ኢሳት (ሰኔ 15 ፥ 2008)
የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ ለብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተሳሳተ መረጃ ሲሰጡ እንደነበር ዛሬ ረቡዕ የወጣ መረጃ አመለከተ።
ሪፕሪቭ የተባለው ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አንዳርጋቸው ጽጌን ለመርዳት ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ የብሪታኒያ ባለስልጣናትን ላይ እንቅፋት ሆኖ እንደቆየና፣ በሰውየው መለቀቅ ጉዳይ ላይ ተስፋ እንዲቆርጡ ጥረት ሲያደርግ እንደነበር አጋልጧል።
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የት እንደታሰሩ ለመናገር ፈቃደኛ እንዳልነበሩና የቆንስላ ጉብኝቶችን ጨምሮ ለመታሰራቸው መሰረታዊ የህግ አግባብነት ያላቸውን ጥያቄዎችን ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ሪፕሪቭ በመግለጫው አትቷል። የብሪታኒያው የውጭ ጉዳይ ሚስተር ፊሊፕ ሃመንድ አቻቸው የሆኑት የኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም መሰረታዊ ጥያቄዎቻቸውን እንኳን በተደጋጋሚ ለመመለስ ባለመፈለጋቸውን ሲማረሩ እንደነበር መገለጹ ተመልክቷል።
በተመሳሳይ ሁኔታም የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ያለቀለት በመሆኑ ጠበቃ እንደማያስልፈልጋቸው ለብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መግለጻቸው ተመልክቷል።
የሪፕሪቭ ሪፖርት እንደተመለከተው፣ አቶ አንዳርጋቸው በታሰሩበት በሁለት የሰቆቃ አመታት፣ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል የገቧቸውን ነገሮች ሁሉ በተደጋጋሚ ሲያጥፉ እንደነበር ገልጿል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የህግ መብት እንደሚጠበቅላቸው በቅርቡ ቃል የተገባላቸው ፊሊፕ ሃምንድ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ሰቆቃ ከማባባስ/ከማስረዘም ባለፈው ምንም መፍትሄ አያመጡም ሲሉ የሪፕሪቭ ዳይሬክተር የሆኑት ማያ ፎዓ መናገራቸው ተገልጿል።
No comments:
Post a Comment