንዳዎች የታጨቁ ናቸው:: በዚህ አጋጣሚ እንደ ፔትሮ ባዶግሊዮ፣ አልቤርቶ ስባቺ፣ አንጄሎ ዴልቦካ፣ አንቶኒ ሞክለር ወዘተ ባሉ የጣሊያን ምሁራኖች አማራውን በተመለከተ የተጻፉ መጽሃፍትን ጉዳዩን በጥልቀት ለመረዳት ይረዳ ዘንድ ለአንባቢ እጠቁማለሁ:: የወያኔ ትግሬ መንግስት በ 5 አመቱ የፋሺስት ጣሊያን ወረራ ወቅት ጠላት በኢትዮጵያ ላይ ለመጫን የሞከረው የጎሳ ብሄርተኝነት አቀንቃኝ እንደመሆኑ መጠን ኢትዮጵያዊነትን(የኢትዮጵ
ያ ብሄርተኝነትን) በጠላትነት ፈርጆ ለማጥፋት በጽኑ ተንቀሳቅሷል:: በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ ከተሳሳተ ስሌት በመነሳት የአማራውን ህዝብ የኢትዮጵያዊነት ብቸኛ ተቆርቋሪና አቀንቃኝ አድርገው በመነጠል እንደ ፋሺስቶች ሁሉ የጥቃት ኢላማ አድርገውታል:: ይህ የኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ብቸኛ አቀንቃኝ አማራው ነው የሚለው መሰረት የለሽ አተያይ ፋሺስት ጣሊያኖችን ብቻ ሳይሆን በ1997 ዓ.ም. ግንቦት ወር አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በጎሳ ላይ የተመሰረተን ፖለቲካና የአናሳው የወያኔ ትግሬን የጎሳ አፓርታይድ ስርአት በመቃወም ባልጠበቁት መልኩ አደባባይ ወጥቶ በማየታቸው ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረባቸው እንደ ወያኔና መድረክ ያሉ የጎሳ ብሄርተኛ ቡድኖችን ጭምር ያሳሳተ አረዳድ ነው:: አጼ ሚኒሊክ በታሪካችን ወደር በማይገኝለት የአመራር ብቃት የጣሊያን ፋሺስት ወራሪዎችንና የኤርትራ አሽከሮቻቸውን ጦር በአድዋ ጦርነት ድባቅ በመምታት አሳፍረው በመመለስ ኢትዮጵያን በአለም ጭቁን ህዝቦች የነጻነት ጮራነት የአለም ካርታ ላይ ለማስቀመጥ የመላው ኢትዮጵያ ህዝብን ታማኝነትና ትብብር መጎናጸፍና አንድ አድርገው ለአንድ ሃገራዊ አላማ ማንቀሳቀስ የመቻላቸውን እውነታ ለመካድ ወይም ላለመቀበል ጣሊያኖች በኮሎኒያሊስት ጽሁፎቻቸው ውስጥ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ላለመጠቀም በመወሰን በምትኩ አቢሲኒያ(አቢሲኒያ ማለት የዛሬው ሰሜናዊ ኢትዮጵያ ማለት ነው) የሚለውን ቃል በመጠቀም መቀጠልን መርጠዋል:: የፋሺስት ጣሊያን ከፋፋይ የጎሳ ርዕዮተ አለም አራማጅ የሆነው የወያኔ ትግሬ ቡድን እንደ ጣሊያኖች ሁሉ አማራውን የኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ቀንደኛና አክራሪ አቀንቃኝ አድርጎ በመፈረጅ በነገዱ ላይ የኢኮኖሚያዊ ስነልቦናዊና አካላዊ ሁለንተናዊ ጦርነት በመክፈት ከምድረ ገጽ የማጥፋት እኩይ አላማውን እየገፋበት ይገኛል::
በዘመነ ኮሎኒያሊዝም ፋሺስት ጣሊያኖች የኤርትራዊያን ቅኝ ተገዦቻቸውን አእምሮ የዛሬው የኤርትራዊያን ማንነት ዋነኛ መገለጫ በሆነው የአማራ ጥላቻ መመረዝ ችለዋል:: የኤርትራዊነት ማንነት በጣሊያን ጌቶቻቸው አማካኝነት ለኤርትራዊያን የተሰጠ የሚኮሩበትና ለሰላሳ አመታት ያህል “ከኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት” በሚል ደማቸውን እስከማፍሰስ የደረሱለት አዲስ የባርነት ማንነት ነው:: ዛሬ ይህ ተገኘ የተባለው “የኤርትራ ነጻነት” ኤርትራዊያን የአንድ ወቅት ተወዳጅ መሪያቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ጥሰው ለማለፍ የሚሞክሩ ስደተኞች በጥይት እንዲቆሉ የሚደነግግ ፖሊሲ ባጸደቀበት የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ላይ ቆመው ፖሊሲውን ያለማንገራገር በሚገባ እያስፈጸሙ የሚገኙ ታማኝ ወታደሮቹን መአት በተአምር እያመለጡ ወደቀድሞ “ቅኝ ገዣቸው” ኢትዮጵያ በገፍ የሚነጉዱበት “ንጻነት” በመሆን ተደምድሟል:: ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በተዋሃደችበት ማግስት አማራውን የጥላቻ ኢላማ አድርገው የተነሱት የዚህች የቀድሞዋ የጣሊያን ቅኝ ተገዥ ኤርትራ የተማሩ ልጆች ነበሩ:: “የአማራ መንግስት” በሚሉት የሃይለ ስላሴ ስርአት ለተቀሩት የኢትዮጵያ ግዛቶች በተለይ እነሱ በስርአቱ ተጠቃሚነት በሃሰት ለሚወነጅሏቸውና በተማሪው እንቅስቃሴ ውስጥ በአብዮታዊ ተራማጅነት ስም የጸረ አማራ የጥላቻ አመለካከታቸውን ለመግፋት በመሳሪያነት ለተጠቀሙባቸው፣ ባብዛኛው የአማራ ተወላጆች ሰፍረው የሚገኙባቸው ለመሃልና የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች የተነፈጉ፣ በሃገሪቱ ምርጥ የሚባሉ በጥራትና በብዛት እጅግ የላቁ የትምህርት ተቋማት ተገንብተውላቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ በመደረጋቸው የወቅቱን የሃይለ ስላሴ ዩኒቨርሲቲ በገፍ መቀላቀል የቻሉት የኤርትራ ብሄርተኞች ነበሩ:: በግዜው የተራማጅነት ጭምብልን አጥልቀው የነበሩት የትግሬ ልሂቃንም እንዲሁ በማርክሲዝም ርዕዮተ አለም ስም የጸረ አማራ አመለካከትን ማስፋፋት ችለው ነበር:: ይህ የተራማጅነት ጭምብል ባለፉት 23 አመታት ዛሬ “ጉዳዬ ሞላ” የሆነላቸው የትላንቶቹ ተራማጅ ትግሬዎች (የኢህኣፓ፣ የመኢሶን፣ የኢሰፓ አባላት የነበሩ)ያለአንዳች ይሉኝታ ከፋሺስቱ የወያኔ ትግሬ መንግስት ጋር መሰለፍን በመረጡበት ወቅት ሙሉ ለሙሉ ሊጋለጥ ችሏል:: ምክንያቱም የትግራይ ተወላጆች በወቅቱ ይታገሉለት የነበረው አላማ የሃገሪቱን ህዝቦች በእኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ ዴሞክራሲያዊ ስርአትን ለመገንባት ሳይሆን የአማራን መንግስት ለመጣል ነበር:: ያልጠረጠሩት የዋህ የአማራ ተራማጆች ደግሞ ይህ የተማሪው እንቅስቃሴ የጸረ አማራ ስብከትና ነጋሪት ጉሰማ በወቅቱ ወዴት እያመራ እንደነበረ ለማወቅ የሚያስችል ግንዛቤ አልነበራቸውም:: ቢያንስ ባለፉት 58 አመታት ውስጥ የአማራው ወጣት አማራውን በጨቋኝነት፣ በደም መጣጭነት፣ በነፍጠኛ ወራሪነት ወዘተ የሚወነጅል ልብወለድ ያለመታከት በመሰበኩ ትክክል ነው ብሎ ተቀብሎ ከማንነትቱ ጋር እንዲያዋህዳቸው ተደርጓል:: ነፍጠኛ የሚለው ቃል ብሄርተኞች አማራ ለማለት የሚጠቀሙበት ምትክ የ“ኮድ” ቃል ሲሆን ምንም እንኳን በግዜው ብዙ ነፍጠኞች አማራ የነበሩ ቢሆንም ነፍጠኝነት ከአንድ ጎሳ ማንነት ጋር የተያያዘ ባህሪ እንዳለመሆኑ መጠን አንድን የኢትዮጵያ ጎሳ ብቻ ሊወክል እንደማይችል ከሚቀጥለው ምሳሌ መረዳት ይቻላል:: ኢትዮጵያዊው የታሪክ ምሁር ሽፈራው በቀለ በዚህ ርዕስ ዙሪያ በሲዳሞ ክፍለ ሃገር ሰፍረው የነበሩ ነፍጠኞችን አስመልክቶ የማክሌላንን “State Transformation & National Integration: Gedeo and the Ethiopian Empire”, East Lansing, Michigan 1988)የተሰኘ መጽሃፍ ጠቅሰው የሚከተለውን ምልከታ አድርገው ነበር:
“ማክሌላን በናሙናነት የወሰዳቸው ሰፋሪዎች በሰጡት መረጃ መሰረት የእያንዳንዳቸው የጎሳ ተዋጽኦ ከመቶ እጅ ምንያህሉን እንደሚይዝ የሚያሳይ አሃዝ የጦር አበጋዞች፣ ተራ ወታደሮች፣ ሲቪሊያኖች በሚል ከፋፍሎ እንደሚከተለው አስፍሮልናል(እኛ አጠቃላይ የጎሳ ተዋጽኦ አሃዙን እንመለከታለን):- ሸዋ 69%፣ ጎጃም 12.05%፣ ወሎ 5%፣ ትግሬ 4%፣ በጌምድር 2.03%፣ እና ሌሎች 7.5%:: ለሸዋ የተሰጠው አሃዝ ሸዋ ኦሮሞዎችን፣ አማሮችን እንዲሁም ጉራጌዎችን የሚያካትት እንደመሆኑ የተፈለገውን የጎሳ ተዋጽኦ ምስል አይፈጥርም:: ለምሳሌ ያህል በሲዳሞ ሰፍረው ከነበሩ ሰፋሪዎች ውስጥ በዛ ያለ እጅ የሚይዙት በአብዛኛው ኦሮሞና ጉራጌ የነበሩ የደጃች ባልቻ አገልጋዮችና ወታደሮች ናቸው:: ስለዚህ የሸዋ አማራ ተወላጆች ተዋጽኦ እዚህ ሰፍሮ ከሚገኘው አሃዝ እጅግ ያነሰ መጠን እንደነበረው ጥርጥር የለውም::” (ለዝርዝሩ, የፕሮፌሰር ሽፈራውን: “An Economic History of Ethiopia” የተሰኘ መጽሃፍ ገጽ 104ን ይመልከቱ)።
ስለዚህ በአዝጋሚ ሁኔታ ነገር ግን በእርግጠኝነት የአማራው ወጣት የነገዱን በጎ ታሪክና አስተዋጽኦ በማደብዘዝ ከማንነቱ ጋር እንዲያያዙ የተደረጉና የወቅቱ የነገዱ መገለጫ ለመሆን የበቁ እንደ ነፍጠኛና ሌሎችም በጥላቻ የታጨቁ ማጥላያዎችን እንዲቀበልና እንደ መጥፎ ነገር እንዳይመለከት ተደርጓል:: ይህ የአማራው ወጣት ለረጅም ዘመን ሰለባ የተደረገበትና እራሱ ዋነኛ የማራጋቢያ መሳሪያ በመሆን የሚገፋው አዝጋሚ ጸረ አማራ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ውርጂብኝ የአማራውን ወጣት በተለይ ተማረ የሚባለውን ልሂቅ ማንነትን አበሻቅጠውና አጨቅይተው የሚያስነውሩ፣ በነገዱ ላይ የሚወረወሩ ርካሽና ጸያፍ የጥላቻ ቅጽላዎችን አሜን ብሎ በተቀበለበት ደረጃ እንዲዘቅጥ አድርጎታል:: ይህ ለረጅም ዘመናት በተሰላና በተቀነባበረ መልኩ የተገፋው የአማራውን ህዝብ ማንነት የማስነወር አዝጋሚ ሂደት በግዜ እየተከማቸና እየተደራረበ መጥቶ ሰለባ ያደረጋቸውን የአማራ ተወላጆች ከጎሳ ማንነታቸው ጋር የተሰፉላቸውን የሃሰት የስም ማጥፊያ ስያሜዎች በሙሉ ትክክል ነው ብለው የተቀበሉበት ደረጃ ላይ አድርሷቸዋል:: ዛሬ የዚህ ትውልድ አባል የሆነው የአማራው ልሂቅና ወጣት አማራው በታሪክ ኢትዮጵያ ላይ ለደረሱ ውድቀቶች ሁሉ ተጠያቂ መሆኑን አምኖ በመቀበሉ ከተከፈተበት ማንነቱን የወንጀለኝነትና የአረመኔነት ገጽታ የሚያላብሱ የፕሮፓጋንዳ ጦርነቶች እራሱን ለመከላከል ሙሉ በሙሉ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል::
ዛሬ አማራው እራሱን መከላከል በማይችልበት ደረጃ እንዳይላወስ ተደርጎ ስነልቦናው ሽባ የተደረገበት ሁኔታ የስነ አእምሮ ምሁራኖች በእንግሊዘኛው “ኢንተርናላይዜሽን” (Internalization) በማለት የሚገልጹት የስነልቦና ለውጥ ሂደት አይነተኛ መገለጫ ነው:: ይህ ሂደት የአማራው ልሂቅ በጠላቶቹ የተጫነበትን አሉታዊ የማንነት መገለጫዎችን እንዲቀበል የተደረገበትን ምክንያት ይገልጽልናል:: የሚሰራው ነገር ሁሉ መጥፎ እንደሆነ በወላጆቹ ወይም በአሳዳጊዎቹ ዘወትር የሚነገረውና ሁሌ ግዜ የሚገረፍ ልጅ በግዜ ሂደት የእውነትም መጥፎ ልጅ እንደሆነ ማመን ይጀምራል:: በተመሳሳይ ሁኔታ ሰዎች ምንም እንኳን ስብእናቸውን የእውነት የማይገልጹ ቢሆኑም በተደጋጋሚ ከሌላ አካል ለሚሰነዘሩ ማንነታቸውን ጥላሸት የሚቀቡ ዘለፋዎች ተጋላጭ ሲደረጉ በሂደት እነዚህን ዘለፋዎች ትክክለኛ የማንነታቸው መገለጫዎች አድርገው መቀበል ይጀምራሉ:: “ኢንተርናላይዜሽን” በማለት የምንጠራው እንዲህ ያለውን አሉታዊ የስነልቦና ለውጥ ሂደት ነው:: ወደ አማራው ልሂቅና ወጣት ስንመለስ ደግሞ ማንነቱ በደም መጣጭነት፣በጡት ቆራጭነት፣ በበዝባዥነት ፣ በባሪያ ፈንጋይነት፣ በወራሪነት ወዘተ አሉታዊ ገጽታዎች የተተካበትን ሁኔታ አሜን ብሎ የተቀበለበትን ሂደት ያስረዳልናል:: በዚህ አይነት ዛሬ ከ23 አመታት የወያኔ ትግሬ ናዚያዊ አገዛዝ በኋላ የአማራው ህዝብ እራሳቸውን “የጭቁን ጎሳዎች ተወካይ” ብለው በሚጠሩ፣ የአማራውን ምስኪን ገበሬ እንዳሻቸው መስደብ፣ ማዋረድ፣ለከፋ እንግልት መዳረግ፣ ማፈናቀል፣ ማሳደድ፣ መጨፍጨፍ የሚያስችል መብት ባለቤቶች እንደሆኑ በሚሰማቸው የጥላቻ አሻሻጭ ብሄርተኞች የሚተላለፍበትን ማንኛውም አይነት ፍርድ ያላንዳች ይግባኝ መቀበል የሚገባው ከሰብአዊ ፍጡርነት በታች ወርዶ እንደ አውሬ እንዲታይ የተደረገና ህልውናው ከፍተኛ ጥያቄ ውስጥ የገባ ማህበረሰብ ለመሆን በቅቷል:: ምክንያቱም እንዲህ እንደ አደገኛ አውሬ እንዲቆጠር የተደረገ እንደ አማራው ያለ ማህበረሰብ ምንም አይነት የዜግነት መብት ስለማይኖረው እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ሊደረግለት የሚገባው አይሆንም:: ስለዚህ የአማራው ህዝብ በደል የሚገባውን ያህል አትኩሮት አለማግኘቱ የሚያስገርም ነገር አይደለም:: በአንድ ወቅት ብቻ 78,000 አማሮች ከደቡብ ኢትዮጵያ ሃብት ንብረታቸውን ተነጥቀው አራስ ልጆቻቸውን እንደያዙ ሲባረሩ አብዛኞቹ ነጻ ሚዲያዎችና ድህረ-ገጾች ለጉዳዩ የሚዲያ ሽፋን ላለመስጠት የወሰኑበት ክስተት እዚህ ጋር ተጠቃሽ ነው:: በዚህ አይነት እንደ ብሄራዊ ጨቋኝነት፣ ደም መጣጭነት፣ ወራሪነት፣ ስግብግብ በዝባዥነት፣ ተስፋፊነት፣ጨፍጫፊነት፣ ጡት ቆራጭነት ያሉ አሉታዊ ታሪኮች ውጪ በጎ አስተዋጽኦ ለሌለው አረመኔ ማህበረሰብ ስቃይና መከራ የሚቆረቆርና ግድ የሚለው ሰው አይኖርም:: በተመሳሳይ እንደ ወያኔ ባሉ የጎሳ ብሄርተኞች የጥላቻ ስብከት ማንኛውም አይነት ሃዘኔታና ርህራሄ የማይገባው አውሬ ሁኖ እንዲታይ የተደረገው አማራ ዛሬ በጎሳ ልሂቃኖች፣ የብሄርተኛ ድርጅቶች ደጋፊዎችና የአማራውን መበደል እንደ አንድ የተለመደ ተራ ነገር የቆጠሩት የራሱ የአማራ ልሂቃኖች ጭምር በቂም በቀል፣በጥላቻና፣ በቸልተኝነት ስሜት መታየቱ የሚያስገርም ነገር አይሆንም::
ሰሞኑን በECADF ፓልቶክ ክፍል ውስጥ አንድ ነጠላ ዘፈን ተለቆ ነበር።
የድምጽ ቀራጯም በፓልቶክ ስሟ ሙያዬ ምስክር ተብላ የምትጠራ ሲሆን ትክክለኛ ስሟ ሙሉ ወንድም አገኘሁ ይባላል።ይቺ ሴት የአማራዎች ከጉራፋርዳ መፈናቀል ያስከተለው የአማራ ብሄረተኝነት መነቃቃት ክፉኛ ካስደነገጣቸው የግንቦት ሰባት አጨብጫቢዎች ዋናዋ በመሆኗ ነው።አማራ የሚባል ዘር የለም እስከማለት ርቀት ሄዳ እሷና መሰሎቿ በሚቆጣጠሩት ፓልቶልክ ክፍል ውስጥ እንደነፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪኣምና ነብሳቸውን ይማረውና ዶክተር ማይገነት አይነቶቹን እንግዶች እየጋበዘች የአማራን ህልውና የክህደት መልክቷን ለመሸጥ በጣም ጥራ የነበረ ቢሆንም ቅሌትን ከማትረፍ ውጪ ምንም ሳታተርፍ በመቅረቷ ተልኮዋን ባለማቋረጥና ማሳደዷን በመቀጠል፤የአማራው በሃገሪቷ አራቱም ማእዘን መሳደድና መገደል ቁጭት የወለደውን ሞረሽ ወገኔን ማብጠልጠሉን ስራዬ ብላ ለረጅም ጊዜ ተያይዛዋለች፤የዚሁ የጠላትነቷ ጉዞ ቀጣይ የሆነው አካል ነበር በሷ አጠራር “አርበኛ”ነዐምን ዘለቀን ጋብዛ መነሻውን ስለሰሞኑ የወያኔና የሻቢያ አደናጋሪ ግርግር ጉዳይ ጠይቃው እሱም ለሻቢያ ያለውን የታማኝነት ጥልቀት ሲደሰኩር ውሎ በመቀጠልም የዚሁ ኢንተርቪው ዋናው አካል የሆነው በመጨረሻ የጠየቀችው ጥያቄ ነበር አስገራሚው ጉዳይ።ያም ጥያቄ ከታች የለጠፍኩት የግንቦት ሰባት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የዘር ስብጥርን አስመልክቶ በአሽሙር መልክ እንዲያውም “አሉባልታ”የሚል ስም ሰጥታው፤”እውነት ነወይ ግንቦት ሰባት የደቡቦች ነው”እየተባለ በአማራ ስም የተደራጁ ቡድኖች የተሰጠው ስም ብላ ነበር የጠየቀችው፤እሱም ያው ታውቁታላችሁ የፈለገውን እንዲናገር ተፈቅዶለት ተሞላቆ ያደገ ልጅ ነበር መሰለኝ አንዳንድ ጊዜ አደባባይ ላይ መውጣቱን ይረሳውና የሚሳደባቸው ስድቦች እንደሱ ላሉ ሊሸከማቸው የማይችላቸውን ስልጣናት ተሸክሞ የማይገባና ጸያፍ በሆነ ቃል ነበር የሞረሽን ሰዎች ሲዘልፍ የተስተዋለው።
እታች የተገለጹት የድርጅቱ ስራ አመራሮችን ከአማራ የጸዳ ነው መባሉን ሽምጥጥ አድርጎ ክዶ ለምሳሌነት ስለራሱ ሲናገር እናቴ ሙሉ በሙሉ አማራ ነች ብሎ ሲል ጠያቂዋም እናቱን እንደምታውቅ ነግራው የእምነት ክደት ትርእይቱ ተባባሪ ለመሆን ሞክራለች።በመቀጠልም “አርበኛ”ነዐምን አባቱም ባባቱ አባት ወገን ነው እንጂ ኦሮሞነቱ በእናት አማራ እንደሆኑና እንዲያውም ሃረር ውስጥ ነፈጠኛ ቤተሰብ ተብለው ከሚጠሩ ወገኖች አካል እንደሆኑና እሱም የአማራው ጎኑ ተደምሮ ሲቀነስ 3/4ኛ እንደሆነ ደስኩሮልናል።”የሰውን ማንነት ለማወቅ ከፈለግህ ከነማን ጋር እንደሚውል ካየህ ወይም ከረጅም ንግግሩም ጭምር ተነስተህ ልትረዳ ትችላለህ”እንዳለው ብሂሉ፤አባቱም ኮማንደር ዘለቀ በኤርትራ ውስጥ 40 አመት በኢትዮጵያ ባህር ሃይል አዛዥነት እንደሰሩ ነግሮናል።ሁላችንም እንደምናውቀው ባህር ኋይሉ ባሳፋሪ ሁኔታ በሻቢያ ተዋርዶ ተደምስሷል።ታዲያ የኝህ ሰው ልጅ ለሻቢያ እንዲህ የሚያንገበግብ ፍቅር ከምን የመነጨነው የሚል ጥያቄ አጫረብኝ።ነገሩ ግር የሚያሰኝ ብቻ ሳይሆን ለማንም ራስ የሚያሳክክ ነገር ነው።
አባቱ የኢትዮጵያን ባህር ሃይል አዛዥ ሆነው 40 አመት ሙሉ ሻቢያን ሲያስጨንቁ ነበር ወይስ ሲጨነቁለት ነበር የኖሩት የሚል ጥያቄም ያስነሳል። ምክንያቱም ሁላችንም እንደምናውቀው ኢሳያስ አፈወርቄ የሚባል ሰው በጣም ቂመኛ ሰው እንደሆነና እንኳን የኢትዮጵያ ወታደር አዛዥ ሆኖ ሲያስወጋው የኖረን መኮንን ቤተሰብ ይቅርና ከአማራ ተራ ወታደርና ከኤርትራዊት ሴት የተወለደችን የ2 አመት ህጻን ልጅ ከነእናቷ ጋር ከኤርትራ መሬት ያባረረና ይህንንም ትእይንት በዚያን ወቅት የአለም ቀይ መስቀል ጉድ ብሎ የዘገበው ጉዳይ ከመሆንም ባሻገር፤የኤርትራና የትግሬ ዝርያ የሌላቸውን ምርኮኛ ወታደሮች በሙሉ እጃቸውን በሰላም ከሰጡ በኋላ እረባዳ ቦታ አስወስዶ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ዜጎቻችንን በአሰቃቂ ሁኔታ ያስረሸነ አረመኔን ሰው ፍቅር ነዐምን የኮማንደር ዘለቀ ልጅ በምን ድግምት አገኘው?ይህን ጥያቄ አንባቢውም ይወያይበት።
“አርበኛ” ነዐምን ትረካውን በመቀጠል ስለብርሃኑ ነጋ ጉራጌነት ነገረንና የሌሎቹን አድበስብሶ ነው ያለፈው፤አልጨረሰውም፤ስለዶክተር ታደሰ ብሩ፤ስለሙሉነህ እዩኤል፤ስለ የምኒሊክ ተሳዳቢው ኤፍሬም ማዴቦ ምንነት አልነገረንም።
እነዚህ ሰዎች አይደሉ እንዴ ቁልፍ የግንቦት ሰባት አመራሮች?እኛ ችግራችን የደቡብ ሰውነታቸው አይደለም፤ችግሩ ዘረኝነታቸው ነው።እኔ የዚያ ፓልቶልክ አድሚን በነበርኩ ጊዜ አንድ የተከሰተ ነገር ልንገራችሁ፤እሁድ ቀን ይመስለኛል ውይይት እያካሄድን እያለን አንድ ታዳሚ ማይክ ያዘና ሎሳንጀለስ ከተማ ውስጥ አንድ አስቂኝም አስደንጋጭም ክስተት መከሰቱን ነገረን፤ነገሩም እንዲህ ነው:
የሎሳንጀለስ አካባቢ የግንቦት ሰባት አባላት ስብሰባ ተጠርተው ውይይት ከተጀመረ ከኋላ ድርጅቱን የሚመሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ቤቱ እንዲመርጥ ለስብሰባው ጠሪዎች ከተሰብሳቢው ጥያቄ ሲቀርብላቸው፤ምርጫው ከስብሰባው በፊት እንደተጠናቀቀ ስብሰባ ጠሪዎቹ ይናገራሉ፤ታዳሚውም መልሶ ማን መረጣቸው ብሎ ላነሳው ጥያቄ መልሱ አጭርና ግልጽ ነበር “የበላይ አካል የድርጅት ክፍል ሃላፊ”የሚል ነበር መልሱ፤ያ ሰው ደግሞ ሙሉነህ እዩኤል ነበር፤የሚገርመውና አይናችንን ያበራው ጉዳይ በበላይ አካል ተወክለዋል የተባሉት ሁሉም የደቡብ ተወላጆች መሆናቸው ነበር።ማይክ ይዞ ይህንን ፈንጂ ያፈነዳውን የሎስንጀለስ ልጅ እነሙያዬ አስቆሙትና ከክፍሉ አስወጡት።በዚያ ጉዳይ ላይ ቤቱም እንዲወያይ አልተፈቀደለትም ነበር።ከዚን ጊዜ ወዲህ ያ ጦሰኛ ልጅ ወደዚያ ክፍል አልተመለሰም በቋሚነት ታግዷል(ባን ይሉታል በእንግሊዘኛ)።
ይህ ፖልቶክ ክፍል ማለትም ECADF ለግንቦት ሰባት ከኢሳት ቴሌቪዥን የማይተናነስ አገልግሎት የሚሰጥና አብዛኞቹ የድርጅቱ አባላት የሚታደሙበት ክፍል በመሆኑ ያ ክስተት ትልቅ አቧራ በማስነሳቱ እነ ብርሃኑ ነጋ ተደናግጠው ሙሉነህ እዩኤልን ከድረጅት ጉዳይ ሃላፊነት ባስቸኳይ አነሱት።እንደፈሩት እኛም ከዚያን ቀን ጀምሮ የየአካባቢያችን የግንቦት ሰባት ተጠሪዎችን መመርመር ስንጀምር ውነትም ተሰብሰበን የመረጥናቸው አይደሉም የድርጅቱ ተወካይ ሆነው የሚመሩን፤ከበላይ አካል የተወከሉ ኖረዋል፤አሁንም እነሱው ናቸው እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ድርጅቱን የሚመሩት፤የደቡብ ልጆች።ሌላም ሌላ ማለት ይቻል ነበር ስንቱ ተወርቶ ያልቅል እንጂ።እንደኔ አይነቱን በምኖርበት አካባቢ የነሱን ሰው እስኪያገኙ ድረስ ያስቀምጣሉ እንጂ እምነት አይጣልባቸውም፤በአንድ ወቅት ስንት ደክሜ ለድርጅቱ መልምዬ ያቀረብኩላቸውን ሰዎች አንቀበል ብለውኝ ወትውቼ ሲያቅተኝ ሙያዬ ምስክርን ራሷን ወደ አለቃዬ አማላጅ ብልክም አልሆን ብሎኝ የሙሉነህ እዩኤልን ስልክ ቁጥር ከሷ ተቀብዬ ደውዬ አግኝቸው ስለችግሩ አነጋግሬው የሰጠኝ መልስ የሚገርም ነበር፤እኔ ምንም አያገባኝም እዚው ጨርስ ነበር ያለኝ።የኔ አካባቢ የአህጉሩ ተጠሪ የሱው አካባቢ ሰው ስለሆነ ለሱው መልሶ ሰጠኝ።ያቺ ቀን ነበረች ከዚህ ጉደኛ ድርጅት የተገላገልኩባት ቀን።ትእቢታቸው እስከዚህ ድረስ ጣሪያ የነካ ነበር።ያን ያህል ተዋርደን በትክክል ምሩን ነበርን ያልናቸው እኛ የአማራ ልጆች፤እነሱ ግን እኛን መግፋቱን ቀጠሉበት።ይህ ነው ሃቁ።
በተረፈ የአማራ ልጅ የሆንክ ሁሉ የየራስህን ምርምር አካሂድ ምን እየተሰራ እንደሆነ በዚሁ ጉደኛ ድርጅት ዙሪያ።ለማጠቃለል ያህል።ይህን አስቀያሚ የዘር ቆጠራና መሰሪ አካሄድ የጀመረው ዘረኛው የግንቦት ሰባት አመራር አካል እንጂ እኛ አይደለንም።እኛም በየዋህነት ልንከተላችው ያሉትን ሁሉ እስከ ህይወታችን መገበር ድረስ ርቀት ሄደን ዋጋ ልንከፍል የተዘጋጀን የዘረኝነት ጋኔል እንደነሱ ያልጠጠናወተን ንጹህ የኢትዮጵያ ልጆች ነበርን።እዚህ የዘቀጠ ጨዋታ ውስጥ ያስገቡን እነሱው ናችው።
ተገፍተን ገደል ሊከቱን አፋፉ ላይ ስለደረስን እነሱ የወረዱበት ወርደን ራሳችንን ማዳን የግድ ይላል።አለበለዚያ መጥፋታችን ነው።የአማራ ልጅ ጀንበር ሳይጠልቅ ራስህን ለማዳን ተንቀሳቀስ፤ገፉን እንጂ አልገፋናቸው።
“ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር”

ሰበር ዜና – በጅማ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል አክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት አደረሱ

ሰበር ዜና – በጅማ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል አክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት አደረሱ

eotc patriarchate edd
  • 2 ኦርቶዶክሳውያን እና 5 ሙስሊሞች መጎዳታቸው እየተገለጸ ነው
  • ከ4ቱ የጥቃቱ አድራሾች አንዱ ተይዟል፤ 3ቱ አምልጠዋል፤ ተብሏል
  • ሀ/ስብከቱ ከወረዳው የአስተዳደርና የጸጥታ አካላት ጋር እየሠራ ነው
 በጅማ ሀገረ ስብከት የም ልዩ ወረዳ ቁንቢ ቀበሌ፣ በቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሰበካ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች፣ ዛሬ፣ ሰኔ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ማለዳ በአክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተሰማ፤ በነዋሪ ሙስሊሞችም ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡
ምእመናኑ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው፣ በቤተ ክርስቲያኑ የኪዳን ጸሎት አድርሰው በሚመለሱበት ወቅት ነው፤ ተብሏል፡፡
በጥቁር አልባሳት ፊታቸውን የሸፈኑ አራት የጥቃቱ አድራሽ አክራሪዎች፣ ወደ አካባቢው በመኪና እንደ ደረሱ ጥቃታቸውን የጀመሩት፣ በቀጥታ በአካባቢው ወደሚገኝ አንድ መስጊድ በመግባት እንደኾነ ተገልጧል፡፡
“ግንባር፣ አንገት፣ እጅ እየመቱ ያገኙትን በስለት ጨፈጨፉ፤” ያለው የስፍራው ምንጭ፣ በጭፍጨፋው አምስት ሙስሊሞች(አክራሪዎቹ እንደ ከሐዲ/ካፊር የሚቆጥሯቸው ነዋሪዎች) ክፉኛ መቁሰላቸውን ተናግሯል፡፡
ከመስጊዱ እንደወጡ ወደ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አቅጣጫ በማምራት፣ የኪዳን ጸሎት አድርሰው በመመለስ ላይ በነበሩ ምእመናን ላይም በቀጠሉት ጥቃት፤ ኹለት ምእመናንን ክፉኛ አቁስለዋል፤ ከቆሰሉት የአንዷ እጇ በጥቃቱ ተቆርጦ ከቆይታ በኋላ መገኘቱ ተጠቅሷል፡፡ 
ከጥቃቱ አድራሾች ሦስቱ በመጡበት መኪና ከአካባቢው በመሰወር ያመለጡ ሲኾን፣ አንዱ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ታውቋል፡፡ “ወደ ጅማ አቅጣጫ ነው የነዱት፤ ቅስቀሳቸውንና ጥቃታቸውን ከማስፋፋታቸው በፊት በተጠናከረ ክትትልና አሠሣ ሊያዙ ይገባል፤” ይላል አንድ የአካባቢው ነዋሪ፡፡
በጥቃቱ ከተጎዱት ምእመናን፣ ለሕክምና ወደ አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የደረሱ መኖራቸው ተጠቁሟል፡፡
የቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሚገኝባት የም ልዩ ወረዳ፣ በሰኩሩ እና ናትሪን መካከል ያለችና አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ምእመናን፣ ከሚበዙት የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር በመከባበርና በመገናዘብ የሚኖሩባት ወረዳ እንደ ኾነች ተመልክቷል፡፡
የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ እና ጽ/ቤታቸው፣ የተጎዱትን ምእመናን ለመርዳትና ጥቃት አድራሾቹን ለመቆጣጠር ከወረዳው አስተዳደርና የጸጥታ አካላት ጋር በቅርበት እየሠሩ መኾኑ ተገልጧል፡፡
በጅማና በኢሉባቦር አህጉረ ስብከት ዴዴሳ ወረዳ፣ ክርስቲያኖች፣ የጦር መሣርያና ገጀራ በያዙ አክራሪዎች ተደጋጋሚ ጥቃት(ግድያ፣ ዘረፋ፣ የቤትና የንብረት ውድመት፣ መፈናቀልና ፆታዊ መደፈር) ሲፈጸምባቸው ቆይቷል፡፡ ከመስከረም 16 ቀን 1999 ዓ.ም. ጀምሮ በነበሩት ተከታታይ ቀናት፥ በጎማ፣ በማና እና በቶባ 12 ክርስቲያኖችን ገድለው፣ ሦስት አብያተ ክርስቲያናትን (የጨጎ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቦሬ ቅዱስ ገብርኤል እና በሻሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ) አቃጥለው ንዋያተ ቅድሳቱን ከመዝረፋቸውም በላይ፤ ከ800 በላይ የአባ ወራ ቤቶችን በማቃጠል ከቀዬአቸው ማፈናቀላቸውና በግዳጅም ማስለማቸው ይታወሳል፡፡

Wednesday, June 15, 2016

Ethiopia's gov't confirms troops clashed along the border with Eritrea

እየመጣ ያለዉ መረጃ እጅግ ቅስም ሰባሪና አስደንጋጭ ነዉ::
አንድ ከፍተኛ የወያኔ ጦር መሪ በሻቢያ ልዩ ሬንጀር ጦር በቁጥጥር ዉሏል እየተባለ ሲሆን አንዳድ ምንጮችም የጦር መሪዉ ተማርኮ ሳይሆን በስሩ ያሉትን በመቶወች የሚቆጠር ጦር እስከትጥቁ ይዞ ነዉ ኤርትራ የነፃነት ሀይሎችን ነዉ የተቀላቀለዉ እየተባለ ነዉ::
ወደነፃነት ሀይሎች መሆኑ መልካም:: ወያኔ አጣብቂኝ ዉስጥ ነዉ::

ሰኔ 07 2008 ዓ.ም / የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት የኤርትራ መንግስት በድንበር አካባቢ ላካሄደው ትንኮሣ ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰዱ ተገለጸ፡፡

Ethiopia's gov't confirms troops clashed along the border with Eritrea

ወያኔ ከገባበት ውጥረት ለመውጣት በከፈተው ጦርነት ትኩረታችን አይቀለበስም !!!አርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ !!

ወያኔ ከገባበት ውጥረት ለመውጣት በከፈተው ጦርነት ትኩረታችን አይቀለበስም !!!
መግለጫ !!
June 13, 2016
በጥጋብና እብሪት የተወጠረው የህወሃት አገዛዝ በትናንትናው ዕለት ዕሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008 በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በኩል ከኤርትራ ጋር በሚያዋስኑ የድንበር ቦታዎች ላይ ጦርነት ጀምራል፤ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ይህን ዜና አረጋግጠው ዘግበዋል። ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በወያኔ በኩል ስለጦርነቱ ምንም የተሰጠ መግለጫ ባይኖርም የኤርትራ መንግሥት በጾረና ግንባር በኩል ጥቃት እንደተፈጸመበት ትናንት ማምሻውን ይፋ ባደረገ መግለጫ አረጋግጦአል።
የህወሃት ዘረኝነት በፈጠረው ኢፍትሃዊነትና አፈና የተማረረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በአገዛዙ ላይ ተቃውሞውን እያጠናከረ ባለበት በዚህን ሰዓት በሙስና የተጨማለቁ የህወሃት የጦር ጀነራሎችና በሲቪል ማዕረግ አስተዳደሩን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩ ሃይሎች ለምን ይህንን ጦርነት መጫር እንደፈለጉ ግልጽ ነው። በኦሮሚያ የተነሳውን የመብት ጥያቄ ለማፈን ከ400 በላይ ሕዝብ መጨፍጨፉና በሺዎች የሚቆጠሩ እስር ቤት መታጎራቸው የህወሃትን ዕድሜ ለማራዘም እንደ አንድ መሣሪያ ሆኖ ላለፉት 25 አመታት ሲያገለግል በኖረው ኦህዲድ ውስጥ እንኳን ከከፍተኛ አመራር እስከ ተራ ካድሬ ያሉትን አስኮርፎአል። የወልቃይት ህዝብ ያነሳው የማንነት ጥያቄ ሌላኛው የህወሃት አጋር በሆነው ብአዴን ውስጥ የማያባራ ክፍፍል ፈጥሮአል። የነጻነት ታጋዮች በቅርቡ አርባምንጭ ከተማ አቅራቢያ የፈጸሙት የጀግንነት ገድል የደቡብ ኢትዮጵያን ሕዝብ የሚያንቃቃና ለትግል የሚያነሳሳ አርአያነት እንደፈጠረ የህወሃት አገዛዝ ተረድቶአል። በቤኔሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ በአፋርና በሱማሌ ከመሬት ንጥቂያ ጋር በተያያዘ ወንጀል ህወሃት ከህዝቡ ጋር አይጥና ድመት ድብብቆሽ ውስጥ ከገባ አመታትን አስቆጥሮአል። በአዲስ አበባና ሌሎች ትላልቅ ከተሞች ቀድሞውኑም የድጋፍ መሠረት እንደሌለው ማወቁ ብቻ ሳይሆን ይኩራራበት የነበረው የትግራይ ምሽግነትም ከእጁ ሙሉ በሙሉ እያፈተለከ መምጣቱን ተገንዝቧል። በዚህም ምክንያት ፊቱን ወደሰሜን በማዞር የሕዝቡን ትኩረት አስታለሁ ብሎ ወያኔ አምኖአል። አባይ ጸሃይዬና ሳሞራ ዩኑስ መቀሌ ላይ በቅርቡ ባደረጉት የህወሃት ስብሰባ ላይ “ህወሃት ከሌለ የትግራይ ህዝብ አይኖርም፤ ኢህአደግ ከሌለ ኢትዮጵያ አትኖርም” ማለታቸው ኤርትራን በመውረር በተለይም የትግራይን ህዝብ ድጋፍ መልሶ ያስገኛል የሚል እምነት በአገዛዙ መሪዎች ውስጥ መፈጠሩን ያመለክታል።
ሌላው ህወሃትን ወደ ጦር አጫሪነት እየነዳው ያለው እብደት መለስ ዜናዊ ከሞተ ወዲህ ድርጅቱ ውስጥ የነገሰው የእርስ በርስ የሥልጣን ሹኩቻ የፈጠረው ውጥረት እንደሆነ መገመት አያዳግትም። አንዱን ውጥረት ለማርገብ ሌላ የውጥረት ግንባር በመክፈት ለሚታወቀው ህወሃት ይህ የተለመደ ስትራቴጂ ነው።
አርበኞች ግንቦት7 ህወሃት የኢትዮጵያን ሕዝብ ትኩረት ለመቀየር የሚያደርገው ማንኛውም አይነት ጥረት እንዳይሳካለትና የጀመረው ይህ የትኩረት ማስቀየሻ ስትራቴጂ የህወሃትን ውድቀት አፍጣኝ እንዲሆኑ ለማድረግ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ካሁን ቀደም ለአገራችን ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም የሚሰጠው ፋይዳ ሳይመከርበትና ሕዝባዊ ስምምነት ሳይኖር ከአሥራ አንድ አመት በፊት ሱማሌ ውስጥ ዘፍ ተብሎ የተገባበት ጦርነት በየቀኑ የስንት ወንድሞቻችንን ህይወት እየቀጠፈ እንደሆነ እያየነው ነው። ቁጥራቸው ከ60 በላይ የሆኑ ወገኖቻችን ሰሞኑ በሽብርተኛው አልሸባብ ሲጨፈጨፉ የወያኔ መሪዎች አንዲትም ወፍ የሞተቺባቸው ያህል እንኳ አልተሰማቸውም ። ይህንን ሁሉም ያገራችን ህዝብ ያውቃል። እስከዛሬ በሰላም አስከባሪነት ስም ወደ ሰው አገር እየተላኩ ደመ ከልብ እየሆኑ ያሉ ወገኖቻችን ህይወት እያንገበገበን ባለበት በዚህን ሰዓት ለወያኔ የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ እንደ አገር የምንዋጋው ሌላ ጦርነት እንደሌለ ሊታወቅ ይገባል። በ1998ቱ የባድሜ ጦርነት ወቅት ህዝባችን የከፈለው ዋጋና ከባድሜ ጦርነት መልስ ጉልበቱን አጠናክሮ ለመውጣት ዕድል ያገኘው የህወሃት በህዝባችንና በአገራችን ላይ እስከዛሬ እየፈጸመው ያለው አፈናና ጭፍጨፋ ተረስቶ ሌላ ዕድል ለመስጠት ዳግም መሳሪያ የምንሆንበት ምክንያት የለም።
አርበኞች ግንቦት 7 ከአሁን ቦኋላ ወያኔ የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘምና የተዘፈቀበትን የሃብት ዘረፋ አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያደርገውን የሞት ሽረት ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ በምንም አይነት ሁኔታ ማስተናገድ የለበትም ብሎ ያምናል። በዚህም ምክንያት በመላው አገራችን የተጀመረው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ለፍትህ ለእኩልነትና ለነጻነት የሚደረገው ትግል ከግቡ እንዲደርስ የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ ትግሉን ለማጠናከር እንዲረባረብ አርበኞች ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያቀርባል ። በመካሄድ ላይ ያለውን የነጻነት ትግል አቅጣጫ ለማስለወጥ ወያኔ የሚያደርገውን የጦርነት እንቅስቃሴ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የነጻነት ቀናችንን እንድናፋጥን ሁላችንም እንነሳ ።
አርበኞች ግንቦት 7 ወያኔ በሰሜን በኩል የጀመረውን ትንኮሳ እየተከታተለ ለህዝባችን ወቅታዊ መረጃ ይሰጣል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
አርበኞች ግንቦት 7!!

wanted officials