Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, May 23, 2014

አንድነት በአዳማ ከተማ የጠራው ሰልፍ ለሰኔ አንድ መተላለፉን አስታወቀ

አንድነት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በአዳማ ከተማ ለማድረግ አቅዶት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ለሰኔ አንድ መተላለፉን ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ አስታወቀ።
የድርጅቱ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚከተለው ነው፦
የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የመሀል ቀጠና ፅ/ቤት ለግንቦት 10 ጠይቆት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በገዢው ፓርቲ የተለያዩ ሰበቦችና ምክንያቶች ሲድበሰበስ ከርሞ ለሰኔ1ቀን2006 ዓ.ም መተላለፉን የመሀል ቀጠና ጽ/ቤቱ በጠራው የአስቸኳይ ስብሰባ መወሰኑንና ይህንኑ ውሳኔውንም በቀን መወሰኛ ደብዳቤው ላይ ገልጾ ለአዳማ መስተዳድር ከንቲባ አቶ አብረሐም ማስረከቡን በመረጃ አያይዞ ገልጧል፡፡ በመሆኑም ሰኔ አንድ የአንድነት ደጋፊዎችና አባላት እንዲሁም የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የሆናችሁ ነጋዴዎች፣ተማሪዎችና ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በሰልፋችን ላይ በመገኘት በገዢው ፓርቲ ላይ የተባበረ የተቃውሞ ድምጻችንን በሰላማዊ የትግል ስልት መንፈስ እንድናሰማ ጋብዘናችኋል፡፡ ሰኔ አንድ አይቀርም!
መነሻችን 4፡00ሰዓት ፣አዳማ ራስ ሆቴል (የቀድሞው መነን ሆቴል) ሆኖ፣ በፍራንኮ ሆቴል አርገን ወደ ምንጃር ጎዳና እንወጣና፤ ከሳር ተራ በአዲሱ ግንብ ገበያ ወደ መብራት ሐይል አቅንተን፤ ቁልቁል በአንደኛ መንገድ (ግርማሜ ነዋይ ጎዳና) ከደራርቱ አደባባይ ፊት ለፊት ካለው

No comments:

Post a Comment

wanted officials