Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, May 26, 2014

ኡስታዝ አብዱሽኩር ዳውድ ከእስር ተለቀቀ

ኡስታዝ አብዱሽኩር ዳውድ ከእስር ተለቀቀ
በፌደራሉ አቃቤ ህግ ሰዎችን በሽብር ድርጊት እንዲሳተፉ ስትመለምል ነበር(ለአልቃኢዳ የምስራቅ አፍሪካ ክንፍ) በሚል በሃሰት ክስ ተከሶ በማእከላዊ ለ ረጅም ወራት በስቃይ እና በድብደባ ካሳለፈ በኋላ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተዘዋውሮ ለ 3 አመተታ በእስር ሲሰቃይ ኡስታዝ አብዱሽኩር ዳውድ አቡበከር የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ነህ በማለት የሶስት አመት እስራት እንዲቀጣ ብይን እንደተሰጠበት የሚታወስ ነው፡፡
ሆኖም የፌደራሉ አቃቤ ህግ ይግባኝ በመጠየቁ ፍርድ ቤቱ ከ 3 አመት ወደ 7 አመት ቅጣቱ ከፍ እንዲልበት በድጋሚ ብይን ሰጥቶ የነበረ ሲሆን የኡስታዝ አብዱሽኩርን የፍርድ ቤት ጉዳይ ሲከታተሉ የነበሩት ጠበቃ ተማም አባቡልጎ ለፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኛቸውን አቅርበው በሰበር ችሎቱም ጉዳዩ ታይቶላቸው ከ 7 አመት እስራት ወደ 3 አመት ዝቅ እንዲልላቸው መወሰኑን ይታወሳል፡፤
ኡስታዝ አብዱሽኩር ከታሰሩ 3 አመታትን ያሳለፉ በመሆናቸው የቅጣት ጊዜያቸውን በመጨረስ በዛሬው ዕለት ከእስር መለቀቃቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ ከሶስት አመተት በፊት መንግስት በሃሰት በመወንጀል መንግስት ሃይሎች ከሚኖርበት ቤት በለሊት አፍኖ ወስደውት ነበረ ሲሆን በወቅቱ ባለቤቱ መንታ ልጆችን ወልዳ አራስ እንደነበረች ይታወቃል፡፡ ኡስታዝ አብድሽኩር በመታሰሩ ቤተሰቦቹ ለከፍተኛ ችግር ተዳርገው ባለቤቱ ልጇቿል ማሳደግ ከብዷት ወደ ገጠር ከፊሉን ልጇቿል ልካ እንደነበር ተሰግለፆል፡፡ እነሆ በአላህ ፈቃድ ከ 3 አመት የግፍ አስራት ቡሃላ ኡስታዝ አንዱሽኩር በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት የእስር ጊዜውን ጨርሶ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሊፈታ ችሏል፡፡
ለቤተሰቦቹ፣ለወዳጆቹ እና በስቃዩ ጊዜ ከቤተሰቡ እና ከሱ ጋር ከጎኑ ለቆመው ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ ደስ የሚያሰኝ ዜና ነው እና እንኳን አላህ በሰላም ለቤትህ አበቃህ ልንልህ እንወዳለን፡፡ አላሃምዱሊላህ !!! አላሁ አክበር!!!
©ABU DAWD OSMAN

No comments:

Post a Comment

wanted officials