Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, June 7, 2016

የግንቦት 7 ተከሳሾች እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ መከላከል አትችሉም ተባሉ

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ መከላከል አትችሉም ተባሉ
የካቲት 4/2008 ዓ.ም ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል በዋለው ችሎት እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ( ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካህሳይ) አቃቢ ህግ ያቀረበባቸውን ክስ በሰነድና በአንድ የሰው ምስክር ማስረጃዎች አስረድቷል በሚል ተከሳሾች መከላከል ይገባቸዋል ሲል ፍርድ ቤቱ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ ውሳኔውን ተከትሎም መከላከያ ማስረጃዎች ያቀርቡ ከሆነ በሚል ፍርድ ቤቱ ጠይቆ፣ ተከሳሾች 200 የሰው ምስክሮችና የሰነድ ማስረጃዎች በጋራ እንደሚያቀርቡ አሳውቀው ነበር፡፡ ከዛ በኋላ በነበሩ ቀጠሮዎችም ምስክሮቻቸውን በዝርዝር ያስገቡ ሲሆን ከዛሬ ግንቦት 30 እስከ ሰኔ 8 , 2008 ድረስ ምስክሮቻቸውን እንዲያሰሙ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው የነበረ ቢሆንም የቀጠሯቸው ቀን ሳይደርስ ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት ቀርበው ጭብጥ እንዲያሲዙ ተጠይቀዋል። እነሱም የምስክርነት ጭብጥ ምስክሮች መሃላ ሳይፈፅሙ መያዝ እንደሌለበት ለፍቤቱ አስረድተው ውሳኔውን ለመስማት ለዛሬ ተቀጥረው ነበር።
የዛሬው ውሳኔ ግን በጣም የሚደንቅ ነው። አራት ወር ሙሉ ፍርድ ቤቱ ሲሰጥ የነበረውን ትእዛዝ ይቃረናል። "መከላከያ ምስክር ማሰማት የለባችሁም ስለዚህ ለፍርድ ብይን ሃምሌ 13, 2008 ቅረቡ" የሚል ውሳኔ አስተላልፋለች ዳኛዋ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials