Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, June 25, 2016

ሶማሊያዊው የአትሌት ገንዘቤ ዲባባ አሰልጣኝ ታሰረ

 የአትሌት ገንዘቤ ዲባባ አሰልጣኝ ጃማ ኤደን ስፖርተኞች ከሚወስዱት አበረታች ዕጽ ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ ስፔን ውስጥ መታሰሩ ተሰማ::
ገንዘቤ ከወራት ወዲህ በኢዩጂን፡ በኦስሎና ስቶክሆልም የሩጫ ውድድሮች የነበሯት ሲሆን ባልታወቀ ሁኔታ በነዚህ ውድድሮች ሳትሳተፍ መቅረቷ አይዘነጋም::
የዓመቱ ምርጥ አትሌትነትን እና ሌሎች ሽልማቶችን የጠቀለለችው ገንዘቤ የወቅቱ የ1 ሺህ 500 ሜትር የዓለም ሻምፒዮና ስትሆን ሶማሊያዊ ዜግነት ያለው አሰልጣኟ በስፔን በካታሎኒያ አትሌቶችን ሰብሰበው በሚያሰለጥኑበት አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ መያዙን የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ዘግቧል;:
ከሶማሊያዊው አሰልጣኝ ጋር እነማን አትሌቶች እንደተነካኩ የተዘገበ ነገር የለም::

No comments:

Post a Comment

wanted officials