Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, June 14, 2016

ሰይፉ ፋንታሁን ታሰረ – ነገ ሊፈረድበት ነው



(ዘ-ሐበሻ) ሰይፉ ፋንታሁን ታሰረ – ነገ ሊፈረድበት ነው:: ጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን በቀረበበት ሀሰተኛ ወሬ የማሰራጨት ክስ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ሰይፉ በመናገሻ ምድብ ችሎት ፍርድ ቤት ዛሬ በቀረበበት ወቅት ‹‹አዎ ድርጊቱን ፈፅሜያለሁ›› በማለት የእምነት ቃሉን እንደሰጠ ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡ ፍርድ ቤቱም ተከሳሹ የቀረበበትን ክስ መፈፀሙን በማመኑ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ቀጠሮ ሰጥቶ ተከሳሹ በቁጥጥር ስር እንዲቆይ አዟል፡፡ በዚህ መሰረት ሰይፉ ፋንታሁን በአሁኑ ወቅት በጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ይገኛል፡፡ በነገው ዕለት በሚውለው ችሎት የእስር ወይንም የገንዘብ ቅጣት ሊጣልበት ይችላል፡፡

ለክስ የዳረገው ጉዳይ በቴዎድሮስ ተሾመና ቴዎድሮስ ተሾመ ድርሰቴን ሰርቆኛል ብለው ክስ በመሰረቱት ግለሰብ ዙሪያ በሬዲዮ ያሰራጨው ወሬ ነው፡፡ የሁለቱ ግለሰቦች ክስ በፍትሀብሄር እየታየ በነበረበት ሰዓት ሰይፉ በችሎት ያልተባለን ነገር ተብሏል ብሎ በማውራቱ ነው የተከሰሰው፡፡
ከዚህ ቀደም ሳያት ሳያት ደምሴ በዚሁ ፍርድ ቤት ሰይፉ ላይ ክስ አቅርባ እንደነበርና ጉዳዩ በሽምግልና ተድበስብሶ እንዲቀር መደረጉ ይታወሳል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials