በሻሸመኔ ከተማ በየዕለቱ ወጣቶች ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ የመገኘታቸው ዜና ያንገሸገሸው የሻሸመኔ ነዋሪ ዛሬ ብሶቱ ገንፍሎ ወጥቶ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን ሲያሰማ ዋለ::
“በየምሽቱ እየተገደሉ የሚገኙት ወገኖቻችን ደም መፍሰሱ ይቁም” ሲሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የሻሸመኔ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን በአደባባይ ቢያሰሙም የፌደራል ፖሊስ እና አጋዚ ሕዝቡ ላይ ጥይት በመተኮስ ለመበተን ሞክረዋል::
በሻሸመኔ ማን እንደገደላቸው አይታወቅ እንጂ ከኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ ጋር የሚገናኙ ወጣቶች ተገድለው እየተገኙ ነው:: ባለፈው ሳምንት ህዝቡ ለቀብር በወጣበት ወቅት በአደባባይ ተቃውሞውን ቢያሰማም ሰሚ አጥቶ እንደውም ግድያው እየተባባሰ መሄዱ ዛሬ ህዝቡ በአደባባይ ወጥቶ ብሶቱን እንዲያሰማ ምክንያት ሆኖታል::
በዛሬው ተቃውሞ ተማሪዎች እና ነዋሪው ሕዝብ በአንድ ላይ ወጥቷል::
No comments:
Post a Comment