Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, May 30, 2014

ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ተመረቀች

ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ተመረቀች

(ኢ.ኤም.ኤፍ) የቀድሞ የቅንጅት ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት የነበረችው እና በኋላም በኢህ አዴግ ታስራ የተፈታችው ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ፤ ከሁለተኛው እስር ከተፈታች በኋላ፤ በ2011 ወደ አሜሪካ በመምጣት በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ትምህርቷን ስትከታተል ቆይታ በያዝነው ሳምንት ከሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተመርቃለች።
Birtukan Midekesa graduated from Harvard university
Birtukan Midekesa graduated from Harvard university
የሬገን ፋሴል ዲሞክራሲ ተቋም ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳን ጨምሮ ለአቶ ስዬ አብርሃም የስኮላርሺፕ በመስጠት ትምህርታቸውን በላቀ ሁኔታ እንዲከታተሉ አድርጓል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፕ/ር መረራ ጉዲናም የዚህ እድል ተጠቃሚ እንደሆኑ የኢ.ኤም.ኤፍ የቅርብ ምንጮች ገልጸውልናል። ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከተመረቀች በኋላ ወደ ፖለቲካ አለም በመግባት የመሪነት ሚናዋን እንደገና ትጫወታለች ተብሎ አይጠበቅም። አሁን ያላወቅነው ነገር ቢኖር፤ ‘ወ/ት ብርቱካን ኑሮዋን በአሜሪካ ትቀጥላለች ወይስ ወደ አገር ቤት ትመለሳለች’ የሚለው ነው። ለማንኛውም ኢ.ኤም.ኤፍ ለወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ እና ለሌሎችም ተመራቂዎች እንኳን ደስ ያላቹህ በማለት ዘገባውን ያጠናቅቃል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials