Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, May 30, 2014

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ለሰማያዊ ፓርቲ ግብዣ የ20 ሰው መግቢያ ካርድ ገዙ፡

የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ታላቅነት!!
----------------------------------------------
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ሰማያዊ ፓርቲ ላዘጋጀው የእራት ግብዣ የ20 ሰው መግቢያ ካርድ ገዙ፡፡ የመግቢያ ካርዱን ለመግዛት ያነሳሳቸውን ነገር ሲገልጹ ‹‹ከዚህ በፊት ታስረው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ያደረጉትን የእራብ አድማና ያሳዩትን የትግል ቆራጥነት በመመልከቴ ነው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ የእራብ አድማ ላይ የነበሩትን ወጣቶች አስር ቤት ድረስ በመሄድ የእራብ አድማቸውን እንዲያቆሙና ምግብ እንዲበሉ አድርገው የነበር መሆኑም ይታወቃል፡፡በጡረታ የሚተዳደሩት አዛውንት ምሁር የ20 ሰው መግቢያ ካርድ መግዛታቸው እጅግ የሚገርም ሲሆን አባቶቻችን ለትግል ያላቸውን ቁርጠኝነትም ፍንትው አድርጎ የሚያሳይም ነው፡፡ የ84 አመት እድሜ ባለጸጋው ፕሮፌሰር ለሚወዷት ሀገራቸው ከ60 አመት በላይ ሶስት አምባገነን ስርዓቶችን ሞግተዋል፡፡ ነገር ግን ትግላቸው ፍሬ አፍርቶ ማየት ባይችሉም እስከዚች ሰዓት ድረስ ተስፋ አልቆረጡም፡፡ እኝህ ታዋቂ ምሁር ሀገራቸውን በሙያቸው ያገለገሉና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤን በገንገዘባቸው ያቋቋሙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ አሁን ያደረጉት የታላቅነት ስራም ለወጣቶቹ ከፍተኛ ውለታ የጣለባቸው ሲሆን ዕራያቸው እውን ይሆን ዘንድም ትልቅ የትግል ስንቅ ነው፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ሆይ አንተ የታላቅነት ምልክት ነህ፡፡እውነት ማለት አንተ፤አንተ ማለት እውነት ነህ፡፡ ምንም እንኳን ተፈጥሮ ብትታገልህም አንተ ግን በህይዎት ዘመንህ ለአምባገነንነት ተንበርክከህ አታውቅምና ታላቅ ምስጋና ይገባሃል፡፡ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የአንተ ውለታ አለባቸው፡፡ስላደረግከው መልካም ስራ እድሜና ጤና ይስጥልን ከማለት ውጭ ምን እንላለን፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials