የአማራው ብሄረሰብና የወያኔ ጥላቻ ወያኔ የትግራይን ወጣት አደራጅቶ በትግራይ ህዝብ ትብብር የጭቁን አማራ ህዝብን መሬትና ንብረት በጉልበት ቀምቶ በትዉልድ አገሩ እያሳደደ ለሞትና ለስደት የተዳረገዉ በሚሊዮን የሚቆጠር ነዉ።ከ1971 ዓ.ም ጀምሮ ወያኔ ከትግራይ ወደ ጎንደር የመስፋፋት ጦርነት አድማሱን ሲያሠፋ የመጀመሪያ እርምጃው በወልቃይት እና ጠገዴ የሚኖሩ የጎንደር ዐማሮችን በጅምላ መፍጀት ነበር። እስከዛሬ ምን ያህል የወልቃይት እና የጠገዴ ዐማሮችን እንደጨፈጨፉ በአሃዝ ለይቶ ለማስቀመጥ ቢከብድም በ20 ሺህዎች የሚቆጠሩትን ከምድረ ገፅ እንዳጠፉ፣ ከ70 ሺህ የማያንሱትን ደግሞ ከጥንት አባቶቻቸው ርስት አፈናቅለው ስደተኛ እንዳደረጓቸው ይታወቃል። ወያኔዎች የጎንደር ግዛት የሆነውን የወልቃይት ፣ የጠገዴ እና የፀለምት አካባቢዎችን «የትግራይ ክልል» ብለው ነጥቀዋል። በአካባቢውም ከተለያዩ የትግራይ አውራጃዎች ያመጧቸውን የራሣቸውን ዘር አሥፍረውበታል።ለምሳሌ በሁመራ የሚመረተው ጥጥ ለአድዋ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃነት ሲያገለግል ሰሊጡ ደግሞ ወደ ውጭ እየተላከ የወያኔ መሪዎችን የዶላር ክምችት በማድለብ ላይ ይገኛል።ትግሬዎች ይህም አላረካቸዉ ብሎ ታች አርማጭሆን ፡የሳንጃ መተማና ቋራ ለም የሆኑና ነዳጅ ዘይት ያለባቸዉ መሬቶችን ለሱዳን አስረከቡ። * በወሎ ክፍለ ሃገር የአላማጣን፤ኮረምን፤መሆኒን፤ዋጃን፤ባላን፤ጨርጨርን፤ወይራ ዉሃን፤ጥሙጋን ህዝብ ለም መሬቱን ወደ ትግራይ አስተዳደር ክልል በጉልበት ወስደዉ የሚደርስበት ግፍ እጅግ የከፋ ነዉ። ዛሬ በኦፍላ(ኮረም)፤በራያ አዘቦ(መሆኒ)ና አላማጣ ወረዳዎች መናገር፣መጻፍ፣ መሰብሰብ፣መቃወም እና መደራጀት ፈጽሞ የማይታሰብ ነዉ። በሃገራችን ያለፈ ታሪክ ውስጥ እንደ ወያኔ ያለ መሰሪና ጠባብ ብሄርተኝነትን የተላበሰ አስተዳደር ወይም የፓለቲካ ብድን ተፈጥሮ አያውቅም። የወያኔ ብህል “እኔ ከሞትኩ ስርዶ አይብቀል” ነው። ዛሬ በጎሳ፤በዘር፤ በሃይማኖት የተከፈለችው ውድ ሃገራችን የእነዚህ ጠባብ ብሄርተኞች መጨፈሪያ ሆናለች። በአንድ በኩል ሃገር እየገነባን ነው ሲሉን፤ በሌላ በኩል ለዘመናት አብሮ የኖረን ህዝብ እያናከሱ በህዝባችን ህይወት ቁማር ይጫወቱበታል። ጅምራችው ቁማር፤ ማጭበርበር፤ መግደል፤ ማፈን ነው። የበረሃው ታሪካቸው የሚዘክረው ያንኑ ነው። የከተማ አለቆች ከሆኑ ወዲህ ደግም ሥራቸው ሁሉ ልክ እንደ ማፊያ ነው። በተለይ በአማራው ህብረተሰብ ላይ ያላችው ጥላቻ በቃል አይተመንም። የደራሲው ማስታወሻ ጸሃፊ “ባላወራው ይሻላል” የሚለው እነዚህ የቀን ጅቦች በአማራው ህዝብ ላይ ያደረሱትን ህቡዕ ወንጀል በዓይኖቹ ስላየ ነው። ዛሬ በተለያዪ የሃገሪቱ ክፍል በአማራ ላይ የሚደርሰው በደል በወያኔ የአመራር አካላት ገና በረሃ እያሉ የታለመ እንጂ ከተማ ገብተው አለቅነትን በጨበጡ ማግሥት የታያቸው የተጣመመ የፓለቲካ ዜይቤ አይደለም። ወያኔ አማራን ከልቡ ይጠላል። ሌላውም እንዲጠላውና እንዲያሳድደው መንገንድ ያመቻቻል። ከልቡ የአማራን ህብረተሰብ ለማዳከም፤ ብሎም ለማጥፋት ሰፊ ዘመቻ ከፍቶ ይህን ሃገር ወዳድ ህዝብ በረሃብ፤ በእሥራት፤ በሞት እያዳከመው ነው። ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ አንድ መሆንና የሃገር ድንበር መከበርን አይወድም። ዛሬም ከበሮ የሚመቱትና ዘፈን የሚያሰሙት ደርግን ጥለን ነጻ አወጣናቹሁ እያሉ ነው። ደርግን የጣለው ጊዜ እንጂ ወያኔ ወይም ሻቢያ አይደሉም። የዓለም የፓለቲካ ነፋስ አቅጣጫ ሲቀይር አለንልህ ይሉት የነበሩት የፓለቲካ ሽርኮቹ እንደ ደመና ሲበኑ ደርግም እንደዛው በነነ። የወያኔ ገድል የውሽት ገድል ነው። ባዶ የከበሮ ድለቃ ነው። ወንድሙና እህቱን ገድሎ የሚፎከር ድርጅት! አያድርስ ነው!! ወያኔ የአማራውን ህዝብ ለማጥፋትም ያቀደው ለሃገር አንድነት ስለሚቆረቆር ነው። በበረሃ እያሉ የተማረኩ አማርኛ ተናጋሪ ወታደሮችን ረሽነዋል፤ ሻቢያ ታንክ ነድቶባቸዋል። አፋቸውን እየከፈተ ጥርስ አውልቆአል። ይህ ከሚያለፍ ወንዝ የተጨለፈ ወሬ ሳይሆን መረጃ ያለው ነው። ሻቢያና ወያኔ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ጥላቸውም ከድንበር ጋር የተቆራኘ አይደለም። ሌባ ሲሰርቅ አይጣላም ሲካፈል እንጂ እንደሚሉት ነው። ወያኔ መንግሥት ነን ካለን በህዋላ ደግም በጂማ፤ በአርሲ፤ በሃረር፤ በጋምቤላና በሌሎችም የሃገሪቱ ክፍል አማራው ህዝብ እንዲገድለ፤ ሃብቱን እንዲዘረፍ፤ ተራፊው እንዲባረር አደርገዋል። በማደረግም ላይ ናቸው። የተማሩ የአማራ ልጆች ለእስር፤ ለስደትና ለሞት ተዳርገዋል። ግፈኛው ወያኔ በአማራው ህብረተሰብ ላይ የሚፈጽመው በደል ተዘርዝሮ አያልቅም። ሰውን መርዝ በማብላት፤ በመኪና በመግጨት፤ በማፈንና በማሰቃየት ይጫወቱበታል። ከሃገር ውጭ በሱዳን፤ በግብጽ፤ በደቡብ ሱዳን፤በኬኒያ ያለቅጥ በተውሳሰበው የስለላ መረባቸው ውስጥ አስገብተው በማፈን ስቃይ ያደረሱባቸውና የሞት ቅጣት የፈጸሙባቸው የአማራው ብሄረሰብ ወገኖቻችን አእላፍ ናችው። ታዲያ ይህ ሁሉ ግፍ ሲሰራ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ምን ማደረግ ይጠበቅበታል? በመጀመሪያ ተጨባጭ የሆኑ መረጃዎችን ማሰባሰብ አስፈላጊ ነው። ዛሬ ዘመኑ መረጃ ለማሰባሰብ አያሌ መንገዶችን ከፍቶልናል። የመንግሥት የሃሳብ መለዋወጫ ሰነዶችን፤ የቴሌፎን ንግግር ቅጅዎችን፤ በመቅረጸ-ድምጽና በቪዲዬ የተደገፉ መረጃዎችን ማሰባሰብ ተገቢ ነው። የወያኔ ሴራ ማጋለጥና ህዝባችን ማንቃት የሚቻለው እውን መረጃዎችን በማቅረብ ነው። አየሁ ያመሳክራል፤ ሰማሁ ያከራክራል እንደሚባለው መረጃዎቻችን ሁሉ ሲፈተሹ ቆመው የሚገኙ ከእውነት ጋር የተመሳከሩ መሆን አለባችው። በእነዚህ መረጃዎች በመመርኮዝ የሚከተለውን እርምጃ መውሰድ፡፡ ፩. ለዓለም መንግስታት ማስታወቅ ፪. ህዝባችን ለሚደርስበት ግፍና መከራ ራሱን መከላከል የሚችልበትን መንገድ መተለም ፫. ወያኔ የሚያሳድዳቸውን በሃገር ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችን ወደ ጎረቤት ሃገራት ሊሸሹ የሚችሉበትን መንገድ ማመቻቸትና ከወጡም በህዋላ ጥበቃ ማረግና በሚቻለን ሁሉ ማገዝ። ፬. የተለያዬ የውጭ ሃገር ዜና አናፋሾች በህቡዕ ሃገር ወስጥ ገብተው ነገርን እንዲፈትሹ መቀስቀስ፡ ፭. በዓለም ዙሪያ ለተበተኑ ሃገር ወዳዶች መረጃ በማቀረብ በደሉን አጉልቶ ማሳየት፡ ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው። ወያኔ ልብ ገዝቶ ህዝባችን በእኩልነት ዓይን አይቶ የሃገር አንድነትንና ሰላምን ያረጋጋል ብሎ መጠበቅ ጅልነት ነው። በአማራው ህብረተሰብ ላይ የተፈጸመውና በመፈጸም ላይ ያለው እልቂት እንዲቆም ሁሉም ሃገር ወዳድ የዘርና የጎሳ ክልል ሳያግደው ሊታገል ይገባል። አማራን እንደ ጠሉ ወደመቃብር የወረድት አቶ መለስ እንዲህ በለው ነበር “እኛ ሰለአማራ ህብረተሰብ አይጨንቀንም የሚጨንቀን ነገር ያለቅጥ የተጎዳው የትግራይ ህብረተሰብ ነው”። ሰው ለቅሶ አልወጣህም ተብሎ እስር ቤት የሚገባባት ሃገር፤ ሥራ ፈላጊ በክልልህ የሚባልባት ምድር፤ ፩/፭ በሚል የተሳሰረ መርሆ ሰው መተናፈሻ ያጣባት ሃገር፤ አንድ ብሄር የበላይ ሆኖ ሌላው እንደ ሁለተኛ ዜጋ በሚቆጠርበት ምድር ነው የወያኔ ጄሌዎችና ጭፍን ካድሬዎች ሃገር ሰላም ነው የሚሉን። ተጨፈኑና ላሞኛቹህ። የልጆች ጫወታ! አይ ወያኔ! መቼ ይሆን ከዘር በሽታ የምትላቀቁት!!
ቸር ይግጠመን
አደፍርስ
https://www.youtube.com/watch?v=QUpJSmpG3q8
Ethiopia Tigres hate Amharas all the time ትግሬዎች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ
Tigres hate Amharas all the time. It is estimated that the number of Amharas and Oromos they killed for the last 20 years is almost 5 million.
ቸር ይግጠመን
አደፍርስ
https://www.youtube.com/watch?v=QUpJSmpG3q8
Ethiopia Tigres hate Amharas all the time ትግሬዎች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ
Tigres hate Amharas all the time. It is estimated that the number of Amharas and Oromos they killed for the last 20 years is almost 5 million.
No comments:
Post a Comment