Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, June 5, 2016

"ካልሞትክ አይገድሉህም" //ዳንኤል ክብረት በዋልተንጉስ ዘሸገር//

"ካልሞትክ አይገድሉህም"
//ዳንኤል ክብረት በዋልተንጉስ ዘሸገር//
በእንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጎድ ውስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ በራሷ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች፡፡ በጣምም መጮህ ጀመረች፡፡ ባለቤቱም አህያዋን ለማውጣት ብርቱ ሙከራ ቢያደርግም ሊሳካለተ አልቻለም፡፡ አህያዋም ብዙ ያገለገለችና ያረጀች ስለሆነች እንዲሁም ሌሎች እንስሳትም ወደ ጉድጓዱ እንዳይገብበት በማሰብ ጉድጓዱ ውስጥ ሊቀብራት ወሰነ፡፡
ጎረቤቶቹንም አስተባብሮ ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመረ፡፡ አህያዋ ይህን ስትመለከት እየቀበራት መሆኑነ ተረዳችና በሰቀቀን አለቀሰች፡፡ይሁን እንጂ አህያዋ አፈር ሲደፋባት አንድ ነገር ታደርግ ጀመር፡፡ አፈሩ በተደፋባት ቁጥር አፈሩን እያራገፈች ከአፈሩ ውስጥ ብቅ ትል ጀመር፡፡በተደጋጋሚ ከሚደፋባት አፈር ላይ መቆምም ትጀምራለች፡፡በሂደት ውስጥ በአፈሩ ላይ በቆመች ቁጥር ከነበረችበት ጉድጓድ ከፍ እያለች ከፍ እያለች በመጨረሻም ጉድጓዱ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ መውጣት ቻለች፡፡በሚገርም ሁኔታ አህያዋን ሊቀብሯት ሞከሩት ሰዎች በአህያዋ አወጣጥ በእጅጉ ተደነቁ፡፡
︵ በህይወታችን ውስጥ ያለው አማራጭ ወደ ላይ መውጣት አልያም ደግሞ ወደታች ወርዶ ከጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ተቀብሮ መቅረት ብቻ ነው!
አይጠቅሙም ብለን ወርውረን የጣልናቸው ለሀገር ኩራት እና መከታ ሲሆኑም እናስተውላለን።

No comments:

Post a Comment

wanted officials