Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, June 23, 2016

የአውሮፓ ሕብረት የኤርትራን ጨምሮ የ19 ሃገራት አየር መንገዶች በአውሮፓ እንዳይበሩ አገደ



ሲሲቲቭ የተሰኘው የቴሌቭዥን ጣቢያ ዛሬ እንደዘገበው የአውሮፓ ሕብረት በ12 የአፍሪካ ሃገራት አየር መንገዶች ላይ በሕብረቱ የአየር ክልሎች እንዳይበሩ እገዳ አስተላለፈ::

ሕብረቱ ኤርትራን ጨምሮ በ12 ሃገራት ላይ እገዳውን ሲጥል ሃገራቱም

1ኛ . ቤኒን
2ኛ. ኮንጎ ሪፐብሊክ
3ኛ. ዴሞክራሲያ ሪፐብሊክ ኮንጎ
4ኛ. ጅቡቲ
5ኛ. ኢኳቶሪያል ጊኒ
6ኛ. ጋቦን
7ኛ. ላይቤሪያ
8ኛ. ሊቢያ
9ኛ. ሞዛምቢክ
10ኛ. ሴራሊዮን
11ኛ. ሱዳን ናቸው::

የአውሮፓ ሕብረት የ214 አየር መንገዶችን የደህንነት ደረጃ የመረመረ ሲሆን ከአፍሪካ 12 እንዲሁም ከሌሎች ዓለም ሃገራት 7 በጥቅሉ የ19 ሃገራትን አየር መንገዶች አግዷል::

ለረዥም ጊዜያት እገዳ ተጥሎበት የቆየው የዛምቢያና የማዳጋስካር አየር መንገዶች በአውሮፓ እንዲበሩ የተፈቀደ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት ሃገራት አየር መንገዶች ለመንገደኞች ደህንነት አስጊዎች ናቸው በሚል በክልሉ እንዳይበሩ መታገዱን ዘ-ሐበሻን ከሲሲቲቭ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል

No comments:

Post a Comment

wanted officials