Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, June 9, 2016

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የህግ ምክር እንዲያገኙ ስምምነት መደረሱ ተነገረ

የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢ/ያ መንግስት በእስር ላይ የሚገኙ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ነጻ የሆነ የህግ ምክርን አግኝተው የሃገሪቱ የህግ- ስርዓት የሚፈቅደውን አማራጭ እንዲመለከቱ ስምምነት መደረሱን ሃሙስ ይፋ ተደረገ። ይኸው ስምምነት በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉ የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሃሞንድና በኢትዮጵያ ባለስልጣናት በኩል መደረሱን የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከምክክክሩ በኋላ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ለሁለት ቀን በአዲስ አበባ ቆይታ
የነበራቸው ሚኒስትሩ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይን በዋና አጀንዳነት አንስተው የተወያዩ ሲሆን፣ በቀጣይ ሊወስዱ በሚችሉ የህግ አማራጮች ዙሪያም ሰፊ ምክክር ማካሄዳቸው ታውቋል።
ከብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር አብረው የተጓዙ ከፍተኛ ባለስልጣናት ረቡዕ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በእስር ቤት ተገኘተው መጎብኘታቸውንና በጉዳዩ ዙሪያ መምከራቸውን የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። በሚኒስትሩ ፊሊፕ ሃሞንድ የቀረበን ጥያቄ ተከትሎ ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር የተገናኙ የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይትን ቢያካሄዱም ባለስልጣናቱ በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር መረጃን ከመስጠት እንደተቆጠቡ ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የብሪታኒያ መንግስት የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጉዳይ በሂደት እንደሚከታተልና ያቀረባቸው ሃሳቦች በምን መልኩ
ተፈጻሚ እንደሚሆኑ ቀጣይ ውይይቶችን እንደሚያካሄድ አክሎ ገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረጉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት የሃገሪቱ መንግስት ዜጋውን ከእስር ለማስለቀቅ በቂ እርምጃን አልወሰደም ሲሉ ዳግም ተቃውሞ መክፈታቸው ታውቋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials