Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, June 3, 2016

አሳዛኝ ዜና እንጋፋው ድምፃዊ መስፍን አበበ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ



ያዥልኝ ቀጠሮ፣ አይሽ አይሽና፣ መልካም ልደትና ሌሎችም ተወዳጅ ሙዚቃዎችን በጊታር በመጫወት የሚታወቀው ድምፃዊ መስፍን አበበ ትናንት በድንገተኛ ህመም ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ዛሬ ከንጋቱ 11 ሰዓት ገደማ ህይወቱ ማለፉን ለመረዳት ተችሏል።


መስፍን አበበ ከደሴ ወ/ሮ ስህን ትምህርት ቤት ባንድ ጋር በመሆን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በመዘዋወር ሙዚቃዎችን ይጫወት ነበር፡፡

ቦክስ ጊታሩን በመያዝ 22 ያህል ካሴቶችን ማሳተሙን ከቤተሰቦቹ ለመተዳት ተችሏል።

ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባት የነበረው የድምፃዊ መስፍን አበበ የቀብር ስነ-ሥርዓት ነገ ከቀኑ በ6 ሰዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያ ይፈፀማል ተብሏል፡፡

ለመላው ቤተሰቡና ወዳጆቹ እንዲሁም ለኣድናቂዎቹ መጽናናትን እመኛለው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials