Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, June 22, 2016

የዘረኝነት ወረርሽኝ፣ ተስፋ አስቆራጭና አስፈሪ የጨለማ ጉዞ መድሃኒቱ ያልተገኘለት ትልቁ በሽታ እና የበታችነት አባዜ




የዘረኝነት ወረርሽኝ፣ ተስፋ አስቆራጭና አስፈሪ የጨለማ ጉዞ መድሃኒቱ ያልተገኘለት ትልቁ በሽታ እና የበታችነት አባዜ
አብዛኛው የምናየው በሰብዓዊነት እና በቀና መንፈስ እየተንደረደረ የወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ቫይረስ ተሸካሚ ሆኗል፤በሰከነ መልኩ ረጋ ብለን በተዘዋዋሪ ማሰብ የጀመርን ቀን ይገባናል ከዚህ ጎን ለጎን መርሳት የሌለብን ነገር ቢኖር ለዚህ ቫይረስ ማስፋፊያ እና ማበረታቻ ወያኔ የፈጠራቸው የዘረኝነት መርፌ ወጊዎች መኖራቸውን ነው፤ በዩንቨርስቲዎች በቅርቡም በስፖርት ሜዳዎች የተከሰቱት የዘረኝነት ችግሮች እና ግጭቶች ከዚህ የወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ሂደት ጋር በጣም የተሳሰሩ መሆናቸውን ልናውቅ ይገባል።ሳንፈልገው እያንደረደረ ወስዶ ከጎሳው ፖለቲካ ስለዶለን በዘረኝነት ስንፎር የምንውል መሆናችንን ባለመረዳታችን የበታችነት ስሜት አየተጠናወተን በጥላቻ አየተመምን ነው።

የዘረኝነት ወረርሽን ከአመት አመት እየተባባሰ፣ አገሪቱ እየተንሸራተተች ናት። የበርካታ ምሁራንና ዜጎች አዝማሚያ ስትመለከቱ… ሁሌም ባይሆን አንዳንዴ፣ የዚህች አገር ነገር፣ተስፋ ያስቆርጣል። ኢህአዴግ፣ ተቃዋሚዎቹን ያወግዛል – “የሁለት ተማሪዎችን ፀብ፣ የብሔረሰብ ፀብ አስመስለው ያራግባሉ” በማለት። ተጠያቂዎቹ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከሆኑ፣ ስልጣን ላይ ከሃያ አመት በላይ የቆየ ፓርቲ፣ ይህን በሽታ ማቃለል ለምን አቃተው? በርካታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ኢህአዴግን ይኮንናሉ – “የብሄረሰብ ፖለቲካን አስፋፍቷል፤ የቀበሌ መታወቂያ ላይ ይመዘግባል” በማለት።ምንሊክ ሳልሳዊ ግን፣ ኢህአዴግ ስልጣን ባልያዘበት በአሜሪካ፣በዳያስፖራ ፖለቲካና በፌስቡክስ ዓለም ለምን ዘረኝነት ገነነ? በዚህ መሃል ግን፣ የዘረኝነት ወረርሽን ከአመት አመት እየተባባሰ፣ አገሪቱ እየተንሸራተተች ናት። የዘረኝነት ወረርሽኝ ለኢትዮጵያ አስፈሪ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ። እርስበርስ፣ “አንተ ነህ ዘረኛ”፣ “አንቺ ነሽ ዘረኛ” እያሉ ይወነጃጀላሉ። ብዙዎቹ የሚያቀርቧቸው አማራጮች ግን፣ በቅፅል ብቻ የሚለያዩ የዘረኝነት መልኮችን ነው።
ምንም እንኳ፣ ኢትዮጵያ በብዙ አይነት የጥፋት ፈተናዎች ውስጥ፣ ህልውናዋን ሙሉ ለሙሉ ሳታጣ ያለፈች አገር ብትሆንም፣ የበርካታ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች ዝንባሌን ስትታዘቡ፣ የበርካታ ምሁራንና ዜጎች አዝማሚያ ስትመለከቱ… ሁሌም ባይሆን አንዳንዴ፣ የዚህች አገር ነገር፣ተስፋ ያስቆርጣል። ከአመት አመት፣ የዘረኝነት ወረርሽኙ እየባሰበት፣ አገሪቱ ወደለየለት የጥፋት አዘቅት እንዳትሰምጥ አትሰጉም? በእርግጥ፣ አልፎ አልፎ፣ የዘረኝነት በሽታው፣ ለአፍታ ጋብ ሲልለት… እሳቱም ትንሽ ሲበርድለት እያየን፣ የእፎይታና የተስፋ ስሜት እናገኛለን። ግን፣ እፎይታው ብዙም አይቆይም። እንደገና በሽታው ያገረሸበታል። ማገርሸት ብቻ አይደለም። ከእያንዳንዱ እፎይታ በኋላ፣ ወረርሽኙ ባገረሸ ቁጥር፣ ከቀድሞው እጅጉን ብሶበት እናገኘዋለን። ተስፋ አስቆራጩና አስፈሪው ነገር ደግሞ ምን መሰላችሁ? የዘረኝነት ወረርሽኙን ለማስቆም የሚያስችል፣ አስተማማኝ መላ ምን እንደሆነ በግልፅ ጎልቶ አለመታየቱ ነው። ዙሪያው ሁሉ በጨለማ የተዋጠ ጉዞ ይመስላል።
በዩንቨርስቲዎች በቅርቡም በስፖርት ሜዳዎች እያየን ያለነው ጉዳይ አጅግ የሚገርም እና የለውጥ ሃይል ነን የሚሉ ኣማሳኞች ሳይቀሩ አየተራወጡ ያሉበት የዘረኝነት መነባነብ በኣገሪቱ ስር አንዳይሰድ ትውልዱ እንዳይበከል የሚያስፈራ ጉዳይ መሆኑ ውሎ ኣድርዋል፥፥ምንሊክ ሳልሳዊየሚደርሱኝ መረጃዎች አንደሚጠቁሙት ዘረኝነትን ለማስፋፋት የተለያዩ ኣካላት ገንዘብ መድበው በሃገር ቤት ያለውን ወጣት ለፍጅት እና ለኣጀንዳቸው ማስፈጸሚያ አያጩት ነው።ይህ ደግሞ የሕወሓት አጅ የለበትም ማለት ዘበት ነው። ሕወሓት ወንጀለኘ አና ኣሸባሪ ዘረኛ እና ኣስመሳይ ማፊያ እና ዘራፊ ሕገወጥ ድርጅት ነው።
በዲያስፖራው ዘንድ በስፋት አየተራገበ ያለው ይህ ወያኔ ወለድ በሽታ ዋናው ክስተቱ የገዢው ፓርቲ ሕወሓት የፈጠረበት የበታችነት ስሜት ሲሆን በሕወሓቶች ዘንድ ከበታችነት ለመላቀቅ በሚደረግ መራወጥ የሚፈጠር ጥላቻ ዘረኝነት የሰረጸባቸው ያዩት የሰሙት ሁሉ የሚያስደነብራቸው የበታች መደቦች ኣንድ ጉዳይ በተነሳ ሰኣት ሁሉ ዘር ላይ የሚንጠለጠሉ እና የስልጣን ጥማትን ለማርካት ሲባል የሃገር አና ሕዝብን ሃብት ለመበዝበዝ የነገ ትውልድ ኣደጋ የማይታያቸው ሕዝብን በዘር በመከፋፈል ለመግዛት የሚያደርጉት ደባ ነው። ቆቤ ኦሮሞ ፤ ቤተ ኣማራ ፤ ትግራዋይ ምናምን እየተባለ በወያኔ የደህንነት ተቍማት ስራ የሚደራጁ ክንፎች በነማን እንደሚመሩ በነማን በጀት እንደሚጦዙ የኣጀንዳዎቹ መነሻዎች እነማን እንደሆኑ ምስክር ኣያስፈልግም።
ይህ ወያኔ ወለድ የሆነ የዘረኝነት በሽታ በኢትዮጵያ ውስጥ ይህን ያህል ባይስፋፋም በዲያስፖራው ዘንድ ግን ስር የሰደደ በሽታ ከሆነ ሰነባብዋል።ጥቂት ዲያስፖራዎች በሃገር ቤት ያሉትን ወጣቶች በገንዘብ በመግዛት ዘረኝነትን ለማስፋፍት ሲጣጣሩ ይስተዋላል።ኣለም በኣንድ የእድገት መሰረት ላይ ለመመስረት በቴክኖሎጂ እና ትልልቅ ግኝቶች ላይ ባተኮረበት በዚህ ዘመን ጥቂቶች የሚፈጥሩት የድህረገጽ የዘረኝነት ወከባ አጅግ ኣሳዛኝ እና ኣስደንጋኝ ነው።ሕወሓት አነዚህን በቆሸሸ ታሪክ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሰዎችን በመጠቀም ኢትዮጵያውያንን በዘር ከፋፍሎ ኣጀንዳውን ለማስፈጸም አየሮጠ ነው።በዲያስፖራው ጉያ ስር ተወኅቀው የወያኔን የዘረኝነት ኣጀንዳ ለመፈጸው አያወቁም ሳያውቁ ደፋ ቀና የሚሉ ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ሊያስቡ ይገባቸዋል።የማያዘልቅ ጸሎት ለቅጽፈት መሆኑን ተረድተው ከዘረኝነት በሽታ ሊላቀቁ ይገባቸዋል። በጥቅም ላይ የተመሰረተ ወጣቱ ያላመነበት የዘረኝነት መስፋፋት ውጤቱ በአኩይ ተግባር ላይ ለተሰማሩ ዘረኞች ኣደጋ ነው።‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment

wanted officials