Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, June 2, 2016

በቃሊቲ በሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የሚደረገው ጫና ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡



በቃሊቲ ወህኒ ቤት በሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ በእስር ቤቱ ሃላፊዎች የሚደረገው ጫና ተጠናክሮ መቀጠሉ
ታወቀ። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የ18 አመት እስራት ተፈርዶበት በወህኒ ቤት የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ካለፈው
ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ ከቤተሰብ እንዳይገናኝ ተከልክሏል፣ ስንቅ እንዳይገባለትም ዕገዳ ተጥሎበታል።
መስከረም 2003 ዓም ጀምሮ ላለፉት 5 አመታት ያህል በአሸባሪነት ተከሶና ተፈርዶበት በወህኒ ቤት የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ቀደም ሲል መጽሃፍ እንዳይገባለት የተደረገ ሲሆን፣ ማናቸውም ጽሁፍ እንዳይጽፍ ባዶ ወረቀቶችን እንዲሁም ወንበርን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጽህፈት ማሳሪያዎችን እንደተወሰደበት መረዳት ተችሏል።
ከ1985 ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ውስጥ ግንባት ቀደም ከነበሩት ጋዜጠኞችና የፕሬስ ባለቤቶች አንዱ ሆኖ የዘለቀው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቀደም ሲል ለሰባት ጊዜያት ያህል የታሰረ ሲሆን፣ የአሁኑን ጨምሮ ሁሉም ክሶች ሃሳቡን በፁሁፍ ከመግልጹ ጋር የተያየዘ መሆኑን መረዳት ተችሏል።ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከቤተሰብ እንዳይገናኝ፣ ወይንም በቤተሰብ እንዳይጠየቅ ስለተከለከለበት ምክንያት የታወቀ ነገር የለም።
ኢሳት ( ግንቦት 23 ፥ 2008)

No comments:

Post a Comment

wanted officials