ትላንት ሌሊት በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በተከሰተ የእሳት አደጋ አንድ የተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ ከጥቅም ውጭ መሆኑ ተገለጸ።
በአደጋው በተወሰኑ ተማሪዎች ላይም መጠነኛ የአካል ጉዳት ማድረሱም ተጠቁሟል ።
የዩኒቨርሰቲውን ፕሬዝዳንት ዶክተር አድማሱ ሽብሩን ጠቅሶ ፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት እንደዘገበው ፤ አደጋው ግንቦት 17 2006 ዓ.ም ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ የተነሳ ሲሆን ፤ መንስኤው ግን እስካሁን ድረስ አልታወቀም ።
እሳቱን በአካባቢው ህብረተሰብና በአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪ ኤጀንሲ ሰራተኞች ትብብር በቁጥጥር ስር ማዋል ተችላል ያሉት ዶክተር አድማሱ ፤ አደጋው በሰው ህይወት ላይ ምንም ዓይነት ጎዳት አለማድረሱን ተናግረዋል።
በቃጠሎው ወቅት ከህንጻው ለመውጣት በሚያደረጉት ግፊያ ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ተማሪዎች ከግድግዳ ጋር በመጋጨትና በመውደቅ ቆስለዋል።
ተማሪዎቹም በአካባቢው በሚገኝው አጣጥ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እነደሆነም በዘገባው ተመልክቷል።

No comments:
Post a Comment