Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, May 26, 2014

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ተካሂዷል

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ተካሂዷል፡፡
“በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚደረገው ጭቆና ይቁም፤ መሬታችን መሸጥ መለወጥ የለበትም፤ አንድነታችን አይከፋፈልም፤ ኢትዮጵያ አንድ ናት፤ መንግሥት የኢትዮጵያን የሕዝብ ክፍሎች ለማጋጨት የሚያደርገውን ሙከራ ማቆም አለበት” የሚሉ መፈክሮች የተሰሙበትና የተያዙበት ይህ ሰልፍ በሺሆች የተቆጠሩ ሰዎች የተሣተፉበት እንደነበረ ሥነ-ሥርዓቱን የተከታተለው ዘጋቢያችን መለስካቸው አምሃ አመልክቷል፡፡

ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላንና አጎራባች ከተሞች ጋር ተያይዞ ከተነሣው ጥያቄና ኦሮሚያ ውስጥ ሲስተዋል ከሰነበተው ሁኔታ ጋር ተያይዞ በተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ንግግር ያደረጉት የመድረክ ዋና ፀሐፊ እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ገብሩ ገብረማርያም “ስለተገደሉት ሰዎች መንግሥት ካሣ እንዲከፍል፣ ገለልተኛነታቸው በተረጋገጠ ሰዎች አጣሪ ኮሚሽን ተቋቁሞ ሁኔታው እንዲጣራ” ጠይቀዋል፡፡
ከሽማግሌዎች ተጋብዘው ንግግር ያደረጉት አቶ ቡልቻ መደቅሣ “የኦሮሞ ሕዝብ መብት መከበር አለበት፤ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች አንድ ላይ ሆነው ዴሞክራሲን ማስከበር አለባቸው፤ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚደረገውን ጭቆና ማስከበር አለባቸው፤ ኦሮሞዎች ሌላ ምንም ሊሆኑ አይችሉም – ኢትዮጵያዊ ናቸው” ብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials