Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, June 5, 2016

በሱዳን አብዬ ግዛት የሞቱ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ቁጥር 16 ደረሰ፡፡

ሁለቱ ሱዳኖች የይገባኛል ጥያቄን አንስተው በሚገኙባት የአብዬ ግዛት በሰላም ማስከበር ስራ ላይ ተሰማርተው ከሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች መካከል በተለያዩ ጊዜያት የሞቱ ወታደሮች ቁጥር 16 መድረሱን የተባበሩት መንግስታት የልዑካን ቡድን ገለጠ።
የሰላም አስከባሪ ቡድኑ ሰላም ማስከበር ስራ ላይ ተሰማርተው ህይወታቸው ላጡ ወታደሮች ቤተሰቦች የክብር የሜዳሊያ ስጦታን ሰሞኑን በአብዬ ግዛት ማበርከቱን የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ሁለቱ ሱዳኖች በነዳጅ ሃብቷ የምትታወቀው የአብዬ ግዛት ይገባኛል ማለታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያና የተለያዩ ሃገራት በሺዎች የሚቆጠሩ የሰላም አስከባሪ ሃይልን በስፍራው አሰማርተው ይገኛሉ።
ይሁንና የሰላም አስከባሪ ሃይል በተለያዩ ጊዜያት ከታጣቂዎች ጥቃት የሚፈጸምበት ሲሆን የሰላም ልዑኩ ከአምስት አመት በፊት ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ 20 ወታደሮች መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል።
ይሁንና ከሟቾቹ መካከል 16ቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የልዑኩ ምክትል ሃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ዘውዱ ኪሮስ የሞቱ ወታደሮች በመወከል የተበረከተላቸውን የክብር ሜዳሊያ መረከባቸው ታውቋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials