ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ላለፉት ሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን የአራተኛ ዙር ታጋዮችን አስመረቀ
የኢትዮጵያዊያንን ስቃይና መከራ ሊያቅብና እንባቸውን ሊየብስ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛው ሕወሃት የደረሰባትንና እየደረሰባት ያለውን ውርደት ወደ ክብር ለመለወጥና የናቋትና ያዋረዷት በፍትህ ሚዛን ላይ እንዲቀመጡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ለማድረግ ዓላማየ ብሎ ምሎ ዱሩ ቤቴ ካለ ገና ሁለት ዓመት እንኳ ያልሞላው ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በቃሉ መሰረት አራተኛውን ዙር የታጋዮች የምረቃ በአል ሚያዚያ 26 2006 ዓ/ም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ማክበሩን አስታወቀ። ይህ የአራተኛው ዙር ስልጠና በሰልጣኞች ቁጥርም ሆነ በስልጠናው ጥንካሬ ካለፉት ሶስት ዙሮች በእጅጉ የተለየ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ያለውን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና ወቅቱ የሚፈልገውን ቴክኖሎጅ በመጠቀም መረጃን መቀበልና ማስተላለፍን የጨመረም እንደነበር ተያይዞ ተጠቅሷል።
በሀገር ውስጥ ፋሽስት ወያኔ እያደረሰው ባለው መረን የወጣ ግፍ የተበሳጩና ሁሉም ልክ እንዳለው ለማሳየት ቆርጠው የተሰለፉት እነዚህ ምሩቅ ታጋዮች ከወታደራዊው ስልጠና በተጨማሪ የፖለቲካ፣ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ሌሎችንም ተያያዥ ክህሎቶችን በበቂ ሁኔታ እንደቀሰሙም ተጠቁሟል። ስልጠናው ታጋዮቹ ወደፊት ከሚያጋጥማቸው ጠንካራ ፈተናና ከሚሰለፉበት ጥብቅ ግዳጅ አንጻር በቀላሉ ተስፋ እንዳይቆርጡ ለማድረግ በአካልም ሆነ በመንፈስ ዝግጁ እንደሚያደርጋቸው የተገለጸ ሲሆን የተጀመረው ሕዝባዊ ትግል በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በጋራና በተቀነባበረ ሃይል ለድል እንደሚበቃና ይህን የጋራ ሃይል በጠነካራ እጆች ላይ ላመስቀመጥም የተሰጠው ስልጠና ከበቂ በላይ ነበር ተብሏል።
ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በሀገር ውስጥ እንደማእበል እየገነፈለ ያለውን የአታግሉን የሕዝብ ጣያቄ በተደራጀና በተቀነባበረ መንገድ በተገቢው መልኩ ለማስተናገድ እንዲችል እንደ ድርጅት ከመቼው በላይ ራሱን እያደራጀና እያጠነከረ እንደሚገኝና ምቹ አታጋይ ተቋም ሆኖ ለመውጣት ሌት ተቀን እየደከመ መሆኑም ተያይዞ ተጠቅሷል። በታጋዮች ስልጠና ወቅት የተገኙ አንዳንድ የክብር እንግዶች እንደጠቆሙትም ”ባሁኑ ሰአት በሀገር ውስጥ ያለው ሁኔታ ከመቼውም በላይ የተመቻቸ ነው” ካሉ በሗላ ”ሕወሃት የሚተማመንበት ወታደሩ እንኳ ቁጥሩ ካልሆነ በቀር ልቡም ሆነ መንፈሱ ከሕዝብ ጋር ነው፤ በሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች እየሆነ ያለው ወያኔ በእርጅና ዘምኑ ማብቂያ ላይ መሆኑን ነው የሚያመለክተው። ስለሆነም በመረጃ መንቀሳቀስና በትብብር መስራት ባጭሩ ለድል ያበቃል። ለዚህ ደግሞ የዛሬ ምሩቅ ታጋዮች ያገኙት ስልጠና ለታሰበው ስኬት የሚያበቃቸው ነው” በማለት ትዝብታቸውን አጠቃለዋል።
በምረቃው ማብቂያ ላይ ራሱን ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ብሎ ከሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ለፋሽስት ወያኔ ከፍተኛ ስጋት እንደሆነ በማስረገጥ የጠቆሙት የሕዝባዊ ሃይሉ ሃላፊዎች፤ ከዚህ በፊት ፋሽስት ወያኔ በከፍተኛ ወጭና ጥንቃቄ ሕዝባዊ ሃይሉን ለማፈራረስና ለማትፋት በከፍተኛ ሁኔታ የሰራ ቢሆንም በሕዝባዊ ሃይሉ መረጃና ደህንነት ክፍል መክሸፉን አስታውሰው፤ ዓላማችንን ከዳር ለማድረስና የሕዝባችንን አርነት ለመመለስ ሀገራችንንም ከወያኔ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት በምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አስተላለፈዋል። ይህን ታሪካዊ ጥሪ ለመመለስና የሀገርና የትውልድ ጠላት የሆነውን ወያኔ ሕወሃትን ለማስወገድ አብረን እንቁም ሕዝባዊ ሃይላችንንም ተቀላቀሉ ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ምንጭ፣ ግንቦት 7
No comments:
Post a Comment