Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, May 28, 2014

ልማት እና ዲሞክራሲ አለ ማለት በህዝብ ልጆች መስእዋትነት ላይ እንደማሾፍ ይቆጠራል።

ልማት እና ዲሞክራሲ አለ ማለት በህዝብ ልጆች መስእዋትነት ላይ እንደማሾፍ ይቆጠራል። 
#Derg_Also Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) #Ethiopia 

መኖር ደጉ አለን ብለን እንደሌለን እየኖርን ነው የአንድ ወጣት እድሜ 23 አመት .... ወታደራዊው አገዛዝ እንዳሰና ሲጫወት ወደ ከርሰ መቃብሩ ቢወርድም ..... የፖለቲካ ቁማሩ ግን የህዝብን ደም እንደጠጣ እንደበላ አለ .......
(ምንሊክ ሳልሳዊ)
የልማት አርበኛ የዲሞክራሲ ጀግና እያለ ራሱን የሚጠራው ሕወሓት .... አምባገነናዊ የጎሳ ፖለቲካውን መርጨት ከጀመረ 23 አመት ቢቆጠርም አንዳችን የልማት እና የዲሞክራሲ ብልችታዎችን ለማየት አልታደልንም ..... እነ በለጸግን የቴክኖሎጂ ጥግ ለመድረስ እየደከመን ነው ያሉ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ታላላቅ እና ሃያላን ሃገራት እንኳን እንደወያኔ አላናፉም .... በየድህረገጹ ስለ ልማቱ እና ዲሞክራሲው የሚያላዝኑት ራሳቸውን ከሞቱ እና ከወደቁ ኋላቀር እና ማርኪሲስት መንግስታት ጋር የሚያወዳድሩልን የአንድ ፓርቲ ማለትም የሕወህት ኮተታም ካድሬዎች መሆናቸው ሌላው የፖለቲካ ቅራቅንቦ ነው... የሚገርመኝ እነ ታገልን የሚሉት ብአዴን እና ኦሕዴድ የት ገቢ ምንም ስለ ዲሞክራሲ እና ልማት አይተነፍሱም .... አላመኑበትም ብለን እንደምድመው።



ዱብ ዱብ ወደ ግንቦት 20 መከበሪያው ለመትመም አበል አለዋ እንዴት ነው በዚህ ኑሮ ጣራ በነካ ዘመን በሰልፍ 50 እና 100 ብር ከተገኘ ተበርቻቻ በተባለ ድግስ ላይ ተሳትፎ ወያኔ በመደበው መኪና ቤት ድረስ ከመጣን ከሰከርን .. ነጻነት ምናገባን የሚለው ካድሬ በገፍ በተጃጃለበት ዘመን ... ምን ፋይዳ አለ ከወያኔ የሚጠበቅ .. የካድሬዎቹ መጃጃል በራሱ በወያኔ ውስጥ ለሚኖረው ለውጥ ደንቃራ ፈጥሯል፡ አመራሮቹ ምነው አምባገነን አይሆኑ ድርጅቴ ኢዲሞክራሲያዊ ነው ብሎ የሚጠይቅ የሚታገል ካድረ ሁሉ ሆዳም ሆኖ በህይወት አለመኖሩ ..ልብሶ ሲሄድ እኮ ካድሬ ሁሉ ስእው ይመስላል በህይወት የለም እኮ ..ልማቱ እና ዲሞክራሲው አንፍዘውታል ።

ልማቱን ሲያስቡት የሰብ አዊ መብቱን የነጻ ፕሬሱን የግለሰብ እና የቡድን ነጻነቱን ግን አስበው ተንፍሰው አያውቁም ፡፤ እስር ቤቶች በመቶ ሺህ በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ እስረኖች ተጥለቅልቋል። ራሳቸውን በዚህ ጉዳይ ለምን ከደርግ አያወዳድሩትም ?
የፍትህ አካላት በባለስልጣን ተጽ እኖ ስር እየዳከሩ ነው ይህንን ለምን አያነሱትም ?
የባለስልጣናት ሙስና ጣራ ነክቷል። ይህ ደሞ ካየነው በግልጽ እንደሚታወቀ ባለስልጣናት የሚኖሩት ኑሮ እና ደሞዛቸው በፍጹም በፍጹም አይገናኝም ... እነሱ አይደሉም ካድሬዎቹ የሚኖሩት ኑሮ እና ደሞዛቸው ሃራምባ እና ቆቦ ነው። ይህ ለምን በፌስቡክ ኮተታም ካድሬዎች አይጻፍም ..ይህን ልማት እኮ ነው ... ቁጥጥር በራሱ ልማት ነው።
ሌላው የድህንነቱ ክፍል እንዳሻው ብዜጎች ላይ ፈላጭ ቆራጭ ከመሆን ጀምሮ እስከ ሕገወጥ ዘረፋ ይፈጽማል። በደህንነት ክፍሉ ከባድ መንግስታዊ ወንጀሎች ይፈጸማሉ ይህም ማጋለጥ ሌላው ልማት ነው።
ወታደሩ እና ፖሊሱ ለህገመንግስት ተገዢ እንዲሆኑ እየተደረገ አይደለም አብዛኛው ወታደራዊ መኮንኖች የፓርቲ ግልባጮች ናቸው። ሃገራዊ የመከላከያ እና የፖለኢስ ሰራዊት እንዲገንባ ለምን አይደረግም ይህም ሌላው ልማት ነው፡
ፕሬሱ ለአንድ ሃገር እድገት መሰረት ለዲሞክራሲ ፍጥነት እና ለህዝብ ንቃተ ህሊና ስፋት ታላቅ አስታውጾ እንዳለው እይታወቅ ይህ እንዳይሆን ግን መንግስታዊ ይሽብር አካላት በጋዜጠኞች በጸሃፊይን በምምህራኖች እና ህዝብን በሚያስተምሩ አካላት ላይ ከፍተኛ የሰቆቃ ወንጀል ሲፈጽሙ ሲያስሩ ሲገሉ እያየን ንነ ይህንንም መዋጋት ሌላኛው ልማት ነው።

ብዙ ብዙ ማለት እንችላለን ..የግንቦት 20 ፍሬ እና ትሩፋት ተጠቅሶ አያልቅም .... በብድርና እዳ ፎቅ ግንብቶ እና ኪስን አደልቦ ልማት የለም .... ልማት ህዝብን ሲያሳትፍ እና የህዝብን ልጆች መብት እና ነጻነት ሲጠብቅ ነው ብዙሃን እያለቀሱ ጥቂቶች የሚፎልሉበት በመሳሪያ ሃይል የሚሽለልበት አገር ላይ ልማት እና ዲሞክራሲ አለ ማለት በህዝብ ልጆች መስእዋትነት እንደማሾፍ ይቆጠራል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials