ያልተሰማው የኢትዮጵያውያን ጩኸት በሚስራና ሜዲካ፡
ያልተሰማው የኢትዮጵያውያን ጩኸት በሚስራና ሜዲካ፡
ትላንት ሚስራና ሜዲካ በተባሉ የኢትዮጵያ አጎራባች በሆኑ ሁለት የደቡብ ሱዳን ከተሞች የነበሩ አራት ኢትዮጵያውያን በዚሁ ዐመት ታሕሳስ ወር ላይ የደረሰባቸውን ዝርፍያና ወከባ እየሰማሁ ምሽቱን ደስ በማይል ስሜት እንዳሳልፈው የሆንኩበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
እኒህ ኢትዮጵያውያን ለዐመታት ጥረው ግረው ያገኙትን ሀብት ሙሉ በዚያ ወር በቅፅበት እንደተቀሙና ለከፍተኛ ችግር እንደተዳረጉ ነው የነገሩኝ፡፡
በሁለቱ በአንፃራዊ ትልልቅ የሚባሉ ኑዌሮች የሚኖሩባቸው የደቡብ ሱዳን ከተሞች አብዛኛውን ቢዝነስና ንግድ የተቆጣጠሩት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ከላይ በተገለፀው ጊዜ የተነሳውን ረብሻ ተገን አድርገው በከተሞቹ የነበሩትን ኢትዮጵያዊያኖች ሀብት ንብረታቸውን ሙሉ ለሙሉ ቀምተው እንዳባረሯቸው ነው የተገለፀልኝ፡፡

በጊዜው በሳውዲ ዐረብያና ጁባ አከባቢዎች በነበሩ ከፍተኛ ችግሮች ምክንያት ይኸንን ምንም እንዳልተባለለት፣ በሚድያዎችም ያልተዘገበና የኢትዮጵያ ሹማምንትም ችላ ያሉት ጉዳይ እንደሆነ ነው የተረዳሁት፡፡
አሁን በነዚያ ከተሞች የሚኖር የነበረ ኢትዮጵያዊ ሙሉ ተጠራርጎ እንደወጣና ለዐመታት ለፍተው ያጠራቀሙት ሀብታቸውን የተቀሙቱ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳሉና በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ቤታቸውን ያደረጉ በርካቶች እንዳሉ ነው የተገለፀልኝ፡፡ መንግስትም አንዳችም ነገር እንዳላደረገላቸው ነው በሀዘን ያጫወቱኝ፡፡
ይኸ ነገር እንዴት እንዲህ ተድበስብሶና ተደብቆ ሳይሰማ እንደቀረ እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ጋዜጠኛ ነን ባዮች የታላችሁ? እስቲ እቺን ትንሽ ማጣራት አድርጋችሁ ለህዝቡ አንድ መረጃ ጀባ በሉት፡፡
ፈጣሪ ከአራቱም የዐለም መዐዝናት የሚሰሙ የኢትዮጵያኖች ጩኸት እንዲያበቃ ያድርግ፣ እንባቸውን ያብስ! አሜን አሜን!!

No comments:
Post a Comment