የሶማሊ ተማሪዎችን ከኦሮሞ ተማሪዎች ጋር ለማጋጨት ወሬዎች እየተናፈሱ ነው
ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦህዴድ -ህወሃት እንደተቀነባበረ በሚነገርለት አሉባልታ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚገኙ የሶማሊ ክልል ተወላጅ ተማሪዎችን ከኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ጋር ለማጋጨት ያለመ መሆኑን ለኢሳት ደረሰው መረጃ ያመለክታል።
የመንግስት ካድሬዎች ” የሶማሊ ተማሪዎች ከመንግስት ጎን ቆመው በኦሮሞ ተማሪዎች ዙሪያ መረጃ እየሰጡን ነው” የሚል አሉባልታ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች መነዛቱ፣ የሶማሊ ተማሪዎችን ስጋት ላይ የጣላቸው ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ከመንግስት ጎን አለመቆማቸውንና እንዲህ አይነት አሉባልታ እየተነዛ ያለው የሁለቱን ብሄር ህዝቦች ለማጋጨት መሆኑን እየተናገሩ ነው።
የተማሪዎች ወላጆች በሚነዛው ወሬ መደናገጣቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።
ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንለት የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አማካሪ የነበረውና የስዊድንን የአንቲገን ሽልማት አሸናፊ የሆነው አብዱላሂ ሁሴን ወሬው እንዲህ አይነቱ አሉባልታ በስፋት የሚሰራጨው የሁለቱን አካባቢዎች ተወላጆችን ለማጋጨት ነው ብሎአል።
ኦህዴድ /ህወሃት የተለያዩ ብሄረሰቦችን ተወላጆች ለማጋጨት እንቅስቃሴ መጀመሩን በተመለከተ ተከታታይ ዘገባዎችን ማቅረባችን ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment