Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, May 27, 2014

የግንቦት 20 የግፍ ሰለባዎች nአርአያ ተስፋማሪያም


የግንቦት 20 የግፍ ሰለባዎች 
አርአያ ተስፋማሪያም ፦ አበበ ይባላል፤ የኦህዴድ/ኢህአዴግ አባል ሲሆን ግልጽ ያልወጣ ከፍተኛ ቁልፍ የደህንነት ስልጣን በመለስ ዜናዊ የተሰጠው ነው። ከምኒልክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ህንፃ 6ኛ ፎቅ ይኖር ነበር። (አሁን ይኑር አይኑር አላውቅም)..1994ዓ.ም ነው፤ በህንፃው ዙሪያ ጫማ በመጥረግና ጀብሎ በመቸርቸር ይተዳደሩ ከነበሩ ወጣቶች መካከል ሱልጣን የተባለ የ22 አመት ወጣት ነበር። ለደህንነቱ ባለስልጣን ወጣት ሱልጣን ይላላካል። በጊዜው ከላወንደሪ ልብስ እንዲያመጣለት ይልከውና ሱልጣን ይዘገያል። አበበ እሳት ጐርሶ..በስፍራው የነበሩ የሱልጣን ጓደኞችን “አላያችሁትም?..የት አባቱ ነው የዘገየውና የጠፋው?..እኔ አይደለሁም..” እያለ በዛቻ ይፎክራል።

የተላከውን ለማምጣት እንደሄደ ይነግሩታል። …ከዚያም ሱልጣን ልብሱን ይዞ ይመጣል። ማጅራቱን አንቆ በቦክስ እየጐሸመና እያንገላታው ወደ ህንጻው ይዞት ይገባል። በዛው ቅጽበት ከ6ኛ ፎቅ ወጣቱን ቁልቁል ወርውሮ በአሰቃቂ ሁኔታ ገደለው። በስፍራው የነበሩ የሟች ሱልጣን ጓደኞች በፖሊስ እየተደበደቡ እንዲሄዱና ዳግም በአካባቢው ዝር እንዳይሉ ተደረገ።…ይህን አሳዛኝና የጭካኔ ተግባር በወቅቱ በኢትኦጵ ጋዜጣ አውጥቼዋለሁ።…ኑሮውን ለማሸነፍ ከገጠር ድረስ የመጣን ምስኪን በእንዲህ ያለ ጭካኔ የገደለውን ሹም የጠየቀው አልነበረም። ሁሌም ከአእምሮዬ ከማይጠፉ የግፍ ሰለባዎች አንዱ ነው። በነገራችን ላይ አበበ በትግራይ ሆቴል መስከረም 1 ቀን 1995ዓ.ም ሆን ተብሎ በተቀነባበረው የፈንጂ ጥቃት ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደነበረ ላረጋግጥ እወዳለሁ።

ይህን በተመለከተ በመረጃ የተደገፈ ሰፊ ዘገባ በወቅቱ በጋዜጣ ይፋ ተደርጐዋል።…ሌላው የደህንነት ሹም የነበረው የሕወሐት አባል ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል ድርጊት ይገኛል። ቦሌ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ “ሊሰርቀኝ ቤቴ ሲገባ ያዝኩት” በሚል ሁለት እግሮቹን በጥይት ደብድቦ (ማንነቱ የማይታወቅ ወጣት) መንገድ ዳር ሲጥለው በአይናቸው ከተመለከቱ ጐረቤቶች አንዷ እዚህ ትገኛለች። የወጣቱ መጨረሻ አይታወቅም።.. ወ/ስላሴ እጅግ አረመኔ ከሆኑ ነፍሰ ገዳዮች አንዱ ነው። የቤተ መንግስት የደህንነት ሹም ዘርኡ መለስን በስለት ያረደ፣ የመገናኛ ት/ስፖርት ሚ/ር አየነው ቢተውልኝን በክራቫታቸው
አንቆ የገደለ…ፋሺስት ነው። ብዙ እጅግ ብዙ ግድያዎችን የፈፀመው ወ/ስላሴ በሙስና ተከሶ እስር ቤት ይገኛል። ..የግፍ ሰላባዎች ብዙ ናቸው!!

No comments:

Post a Comment

wanted officials