Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, June 1, 2016

የኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም አጎት በዙምባብዌ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው አልፏል

asrat welde 2
(ዘ-ሐበሻ) የኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም አጎት የሆኑት አምባሳደር አሥራት ወልዴ በዙምባብይ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ባለፈው ማርች 1 ቀን 2016 አልፏል:: ለዘ-ሐበሻ የደረሰው የ40 ቀን መታሰቢያ ካርድ እንደሚያስረዳው አምባሳደር አስራት ወልዴ ቤተሰቦቻቸው ካፈራቸው 10 ልጆች መካከል የመጨረሻው ታንሽ ልጅ ሲሆኑ ወላጅ አባታቸው እና እናታቸው እንዲሁም ወንድሞቹና እህቶቻቸው ገና ወጣት ሳለ በተለያዩ ጊዜያት በሞት በመለየታቸው ኃላፊነትን ለመሸከም ብቃት እና ፍላጎት ባላቸው በመጀመሪያውናና በታላቅ ወንድማቸው (የመንግስቱ ሃይለማርያም አባት) ሃምሳ አለቃ ኃይለማርያም ወልዴ እንክብካቤ አድገዋል::
አምባሳደር አሥራት ወልዴ በኢትዮጵያ ሚሽን ትምህርት ቤና በተስፋ ኮከብ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሩ ሲሆን በአሜሪካን አገር በባችለር እና በማስተርስ ዲግሪ ተመረቀው በከፋ; በወሎና በአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ትምህርት ቤት በዳሬክተርነት እንዳገለገሉ የሕይወት ታሪካቸው ያሳያል:: በትምህርት ሚኒስተር ምክትል ሚኒስቴር በመሆን እንዲሁም በራሺያና በዙምባብዌ አምባሳደር ሆነውም አገልግለው ነበር::
አምባሳደር አሥራት ወልዴ ማክሰኞ ማርች 1 2016 ባልታሰበና ድንግተኛ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ የቀብር ሥነስር ዓታቸውም ኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያምን ጨምሮ የተለያዩ ወገኖች በተገኙበት ተፈጽሟል::
ሙሉ ታሪካቸውን ለማንበብ ፎቶዎቹን ይጫኑ
asrat welde
asrat welde 1

No comments:

Post a Comment

wanted officials