Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, June 3, 2016

እነ ብርሀኑ ተ/ያሬድ ያለቀጠሮአቸው ተገደው ፍርድ ቤት ቀረቡ



–ፍርድ ቤቱ የተክሳሽኦችን የመክላክያ ምስክሮች በምን ጭብጥ ላይ እንደሚመስክሩ ከምስክሮቹ ቀጠሮ አስቀድሞ እንዲገለፅ ጠይቃል
–ተከሳሾቹ ግርድ ቤቱን እና ማረሚያ ቤት ህገወጥ ጫናና ወከባ እየፈጠሩብን ነው ብለዋል
የክስ መዝገባቸው በከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት በመታየት ላይ የሚገኘው 4 ተከሳሾች ብርሀኑ ፤እየሩሳሌም፤ፍቅረማርያም እና ደሴ ፍርድ ቤቱ እንዲከላከሉ ብይን በሰጠባቸው ጉዳዮ ላይ የመከላከያ ምስክር ለማቅረብ ከግንቦት 30-ሰኔ 8 ክትሮ ተይዞላቸው የነበረ ቢሆንም ዛሬ ግንቦት 23 ቀን ያለቀጠሮዋቸው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተደርጋል
ተከሳሾቹ ዛሬ ፍርድ ቤት እንደሌላቸው ለማረሚያ ቤቱ ሀላፊዎች የገለፁ ቢሆንም በማረሚያ ቤቱ የጥበቃ ሃላፊዎች ወከባና ግፍተራ እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችላል ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ከቀረቡም በሀላም ለፍርድ ቤቱ ይህንን ያስረዱ ሲሆን የፍርድ ቤቱም ዳኛም “ዛሬ ቀጠሮ ባይኖራችሁም ፍርድ ቤቱ ማጣራት ያለበት ጉዳይ ስላለ ነው የጠራናችሁ”በማለት የተከሳሾቹ መከላከያ ምስክሮች የሚመሰክሩበትን ጭብጥ ተከሳሾቹ ዛሬ ለፍርድ ቤቱ እንዲያስረዱ ጠይቀዋል ተከሳሾቹም ምስክሮቻቻ  ሚመስክሩበጽን ጭብ ጥ ምስክር ነጽ በሚሸፅበጽ እለት እንጂ ምስክሮቹ ከመቅረባቸው አስቀድሞ ለፍርድ ቤቱ የማሳወቅ ህጋዊ ግዴታ የሌለባቸው መሆኑን የገለፀ ሲሆን ዛሬ በፍርድ ቤቱ እየተጠየቁ ያለው ቅድመ ሁኔታ ግን ህጋዊ መሰረት የሌለው እና ፍርድ ቤቱም የሌሎች የገዢው ፓርቲ የአፈና መዋቅርት ተፅእኖ እንዳረፈበት የሚያሳይ ነው ብለዋል.
ተከሳሾቹ አያይዘው እንደገለፁትም ለምስክሮች የተዘጋጀው መጥሪያ በፍርድ ቤቱ ዳኛ ተፈርሞ ለምስክሮቻቸው እንዲሰጥ ማረሚያ በት ለሚገኙ ተከሳሾች ከደረሳቸው በሀላ በድጋሚ “በፍርድ ቤት ትእዛዝ ነው” በሚል ምክንያት መጥሪያዎቹን የተነጠቁ ሲሆን በማረሚያ ቤቱ ሀላፊዎች በኩልም መከላከያ ምስክሮቻቸውን በተመለከተ በተለይም የገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ለምስክርነት ማስጠራታቸውን ተከትሎ ማስፈራርያና ወከባ እየደረሰባቸው ነው በመጨረሻም ተከሳሾቹ የምስክሮቻቸውን ጭብጥ ለፍርድ ቤቱ እንደማያሳውቁ በአፅንኦት የገለፁ ሲሆን የፍርድ ቤቱ ዳኛ “ከአነጋገራችሁ የምስክሮቹን ጭብጥ ለመረዳት ጭለናል በመሆኑም ይህኑኑ ጉዳይ መርምረን ለግንቦት 30-2008 ብይን እንሰጥበታለነረ “ በማለት ተከሳሾቹን በተጠቀሰው ቀን እንዲርቡ ትእዛዝ ሰጥተዋል::

No comments:

Post a Comment

wanted officials