Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, June 19, 2016

የጳጳሳት ሹመትና ተቸዎች ያላወቁት እውነት

የጳጳሳት ሹመትና ተቸዎች ያላወቁት እውነት

የጳጳሳት ሹመትና ተቸዎች ያላወቁት እውነት የኢትዮጵያ ህዝብ በስደትም ይሁን በሃገር ቤት ቁጥሩ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው በዚያው ልክ እረኛ አባት ማስፈለጉ አያጠያይቅም እንዳለመታደል ሁኖ የሁለት ሲኖዶስ ባለቤት ከሆን ሰንበትበት ብለናል ልዩነቱን ባንደውም በየፊናቸው እየሰሩት ያለው ግን ቀላል አይደለም ምንአልባትም ባንድነታቸው ሊሰሩት አይችሉ ይሆናል ምክንያቱም ለመላ አሜሪካ ይመደብ የነበረው ጳጳስ አንድ ብቻ ነበር አሁን ውድድር ስለሆነ በሁሉቱም በኩል ቁጥሩ ጨምሯል ግን አሁንም በቂ አይደለም ምክንያቴን ወደፊት እገልጻለሁ ልዩነቱ ያመጣው መዘዝ ለትውልድ ከተረፈ ግን አደጋው የከፋ ቢሆንም ለጊዜው ግን ሁሉም በየፊናቸው ለቤተክርስቲያን እንድገት በአቅማቸው ጊዜው የሚጠየቀውን አድርገዋል እያደረጉ ነው በርግጥ ከእነሱ ብዙ ስለምንጠብቅ ከተሰራው፡ ሊሰራ የሚገባው ጎልቶ በማየታችን ድክመታቸውን አጉልተን ስንናገር እንሰማለን ይህም ለስራው ካለን ቀናኢነት እንጅ አባቶች ጠልተን አይደለም ይሁንና በስራው ቀርበን ሳንጠይቃቸው ሳናግዛቸው ወቅቱ ውስብስብ መሆኑን ሳንገነዘብ ያቅማቸውን ውስንነት ሳንረዳ መፍረዱ የኛን የአረዳድ ድክመት ከማሳየት አልፎ በነሱ ላይ ለውጥ ሊያመጣ ግን አይችልም በስደት የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች ለመሾም የሄደበት መንገድ አግባብነት አለው ምክንያቱም ሲኖዶስ እስካለ ድረስ ጳጳስ መሾም ጥያቄም ውስጥ ሊገባ አይገባውም የሲኖዶስ ሥራው ምንሆነና ነው። መጀመሪያ እራሱን ሲኖዶሱን በሰው ሃይል ማጠናከር ተገቢ ነው ባይሾሙ ነበር እንጅ የሚገርመው መሾማቸው ምን ይገርማል ብዙ ሰዎች የማያስገርመው ያስገርማቸዋል ቅዱስ ሲኖዶስ ጳጳስ ለምን ሾመ ብሎ መጠየቅ እናት ለም ልጅ ትወልዳለች ብሎ እንደ መጠየቅ ያህል ያስቆጥራል ወይም የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣንና ልዕልና አለመረዳት ነው በሀገርቤቱም ይሁን በስደቱ ለቤተክርስቲያኒቱ የሚያስቡና የሚሰሩ አባቶችን ህዝቡ በስማ በለው ሳያውቃቸው መተቸቱ ልማዳዊ ባህል እየሆነ መጥቷል የማያውቀውን የሚተች ህዝብ እየበረከተ መምጣቱ እጅግ ያሳዝናል አባቶቻችን እስከነ ድክመታቸውም ቢሆን ወርቃማ ናቸው የነሱን ሩብ ዘመን ሳንኖር የሰሩትን ስራ እንኳን አይተን ሳንጨርስ ለመተቸትና ለመናገር እንቸኩላለን እኛ ምን ሰራን ብለን ግን እራሳችን ጠይቀን አናውቅም አሁን የተሾሙ ጳጳሳት ጉድለታቸው ምንድ ነው ከተሿሚዎቹ አንዱ ምን አልባትም አባ ወልደ ትንሳኤ አሳማ ብሉ በለው አስተምረው ከሆነ ይህን ቀድመው በመጻፍ ያስቀመጡት ብጹእ አቡነ ጎርጎሪዮስ ናቸው የሳቸውም ትምህርት ከውጭ ሀገር ተምረው ሲመለሱ አውሮፓውያን ሳይመርጡ ሲበሉ ማየታቸው የእኛን ሀገር ትውፊትና ባህል በተጣረሰ መልኩ ጽፈዋል ቢሆንም ብጹነታቸውን እንወዳቸዋለን ታዲያ አባ ወልደ ትንሳኤን /አቡነ በርናባስ/ ለምን እጠላቸውአለን ለመሆኑ መናፍቅ ብሎ ለመናገር እኮ ተናጋሪው መጀመሪያ የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና ትውፊትና ባህል ለይቶ ማወቅ አለበት የቱ ነው መናፍቅ የሚያሰኘው የሚለውንም መረዳት አለበት አንዳዶቹ የግል አለመግባባታቸውን ሃይማኖታዊ ሽፋን በመስጠት ለማስጠላት ይሞክራሉ እንዴውም አባ ወልደ ትንሳኤ/አቡነ በርናባስ/ ትምህርቶቸ መሠረት ያደረጉት የአቡነ ጎርጎሪዮስን መጻህፍቶችን ነው በመሆኑም ስህተት የለበትም እንጅ ቢኖርበት ተጠያቂ የሚሆኑት አቡነ ጎርጎሪዮስ ናቸው አንባቢ ማስተዋል ያለበት ሃቁ ነው የግል ጥላቻ በቤተክርስቲያን ላይ ባይጸባረቅ ጥሩ ነው ከሆነም ደግሞ ሰው መወቀስ ያለበት በሰራው እንጅ ሌላ በሰራው መሆን የለነበትም አባ ወልደ ትንሳኤ ብዙ ጥሩ ኳሊቲ አላቸው በምንኩስናቸው አይታሙም የገንዘብ ጾር የለቸውም አንደበተ ርቱእ ናቸው ቤተክርስቲያንን በብዙ መልኩ ይጠቅማሉ ከበብዞች ያጣነውን ንጽህና ማገኘቱ በራሱ ቀላል አይደለም በርግጥ ደፋር አስተማሪነታቸው ቢወደድም ሃይማኖት መገለጫው ባህል ነውና ይህን ያለማክበር አዝማሚያ በአንድ ወቅት አሳይተው ነበር አሁን ግን ትተዋል ብዞቹ አባቶች በሃገር እርቀት በዘመን ብዛት በሀገር ውስጥ የሚደረገውን አያውቁም ቀደምሲል ነቃ ያሉት አገልጋዮች እንደ ሃይማኖት ለዋጭ ይቆጠሩ ነበር አለባበሳቸው አነጋገራቸው ሁሉ ይመዘን ነበር እናም መናፍቅ የሚትለው ቃል በሆነ ባልሆነው ስንጠቀምባት ስለ ቆየን አሁን ቤተከርስቲያኒቱ ሊያፈርሱ የተነሱትን ማጋለጥ እንኳን አልተቻለም እራሳቸው በወብሳይት እያስተዋወቁ አለን እያሉ ህዝቡ የራሱ የሆኑት ለይቶ ለማወቅ እድል አላገኘም ይልቁን የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ህዝቡን በማደናገር የሆኑትን ካልሆኑት መለየት እንዳንችል አድርገውናል ይህንን በማስመልከት ብዙ አላስተማሩ ይሆናል ክፍተቱ ግን የኢንፎርሽ እጥረት ነው ይህም የሆነው ብዞቹ አባቶች ከመጡ ከ 20 ዓመት በላይ የሆናቸውና ያንጊዜ ያለውንና አሁን ሆን ተብሎ ቤተክርስቲያን ለማዳከም የሚሰራውን አለማዎቃቸው ነው የችግሩ ምንጭ ይህ ካልሆነ በቀር አሁን የተሾሆሙ አባቶች የሚተቹበት ነውርም ሆነ ነቀፋ የለባቸውም ሿሚዎች ቤተክርስቲያኒቱ በሁለመናዋ ልቃ እንድትገኝ የደከሙ አባቶች ናቸው ያባቶችን ስህተት በማስረጃ አስደግፎ የጻፈ አላየሁም ጥላቻን ያንፀባረቀ ምቀኝነት መሠረት ያደርገ ብዙ ተብሏል እውነተኛ ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆር ካለ አባቶችን ቀርቦ የወቅቱን ተጨባጭ እውነታ ማስረዳቱና መረዳቱ ከከንቱ ጥላቻ ያድናል አንባቢ ሆይ እውነቱ ማወቅ ተገቢነው አቡነ መልከ ጼዴቅን ያህል ጸሎተኛ ጾሚ ለአግልግሎት ቀናኢ የለም ቀርበህ እወቃቸው በሩቅ አተች ለአንተም ጥሩ ነው እራስህን ታይበታለህ ምንአልባትም ወደፊት በወሬ መጥላት ታቆማለህ ይጠቅምሃል ወደፊት ሰፋ አድርገን እንመለስበታለን እስከ ዚያው ግን አባቱ የሚሰድብና የሚያቃልል ልጅ ከመሆነ እግዚአብሔር ይጠብቀን ይቀጥላል ከሊቀ መራህያን ማንኛውም ሰው እውነቱ ማወቅ ከፈለገ በንጹ አይምሮ በዚህ እሜል ሊያገኘኝ ይችላል jemis1968@gmail.com

No comments:

Post a Comment

wanted officials