በአዲስ አበባ ዙሪያ ከቀያቸው ተፈናቅለው ኮረብታ ላይ የሰፈሩት ዜጎች እንደገና ተነሱ
ሰኔ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም
ኢሳት ዜና
እንደገለጸው ከአዲስ አበባ የዘፈቀደ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የእርሻ ቦታቸውን የተነጡቁት አርሶአደሮች ፣ በለቡ አደባባይ አብርሃሙ ስላሴ ቤተክርስቲያን ያለበት ኮረብታማ ቦታ ላይ መኖሪያ ቤታቸውን ሰርተው ቢኖሩም፣ አሁንም እንደገና ቤታቸው እንዲፈርስ በመደረጉ ያለምንም ካሳ መውደቂያ አጥተው ይገኛሉ። ነዋሪዎቹ ቤቶቻቸው ሲፈርሱባቸው እቃዎቻቸውን እንኳን እንዲያወጡ ጊዜ አልተሰጣቸውም። ነዋሪዎቹ ከዚህ በፊት በከተማው መስፋፋት ምክንያት ሲገፉ ቆይተው ኮረብታው ላይ ቢሰፍሩም አሁን ደግሞ ይህንንም ቦታ ተቀምተው ህልውናቸው አደጋ ላይ ወድቋል ብሎአል። አካባቢው ከፍ ያለና ከተማውን ቁልቁል ለመመልከት የሚመች እይታ ያለው በመሆኑ ፣ ለባለሃብቶች እና ለባለስልጣናት መኖሪያ ግንባታ እንደሚያገለግል መሃንዲሶች ገልጸዋል።
የድሆችን ቤት የሚያፈርሱት አፍራሽ ግብረሃይል እየተባሉ የሚጠሩ ሲሆን፣ እነሱም በፈንታቸው በድህነታቸው ምክንያት በአነስተኛ እና ጥቃቅን ድርጅቶች የተደራጁ ናቸው። እነዚህ ወጣቶች ያፈረሱትን ቤት ቆርቆሮ ነቅለው በመውሰድና በመሸጥ ገቢ የሚያገኙ በመሆኑ፣ ቤቶችን ሲያፈርሱ ለነዋሪዎች ምንም ርህራሄ አያሳዩም። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ወደ ጀሞ በሚወስደው መንገድ ወይም ከሆፕ ዩኒቨርስቲ ገባ ብሎ ባለ ሰፊ ቦታ ላይ ለሚገነባው ሁዋጃይን አለማቀፍ የቀላል ኢንዱስትሪ ዞን ሲባል በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች በይል ከቀያቸው እንዲባረሩ በመደረጉ ለችግር ተዳርገዋል።
የቤት ማፍረሱ ስራ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ተጠናክሮ በመቀጠሉ በርካታ ዜጎች ለችግር መዳረጋቸውን ለኢሳት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል።

No comments:
Post a Comment