የጅቡቲ መንግስት 30 ስደተኞችን ለኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች አሳልፎ ሰጠ
የአገሪቱ መንግስት ከኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ጋር በመተባበር ያሰራቸውን ስደተኞች ከፍተኛ ስቃይ ወደ ሚፈጸምበት ጅጅጋ እስር ቤት መውሰዱን የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር አስታውቋል።
ግንባሩ እንዳለው እርምጃው የተወሰደው የኦጋዴን ተወላጅ የዳያስፖራ አባላት በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የደረሰውን ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ካወገዙ በሁዋላ ነው።
ጅቡቲ በኦጋዴን አካባቢ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደምትደግፍ ግንባሩ አስታውቆ፣ ጅቡቲ የኦጋዴን ስደተኞችን ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፎ ሲሰጥ የአሁኑ ለ6ኛ ጊዜ ነው።
የአለማቀፉ ማህበረሰብ የጅቡቲን ድረጊት እንዲያወግዝ ግንባሩ አክሎ ጠይቋል።
No comments:
Post a Comment